Dire Dawa Football Federation

Dire Dawa Football Federation

Share

This is Official page of DDFF

Photos from Dire Dawa Football Federation's post 06/07/2026

የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለስፖርቱ ዕድገት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ዕውቅና ሰጠ

​የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ2018 ዓ.ም የከፍተኛ ዲቪዚዮን የውድድር ዘመን ስኬታማነት የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የእውቅናና የምስጋና መርሃ ግብር አካሄደ።

​በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ክቡር ኮሚሽነር አለሙ መግራ፣ የድሬዳዋ እግር ኳስ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ መነቃቃት የታየበት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ኮሚሽነሩ አያይዘውም፣ ወጣቶች ጊዜያቸውን በአልባሌ ቦታዎች ከማሳለፍ ይልቅ ወደ ስፖርት ሜዳዎች በመምጣት አቅማቸውን እንዲያሳድጉ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። ክለቦችም ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣት ተጫዋቾች በመለየትና በስርዓት በማሳደግ የከተማዋን የስፖርት መዋቅር በእጅጉ እያጠናከሩት እንደሚገኝ አንስተዋል።

​ክቡር ኮሚሽነር አለሙ አክለውም፣ ከዛሬ አራት ዓመታት በፊት በአዲስ መልክ የተደራጀው የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ የከተማዋን ስፖርት በማነቃቃት ረገድ ትልቅ አሻራ ማሳረፉን አስታውሰዋል። ለዚህ ስኬት መገኘት ሀብታቸውን፣ እውቀታቸውንና ጉልበታቸውን በሙሉ አቅም ላዋጡ አጋር አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። እነዚህ አካላት ለስፖርቱ ዕድገት ሲሉ ያሳዩት ወኔና የላቀ ትብብር ለወደፊትም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

​በተጨማሪም የፌዴሬሽኑ አመራር፣ ወጣቶች ያላቸውን የእግር ኳስ ጥበብ እና ተሰጥኦ በአግባቡ እንዲያሳዩ በማድረግ ረገድ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ስራዎች ውጤታማ እንደነበሩ ገልጸው፣ ወጣቶችን ከጎጂ ድርጊቶች በመጠበቅ በስፖርቱ እንዲታቀፉ የተጀመረው የተቀናጀ ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

​ፌዴሬሽኑ በተለይ በተለያዩ ደረጃዎች የአሰልጣኞችን አቅም ግንባታ ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት፣ በተከታታይ ዙር የሰለጠኑ አሰልጣኞችን ለከተማው እግር ኳስ ማበርከቱን የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ ይህ የተጀመረው የክህሎት ማሳደግ ተግባር አሁንም በስፋት እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

​በመጨረሻም፣ ይህ የእውቅና መርሃ ግብር የተዘጋጀው ፌዴሬሽኑን ከጅምሩ ጎን በመሆን የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርጉ የነበሩ ግለሰቦችና ተቋማት ያደረጉትን በጎ አስተዋጽኦ ለመዘከር እና አርአያነታቸውን ለማጉላት መሆኑን ተገልጿል። በዕለቱም ለተለያዩ አካላት የምስጋና የምስክር ወረቀትና እውቅና ተሰጥቷል።

05/07/2026
Photos from Dire Tv - አማርኛ's post 25/06/2026
Photos from Dire Dawa Football Federation's post 11/06/2026

የድሬዳዋ እግር ኳስ የላቀ ብቃት ለማምጣት የካፍ ዲ ላይሰንስ (CAF D License) የአሰልጣኞች ስልጠና ተጀመረ።

የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመቀናጀት፣ የአካባቢውን እግር ኳስ በዘመናዊ እውቀት ለመገንባት የሚያስችል የካፍ ዲ ላይሰንስ (CAF D License) የአሰልጣኞች ስልጠና በድሬዳዋ ከተማ በይፋ መጀመሩ ተገለጸ።

​በስልጠናው ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ የተገኙት የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ እና የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ክቡር ኮሚሽነር አለሙ መግራ፣ የድሬዳዋን እግር ኳስ እድገት ይበልጥ ለማሳደግ የአሰልጣኞችን ሙያዊ ብቃት እና የዘመናዊ ስልጠና ክህሎት በአለም አቀፍ ደረጃ ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

​ፕሬዚዳንቱ አክለውም እግር ኳሱን ወደ ተፈለገው ከፍታ ለማድረስ፣ አሰልጣኞችን በተለያዩ ሳይንሳዊ እና ተግባራዊ ስልጠናዎች ብቁ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፣ ይህ ጥረት ተጫዋቾችን በመቅረጽ እና የክለቦችን አቅም በመገንባት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ጠቁመዋል።

