14/12/2025
FASIL-fãfér tx
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from FASIL-fãfér tx, Tai Chi Studio, Gondar.
14/12/2025
12/06/2023
ማ ሎሬት ይባላል?
የላቀውን ተግባር የፈጸመ
ማ ፖኤት ሎሬት ይባላል?
አምራች ባለቅኔ! አምራች ገጣሚ!
ሎሬትነትን ማ ይሸልማል?
የጥበብ አፍቃሪው፣ ዕውቅና መስጠትንና ታላቅ ሰውን ማክበርን የተማረውና ባህሉ ያደረገው ህዝብና ማህበር ሎሬትነትን ይሸልማል። (ከጊዜ ኪነጥበባት )
የዓለም ፖኤት ሎሬት ፀጋዬ ገብረ፡መድኅን ሽልማቶች
ይየዓለም ፖኤት ሎሬት ፀጋዬን ብዙ ማምረት በሚችልበት ገና በ69 ዓመት ዕድሜው ነበር፡ የካቲት 18/1998 ያጣነው።
አምራች ፀሃፊው ጸጋዬ ከ32 በላይ ተውኔቶችን፡ አብላጫዎቹንም በግጥምና በቅኔ ጽፏል። የኢትዪጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ፀሀፍት መነሸጫ የሆኑ ስራዎችን ሰርቷል።
የመሞቱ ምክንያትና ዝርዝር ማንነቱን ዩኤስ ኤ ኮንግረንስ ዝርዝር ነጥቦችን በሚያዳምጥበት ጉባኤ ላይ ፤
ሜይ 15/2006 የሜሪይላንዱ ተመራጭ ሰር አሊጃህ ኢ ኩሞንግስ ጸጋዬን በሰፊው የሚተነትን ጽሁፍ አቅርበዋል። ይህንን ጽሁፍ ዊኪፒድያ እንዳለ አቅርቦታል።
ምንም እንኳን ከነፍሱ በላይ የሚያፈቅራት እናት ሀገሩ ባለውለታዋንና ታላቁን ልጇን ስሙን በዜና እወጃ እንኳን ባለመጥራት ና መርዶውን ባለመዘገብ ልስ ብትበላም፤ ዓለም ግን ለያንዳንዱ ስራው ዕውቃና ሰጥቶታል፤ አክብሮታል፤ ታላቅነቱንም መስክሮለታል። (ከዚህ ላይ ስንደርስ ነፍስ ይማር! ብለን እንለፍ)
የ2ኛ ደረጃ ትምህርቱን ከጄነራል ዊንጌት ካጠናቀቀ በኋላ ቺካጎ ከብላክ ስቶን የህግ ትምህርት ቤት በህግ የመጀመርያ ዲግሪውን በ1959 ሊያጠናቅቅ በቅቷል። በዚያው ወደ ለንደንና ፓሪስ በማቅናትም የህይወቱን ጥሪ ትያትርን በ1959 ና በ1960 ከሮያል ኮርት ኮሌጅ ለንደን የጥናታዊ ድራማንና ከፓሪስ ደግሞ የፈረንሳይ ኮሜዲን አጥንቷል።
የፀጋዬ አብዮተኛ ተውኔቶች ድሆችን፣ የተረሱትን፣ ጦርነትን፣ በዝባዥ ሥርዓትን፣ የሰውን ልጅ ሰብዓዊ ስሜቶችንና መነቃቃቶችን የያዙ ለዘመኑ ብርሃን መሆን የቻሉ ዛሬም፡ድረስ ስነጽሁፋዊ ለዛቸው የማይደበዝዙ፣ መልዕክቶቻቸው ዘመን ተሻጋሪ ከሆኑ 32 በላይ ተውኔቶች መካከል 18ቱ ለተመልካች እንዳይቀርቡ፡ በይፋ የተከለከሉ ሲሆን አብዛኞቹም ተዋንያኑ ልምምዳችስውን አጠናቀው፡ ለእይታ ለመቅረብ ጥቂት ቀናት ሲቀሯቸው የታገዱ ናቸው።
ከእንግሊዝኛ ግጥሞቹ፡መካከል ስለረሃብ የጻፈው "The days hunger consumed" የተሰኘው ግጥሙ ርሃብ ስንት ቀን ይፈጃል' ዓይነት ስልቱን የወገናችንን ዕልቂትና የነፍሱን እሪታ ለዓለም አቅርቦበታል።
ከ1954 እስከ 1964 የቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ትያትር ቤት(ብሄራዊ ትያትር) ዳይሬክተር በመሆን እየሰራ ሳለ፤ "Oda oak oracle' በሚል ርዕስ ጽፎ ያዘጋጀውን የፎክሎር ተወኔት በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት፣ በኢንግላንድና በሰሜን አሜሪካን አቅርቦታል።
.......(ይቀጥላል።) FASIL-fãfér tx
12/06/2023
Back In International duty 🔥🌟
12/06/2023
አንጋፋዋ ድምጻዊት ሂሩት በቀለ አረፈች፡፡
⚡️ሕይወት እንደሸክላን ጨምሮ በርካታ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎችን እንካችሁ ያለችው ድምጻዊት ሂሩት በቀለ፣ በአደረባት ህመም በሃገር ውስጥና በውጭ በህክምና ስትረዳ ቆይታ በዛሬው እለት ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም በ80 ዓመቷ ህልፈተ-ሕይወቷ ተሰምቷል፡፡
⚡️ከ1950 መጀመሪያ እስከ 1980ዎቹ መጨረሻ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎችን ያስደመጠችን ሂሩት በቀለ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዘማሪነት/አገልጋይነት ስራዎችን ስትስራ እንደነበር ይታወሳል፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
Gondar
17/06/2023