09/27/2026
በ2028 ኦሊምፒክ ሴቶች እግር ኳስ ማጣርያ ከሩዋንዳ ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ በዝግጅት ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጋር ሁለት ዓለምአቀፍ የወዳጅነት ጨዋታዎች ያደርጋሉ።
የመጀመርያው ጨዋታ ረቡዕ መስከረም 20 ከቀኑ 9፡00 ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ሲደረግ ሁለተኛው ጨዋታ ቅዳሜ መስከረም 23 በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ የሚጫወቱ ይሆናል።