15/10/2025
!!
የአዊ ዞን እግር ኳስ ዳኞችና ታዛቢዎች ማህበር በፌዴራል ረዳት ዳኛ ደረጄ አመራ ህልፈት የተሰማውን እጅግ ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰብ፣ ለወዳጅ ዘመድ እና ለእግር ኳስ ቤተሰብ መፅናናትን ይመኛል።
Awi football Referees and Commissioners Association is established in 2018, at Addis Kidame town.
15/10/2025
!!
የአዊ ዞን እግር ኳስ ዳኞችና ታዛቢዎች ማህበር በፌዴራል ረዳት ዳኛ ደረጄ አመራ ህልፈት የተሰማውን እጅግ ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰብ፣ ለወዳጅ ዘመድ እና ለእግር ኳስ ቤተሰብ መፅናናትን ይመኛል።
ለአዲስ የፌደራል የጨዋታ አመራሮች
⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️
በተለያዬ ጊዜ የፌደራል ዳኝነት ስልጠና ወስዳችሁ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስር የሚካሄዱ ውድድሮችን መምራት ያልጀመራችሁ በመላ ሀገሪቱ የምትገኙ አዲስ የፌደራል ደረጃ የጨዋታ አመራሮች የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ብቻ:-
✍የፌደራል ዳኝነት ስልጠና ወስዳችሁ ሰርተፍኬት ያላችሁ
✍ዕድሜ ከ35 ዓመት በታች የሆናችሁ ብቻ
✍በየአካባቢያችሁ ጨዋታ እየመራችሁ ያላችሁ
✍የተስተካከለ የሰውነት አቋም ያላችሁ
የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ መልምሎ ወደ ስራ ማስገባት ይፈልጋል በመሆኑም የአካል ብቃት ፈተና የሚሰጠው እና ምልመላ የሚደረገው ሐሙስ በ03/04/2017 ዓ/ም በመሆኑ ከጠዋቱ በ12፡00 ጀምሮ በአበበ ቢቂላ ስታድየም የጤና የምርመራ ውጤት እና የ8ኛ ክፍል ካርድ ይዛችሁ በመምጣት የጤና ምርመራ ውጤቱን ለጤና ባለሙያዎች ማረጋገጥ እና በዚያው ቀን 2፡00 ጀምሮ የአካል ብቃት ፈተና በመውሰድ በዚሁ ቀን እንደ አስፈላጊነቱ አካል ብቃት ፈተናውን ያለፋችሁ ብቻ ተግባራዊ ዳኝነታችሁን ለመመዘን እዛው አበበ ቢቂላ ከተጨዋች ጋር በባለሙያዎች ልትገመገሙ ስለሚችል ዝግጅት አድርጋችሁ እንድትመጡ ከወዲሁ እናሳውቃለን።
ማሳሰቢያ
#ከዚህ በፊት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሚያወዳድራቸውን ውድድሮች ስትመሩ የነበረ የጨዋታ አመራሮችን የማናስተናግድ መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።
#ለምልመላ ስትመጡ ሙሉ ወጭአችሁን በራሳችሁ የምትሸፍኑ መሆኑን እናሳስባለን።
#ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት በሙሉ የማታሟሉትን የማናስተናግድ ስለሆነ ይህን አውቃችሁ ከአላስፈላጊ የገንዘብ ኪሳራ ራሳችሁን እንድትጠብቁ እናሳስባለን።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
“አለምአቀፍ ተወዳዳሪነት ያላቸው የዳኝነት ባለሙያዎች ለመፍጠር እንሰራለን”
20/07/2024
የሐዘን መግለጫ
በአዊ ብሔ/አስ/ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ የስራ ባልደረባ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ወ/ሮ አልማዝ መሸሻ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሀምሌ 13 /2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
የቀብር ሥነ-ሥርዓታቸውም ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በእንጅባራ ከተማ በባሁንክ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ-ክርስቲያን ሀምሌ 14/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡00 ሠዓት ይፈፀማል ።
የአዊ ብሔ/አስ/ እግር ኳስ ዳኞችና ታዛቢዎች ማህበር አባላት በወ/ሮ አልማዝ መሸሻ ህልፈተ ህይወት የተሠማንን ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን እንመኛለን ፡፡
የእህታችንን ነፍስ እግዚአብሔር በአፀደ ገነት ያሳርፍልን!!
07/06/2023
29/05/2023
ቲሊሊ ከተማ ወደ ኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ማለፉን አረጋገጠ። መልካም ዕድል!!
27/05/2023