Sidaama Bunna FC

Sidaama Bunna FC

Share

ይህ የሲዳማ ቡና እ/ኳስ ክለብ ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ ነው።

Photos from Sidaama Buna Football Club / ሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ's post 27/08/2026
06/08/2026

"ለሲዳማ ቡና እሮጣለሁ" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀዉ ታላቁ የጎዳና ላይ ሩጫ ቀን መራዘሙን እናሳዉቃለን

​ክለባችን ሲዳማ ቡና የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ አህጉራዊ ውድድር ላይ ሀገራችንን ወክሎ የሚሳተፍ በመሆኑ ለውድድሩ የሚደረገው ጥብቅ የቅድመ-ዝግጅት ፕሮግራም እና የጊዜ መጣበብ በመፈጠሩ ምክንያት ነሐሴ 2/2018 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው "ለሲዳማ ቡና እሮጣለሁ" ታላቁ የጎዳና ላይ ሩጫ ወደ ሌላ አመቺ ቀን መራዘሙን እናሳውቃለን።

​ይህ ውሳኔ ክለባችን ለአህጉራዊው መድረክ የሚያደርገውን ዝግጅት ለማጠናከር እንዲሁም የሩጫውን መርሃ-ግብር ቡድናችን ከሚያደርገዉ ታሪካዊዉ የአፍሪካ መድረክ ጉዞ የሽኝት መርሐግብር ጋር በማጣጣም በላቀ ድምቀት ለማካሄድ ታስቦ የተደረገ ነው።

​በመሆኑም በሐዋሳ ከተማና በተለያዩ አካባቢዎች የምትገኙ ደጋፊዎቻችን ከዚህ ቀደም በተገለጹት ይፋዊ አድራሻዎች የመሮጫ ቲሸርቶችን አስቀድማችሁ በመግዛት ለሩጫውና ለተጫዋቾቻችን ለሽኝት መርሃ-ግብሩ አስፈላጊውን ቅድመ-ዝግጅት እንድታደርጉ ጥሪያችንን እያቀረብን በየወረዳዎቹ የቲሸርት ማዳረስና ሽያጭ ስራው በተጠናከረ ሁኔታ የሚቀጥል ይሆናል።

​የአዲሱን የሩጫ ቀንና ተያያዥ መረጃዎችን በቅርብ ቀናት የምናሳውቅ ይሆናል።

​የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ፅህፈት ቤት
ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም

04/08/2026
Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Hawassa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Address


Hawassa