19/12/2024
አንዳንድ ጊዜ መልቀቅ የመፈወስ መንገድ ነው
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Desta huruy beyene, tigray, wukro kilta awlalo, Wukro.
19/12/2024
አንዳንድ ጊዜ መልቀቅ የመፈወስ መንገድ ነው
19/12/2024
የድግግሞሽ አዙሪት
በየቀኑ እየተነሳችሁ ከቤት ወጥታችሁ በሚኖራችሁ ስምሪት፣ የምትሰሩት ስራ፣ የምትውሉበት አካባቢ፣ የምታገኟቸው ሰዎችና የመሳሰሉት ሁኔታዎች ከሰለቻችሁና የትም እንደማያራምዳችሁ ካሰባችሁ “የድግግሞሽ አዙሪት” ውስጥ እንዳላችሁ ላስታውሳችሁ፡፡
የድግግሞሽ አዙሪት ምልክቶች፡-
1. ተስፋ መቁረጥ፣
2. ሁሉም ነገር የማስጠላት ስሜት፣
3. ነገሮች እንደማይለወጡ ማሰብ፣
4. ኋላ የመቅረት ስሜት እና የመሳሰሉት ስሜቶች ናቸው፡፡
ከዚህ አዙሪት ለመውጣት መውሰድ የምንችላቸው እርምጃዎች፡-
1. ራእያችን ወይም የሕይወታች ዋና ዓላማ ምን እንደሆነ መለየት፣
2. ከራእያችን አንጻር ወደ አዲስ ነገር ለመግባት መወሰን፣
3. በወሰንነው ውሳኔ ዙሪያ በየእለቱ የሚወሰዱን ትንንሽ እርምጃዎች መጀመር፣
4. የጀመርነውን እርምጃ በፍጹም አለማቆም፣
5. በምክር ሊያግዘን የሚችል ሰውን በመለየት ምክርን መቀበልና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
https://t.me/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
17/10/2024
አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ትናንት ምሽት 5:11 አከባቢ ምሽቱን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል ንዝረቱ መተሃራ፣ ናዝሬት፣ ደብረ ዘይት እንዲሁም አዲስ አበባ ተሰምቷል ።
በአፋር አዋሽ ፈንታሌ አከባቢ መሬት መንቀጥቀት ይሄን ወር ሁለት ቀን ሶስት ቀን መሃል እየተከሰተ ይገኛል፣ በአዲስ አበባ እና በሌሎች አከባቢ ንዝረቱ የዛሬን ጨምሮ ለሶስተኛ ግዜ መከሰቱ ነው።
ይህ በተደጋጋሚ እየተከሰተ የሚገኘው የመሬት መንቀጥቀጥ መነሻ የሆነው አዋሽ ፈንታሌ አከባቢ ክስተቱ ለወደፊት ለአከባቢ ማህበረሰብ አስጊ ስለሆነ ከፍተኛ የሆነ ጥናት እና የሚዲያ ሽፋን ከዚያም አልፎ ለማህበረሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ሊሰራ ይገባል፣ እየተሰራን ከሆነ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።
ሁላችንንም አላህ ይጠብቀን ፤ አሏህ ይታረቀን 😥
አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ በወቅታዊ የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች ዙሪያ መግለጫ እየሰጡ ነው
👉 “ከአምስት ቀን በኋላ እለቃለሁ…”
👉 “እኔ ከማንም በላይ እጎዳለሁ ስሜቱ በጣም ከባድ ነው…”
| የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከጊኒ ጋር ያደረጋቸውን ሁለት ጨዋታዎች ሰባት ጎል ተቆጥሮበት ሽንፈት በማስተናገድ ወደ አፍሪካ ዋንጫ የማለፍ ዕድሉን አመንምኖ መመለሱ ይታወሳል።
በፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ አሰልጣኙ ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ ከተነሳላቸው ጥያቄዎች መካከል እንደ አንድ ግለሰብ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እየተመዘገበ ባለው ውጤት በግልህ ኢትዮጵያ ስትሸነፍ ምን ይሰማሀል? ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ ሲመልሱ
“ኢትዮጵያ ስትሸነፍ ከእናተ የተለየ ስሜት አይኖረኝም። ከአንተ በላይ ነው የምቆረቆረው። እኔ ተዋናይ ስለሆንኩ እናንተ ተዋንያን ላትሆኑ ትችላላችሁ እኔ ደግሞ ከማንም በላይ እጎዳለው ስሜቱ በጣም ከባድ ነው። የምንችለውን ያህል ነው ጥረት የምናደርገው። አሁን መታወቅ ያለበት ተጨባጭ አቅማችንን ማወቅ አለብን።
አንዳንድ ጊዜ ስሜታዊ መሆን አያስፈልግም። ከጊኒ ጋ ተጨባጭ የአቅም ልዩነት አለን እንደ ቡድን ጠንካራ ሀገር ነው። በተቻለ መጠን ያለውን ልዩነት አጥብበን ተፎካክረን ለመውጣት ጥረት አድርገናል። ያም ቢሆን የፍጥነት ልዩነት ይጎላል።
በተለይ የመከላከሉ ላይ እና ኳስ ስናጣ የምናደርገው እንቅስቃሴ የለም። የምንጫወተው ኳስ ስናገኝ ብቻ ነው። ይህ በጣም መታረም ያለበት ሥራ የሚፈልግ ነገር ነው።”
በቀጣይ ከብሔራዊ ቡድን ጋር የሚኖራቸውን ቆይታ አስመልክቶ ሲናገሩ “ከአምስት ቀን በኋላ እለቃለሁ ውሉ በሃያ ሦስት ነው የሚያልቀው ምን እንደሚያስጨንቃችሁ አላውቅም። ውሉ ሲጠናቀቅ እለቃለሁ በማለት ተናግረዋል።”
Soccer Ethiopia
ዳንኤል መስፍን
01/06/2024
እንዳ አብነ አረጋዊ ዳሞ 2012
01/06/2024
2012 mimoris hawelti semaetat