01/09/2026
ሀገሬስ ገንፎ ናት
በስልጣን ማንኪያቸው የሚቆራርሷት
ቂቤ ወሬያቸውን በርበሬ ስራቸው
ጨመር አርገውባት
እሷ ያዝኩት ስትል
የስጧትን ሁሉ አጣቅሰው አላውሰው
በዛ ስልጣን ማንኪያ በህብረት አብረው
ያውም ክብ ሰርተው
እንደ ጉድ ሚበሏት የሚጎራረሷት
ሀገሬ ለእነርሱ ገንፎ ብቻ እኮ ናት
ሀገሬስ ገንፎ ናት
በስልጣን ማንኪያቸው የሚቆራርሷት
26/08/2026
?
*****
በኢትዮጵያ ሕግ መሬት የመንግሥት ነው ወይም መሬት የሕዝብ ነው ብሎ ብቻ መመለስ በቂ አይደለም። ሕገ-መንግሥቱ መሬትን ከባለቤትነት እና ከየመሬት ጥቅም/ይዞታ መብት በመለየት ያደራጃል።
1. የመሬት ባለቤትነት
የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 40(3) በግልጽ ሁኔታ የመሬት ባለቤትነት በመንግሥትና በሕዝቦች ብቻ የተሰጠ ነው።
በሌላ አነጋገር መሬት በግል ሰው እንደ ተንቀሳቃሽ ንብረት የግል ባለቤትነት ሊያዝበት አይችልም።ስለዚህ መልሱ፦ መሬት በሕገ-መንግሥቱ መሠረት የመንግሥትና የሕዝቦች ንብረት ነው።
2. የግለሰብ መብት ምንድነው?
ይህ ግን አንድ ግለሰብ በመሬት ላይ ምንም መብት የለውም ማለት አይደለም።የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 40(4) እና 40(5) የመሬት አጠቃቀምና ይዞታ መብቶችን ይጠብቃሉ።በተለይ ገበሬዎች በመሬት ላይ የማልማት፣ የመጠቀምና በሕግ የተፈቀደላቸውን የይዞታ መብት የመጠቀም መብት አላቸው።
ስለዚህ ባለቤትነት ማለት ይዞታ የመጠቀም መብት ነው።አንድ ሰው የመሬቱ የግል ባለቤት ባይሆንም በመሬቱ ላይ ጠንካራ ሕጋዊ የይዞታና የአጠቃቀም መብት ሊኖረው ይችላል።
3. መንግሥት የመሬት ባለቤት መሆኑ ምን ማለት ነው?
መንግሥት የመሬት ባለቤት ነው ሲባል መንግሥት እንደ አንድ ግለሰብ መሬቱን በፈለገው መንገድ ይሸጣል ወይም ይወስዳል ማለት አይደለም።የመሬት አስተዳደር ሥልጣን በሕግ የተገደበ ነው። የግለሰቦችን የይዞታ፣ የአጠቃቀምና በመሬቱ ላይ የተገነቡ ንብረቶችን መብቶች ሕጋዊ ሥርዓት ሳይከተል መጣስ አይቻልም።
4. የመሬት ይዞታ መብት ለምን አስፈላጊ ነው?
የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 40(7) በመሬት ላይ በሕጋዊ መንገድ የተገነቡ ሕንፃዎች፣ ሰብሎች እና ሌሎች በመሬቱ ላይ የተደረጉ ጥረቶች የንብረት መብት ጥበቃ እንዳላቸው ያረጋግጣል።ይህ ማለት መሬቱ በራሱ የግል ባለቤትነት ባይሆንም በመሬቱ ላይ ያለው ሕንፃ፣ ሰብል ወይም ሌላ ሕጋዊ ንብረት የተለየ የንብረት መብት ሊኖረው ይችላል።
5. መሬት ሊሸጥ ይችላል?
በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 40(3) መሠረት መሬት እንደ የግል ንብረት ተወስዶ መሸጥ፣ መያዝ ወይም ማውረስ አይቻልም።ነገር ግን በመሬት ላይ ያለ ሕጋዊ የይዞታ ወይም የአጠቃቀም መብት በሕግ በተፈቀደ መንገድ ሊተላለፍ ይችላል።ይህንን ልዩነት አለመገንዘብ ብዙ የመሬት ውዝግቦችን ያመጣል።
6. መንግሥት መሬትን ለሕዝብ ሊያስረክብ ይችላል?