​ይህ ስልጠና ለሁለተኛ ጊዜ በድሬዳዋ ከተማ እየተሰጠ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በዚህ ዙር 30 አሰልጣኞች በንድፈ-ሀሳብ እና በተግባር የታጀበ ስልጠና በመከታተል ላይ ይገኛሉ።

ከስልጠናው ተሳታፊዎቹ የሚጠበቀውን የቴክኒክ አቅም በማጎልበት፣ በክለቦች ውስጥ የኳስ ፍልስፍናን እና የዲሲፕሊን አሰራርን ለማሻሻል ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

​የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በየደረጃው ያሉ አሰልጣኞችን ብቃት ለማሻሻል የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም በስልጠናው መክፈቻ ላይ ተገልጿል።

በዚህ የስልጠና መክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ የድሬዳዋ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የውድድር እና ስነ-ስርአት ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ኤርሚያስ ሀይሉ እና ቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ የማነ ዘገየም ተገኝተዋል ።

ሪፖርተር


ካሜራ

Photos from Dire Dawa Football Federation's post 08/06/2026

በድሬዳዋ የእግርኳስ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከተመልካች በተገኘ ገቢ ለክለቦች የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ

የድሬዳዋ እግርኳስ ፌዴሬሽን በከፍተኛ ዲቪዚዮን እየተወዳደሩ ለሚገኙ ክለቦች የገንዘብ ድጋፍ አበረከተ።

በዕለቱ የድጋፍ መርሃ-ግብር ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ እና የእግርኳስ ፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ክቡር ኮሚሽነር አለሙ መግራ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግብዓት የሚሆኑ የድሬዳዋ ልጆችን በማፍራት ብሔራዊ ቡድኑን ለማጠናከር ፌዴሬሽኑ እንደሚተጋ ተናግረው ከተለያዩ ክልሎች መጥተው የሚወዳደሩ ተጫዋቾች መኖራቸው ድሬዳዋ "ትንሿ ኢትዮጵያ" ለመሆኗ ማሳያ ነው ብለዋል።

የድሬዳዋ ወጣት በፍቅር ከተያያዘ የሚሉትን የሚሰማ የሚታዘዝ ቅንና ፍቅር ወዳድ መሆኑን በዲቪዚዮን ውድድሮች ላይ መመልከት ተችሏል ሲሉም አስታውቀዋል ።

ዛሬ የመጀመሪያችን የሆነው የገንዘብ መጠን ትንሽ ቢሆንም፣ ሐሳቡ ግን ትልቅ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል ያሉት ኮሚሽነሩ ፌዴሬሽኑ አሠራርን በመዘርጋት በድሬዳዋ እግር ኳስ ዕድገት ላይ ጠያቂ ትውልድ ለመፍጠር አልሟል ብለዋል።

​በመድረኩ ላይ የተገኙት የሁሉም ዲቪዚዮን ክለቦች አመራሮች፣ ድጋፉ ከተመልካች ገቢ መገኘቱ እጅግ ታሪካዊ እና የፌዴሬሽኑን አዲስ የአስተሳሰብ ለውጥ የሚያሳይ በመሆኑ የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ገልጸዋል።

​አመራሮቹ በንግግራቸውም ይህ በድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተተገበረ አርአያነት ያለው ተግባር ነው፣ በድሬዳዋ የታየው አዲሱ የእግር ኳስ መነቃቃትና ተነሳሽነት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፤ ለዚህም ሁሉን አቀፍ ድጋፍና ትብብር ያስፈልገዋል በማለት የጋራ ስሜታቸውን አንጸባርቀዋል።

በዚሁ የድጋፍ አሰጣጥ መርሃ-ግብር ላይ ክቡር ኮሚሽነር አለሙ መግራ የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትና የፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ፣ ዶክተር ዳኛቸው ንገሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት፣ የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ አመራሮች
ሌሎች የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የሁሉም ዲቪዚዮን ክለቦች አመራሮች ተገኝተዋል ።

በመድረኩ ላይ በስፋት ውይይት ተደርጎ ሐሳብና አስተያየቶች የተለዋወጡ ሲሆን፣ በቀጣይ ሥራዎች ላይ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ መርሃ-ግብሩ በስኬት ተጠናቋል።

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Dire Dawa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Address


Dire Dawa