አዎ መሬት በመንግሥትና በሕዝቦች ባለቤትነት ሥር ቢሆንም፣ ሕጉ በሚያስቀምጠው ሥርዓት መሠረት ለግለሰቦች የይዞታና የአጠቃቀም መብት ሊሰጥ ይችላል።
#ለምሳሌ፦ አንድ ገበሬ የእርሻ መሬት ይዞ ሊያርስ ይችላል።አንድ ሰው በሕግ በተፈቀደለት የከተማ መሬት ይዞታ ላይ ቤት ሊገነባ ይችላል።የይዞታ መብቱ በሕግ በተፈቀደ መጠን ሊተላለፍ ይችላል።
7. መንግሥት የሰውን የመሬት ይዞታ መብት ሊያስወግድ ይችላል?
➲አዎ ነገር ግን በሕግ የተደነገገውን ሂደት በመከተል ብቻ ነው።
የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 40(8) መሬት ለሕዝብ ጥቅም ሲፈለግ በሕግ መሠረት የመሬት ይዞታን መንጠቅ እንደሚቻል እና በሚያስፈልገው ጊዜ ተገቢ ካሳ መክፈል እንዳለበት ያስቀምጣል።
ስለዚህ መሬቱ የመንግሥት ነው ስለዚህ መንግሥት ያለ ሕጋዊ ሂደት ሊወስደው ይችላል የሚለው አመለካከት ትክክል አይደለም።
#ምሳሌ፦ አቶ አበበ በሕጋዊ መንገድ የእርሻ መሬት ይዞ ለ20 ዓመታት እያረሰ ነው።መሬቱ በሕገ-መንግሥቱ መሠረት የግለሰቡ የግል ባለቤትነት ባይሆንም አቶ አበበ በመሬቱ ላይ ሕጋዊ የይዞታና የአጠቃቀም መብት አለው።
ከዚያም መንግሥት አካባቢውን ለሕዝብ ጥቅም ለሚውል ፕሮጀክ
13/08/2026
ሚዛኑ ቢያደላ፤ ጊዜ ሆኖ ዳኛ
ቋንቋ ቀለም ሆነ፤ የሰው መመዘኛ።
ትገል እደው ግደል፤ ታድን እንደው አድን
ጠባሳ አይዝም፤ መርቅዞ የሚድን።
ብዬ ባዜምበት ....
ይፈትለው ጀመረ ቃል አጠቃቀሜን
ምንሽር አንስቼ ላላሳየው አቅሜን
ማንስ ገሎ ዳነ ማን ሞቶ ተረሳ ?
ፍጻሜው ሰይፍ ነው፤ ሰይፍ ለሚያነሳ።
***
ስለዚህ፤ ትርጉሙን
"ሀገር" ማለት ብባል?
"ሀገር" ማለት "ሰው ነው" አልልም ደፍሬ።
ሀገር የሚሆን ሰው፤ አታለች ሀገሬ።
By
10/08/2026
በራያ አላማጣ የድሮን ጥቃት ተፈጸመ‼
በራያ አላማጣ መረዋ በተባለ ት/ቤት ዛሬ ነሐሴ 4 ቀን ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት የድሮን ጥቃት መፈጸሙ ታውቋል።
📌 የህውሃት ታጣቂዎች ትናንት ምሽት ለየክፍላቸው የጦር መሳሪያ ክፍፍል አድርገው ዛሬ ከመረዋ ት/ቤት ጭነው ለመውሰድ በዝግጅት ላይ እንዳሉ ጥቃቱ መፈፀሙ ተነግሯል።
በታጣቂዎቹ ላይ ጉዳት መድረሱ እና ወደ አላማጣ ሆስፒታል ተሽከርካሪዎች ሲመላለሱ ነበር ተብሏል።በአካባቢው ከፍተኛ የጦርነት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የሚያመለክቱ ተደጋጋሚ መረጃዎች እየወጡነው።ምስሉ AI ነው።
09/06/2026
የ2026 የአለም ዋንጫ ጨዋታዎች የት ይከናወናሉ?
ውድድሮች የሚካሄዱባቸው 16ቱ ሜዳዎች በሰኔ ወር ይፋ ሆነዋል። ሁሉም ስታዲየሞች ተገንብተው ተዘጋጅተዋል። አብዛኛዎቹ ትልቅ አቅም ያላቸው ስታዲየሞች ያሉት በአሜሪካ ሲሆን፣ የኤን ኤፍ ኤል ቡድኖች የሚጠቀሙባቸው ናቸው።
አንዳንድ ስታዲየሞች ከ2026 በፊት ማሻሻያ ይደረግባቸዋል። አንዳንዶቹ ደግሞ ሰው ሠራሽ ሣር በፊፋ የማይፈቀድ በመሆኑ ተፈጥሯዊ ሳር ማንጠፍ ይጠበቅባቸዋል።
አሁን ባለው ሁኔታ በ2026ቱ ውድድር 80 ግጥሚያዎች ይኖራሉ። ይህም ግን ሊቀየር ይችላል። ዩናይትድ ስቴትስ ከሩብ ፍፃሜው ጀምሮ ያሉትን ጨዋታዎች ጨምሮ 60 ግጥሚያዎችን ታስተናግዳለች። ጎረቤት ካናዳ እና ሜክሲኮ እያንዳንዳቸው 10 ግጥሚያዎችን ያስተናግዳሉ።
ዩናይትድ ስቴትስ እና ሜክሲኮ ከዚህ ቀደም የዓለም ዋንጫን አስተናግደዋል። አብዛኛዎቹ ስታዲየሞች የ2026ዱን አያስተናግዱም። አሜሪካ በ1994 የተጠቀመቻቸውን ስታዲየሞች በድጋሚ አታስተናግድባቸውም።
ሜክሲኮ ግን በ1970 እና 1986 ጨዋታዎችን ያስተናገደውን በሜክሲኮ ሲቲ የሚገኘውን ታዋቂው ኢስታዲዮ አዝቴካ ለሦስተኛ ጊዜ ትጠቀማለች።የ2026 ጨዋታዎች የት ይከናወናሉ?
ውድድሮች የሚካሄዱባቸው 16ቱ ሜዳዎች በሰኔ ወር ይፋ ሆነዋል። ሁሉም ስታዲየሞች ተገንብተው ተዘጋጅተዋል። አብዛኛዎቹ ትልቅ አቅም ያላቸው ስታዲየሞች ያሉት በአሜሪካ ሲሆን፣ የኤን ኤፍ ኤል ቡድኖች የሚጠቀሙባቸው ናቸው።
አንዳንድ ስታዲየሞች ከ2026 በፊት ማሻሻያ ይደረግባቸዋል። አንዳንዶቹ ደግሞ ሰው ሠራሽ ሣር በፊፋ የማይፈቀድ በመሆኑ ተፈጥሯዊ ሳር ማንጠፍ ይጠበቅባቸዋል።
አሁን ባለው ሁኔታ በ2026ቱ ውድድር 80 ግጥሚያዎች ይኖራሉ። ይህም ግን ሊቀየር ይችላል። ዩናይትድ ስቴትስ ከሩብ ፍፃሜው ጀምሮ ያሉትን ጨዋታዎች ጨምሮ 60 ግጥሚያዎችን ታስተናግዳለች። ጎረቤት ካናዳ እና ሜክሲኮ እያንዳንዳቸው 10 ግጥሚያዎችን ያስተናግዳሉ።
ዩናይትድ ስቴትስ እና ሜክሲኮ ከዚህ ቀደም የዓለም ዋንጫን አስተናግደዋል። አብዛኛዎቹ ስታዲየሞች የ2026ዱን አያስተናግዱም። አሜሪካ በ1994 የተጠቀመቻቸውን ስታዲየሞች በድጋሚ አታስተናግድባቸውም።
ሜክሲኮ ግን በ1970 እና 1986 ጨዋታዎችን ያስተናገደውን በሜክሲኮ ሲቲ የሚገኘውን ታዋቂው ኢስታዲዮ አዝቴካ ለሦስተኛ ጊዜ ትጠቀማለች።
27/05/2026
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ቤተሰቦቻችን በሙሉ
እንኳን 1447 ለ ኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ !
✨ ኢድ ሙባረክ! ✨
22/05/2026
ባህር ዳር‼
የባሕር ዳር አየር ማረፊያ አዲስ ተርሚናል አገልግሎት ሊጀምር ነው‼
ከ40 ሚሊየን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አዲስ ተርሚናል በቅርቡ ሥራ ሊጀምር እንደሆነ ተነግሯል።
በቻይናው ሲኖሃይድሮ ኮርፖሬሽን የተገነባው ይህ ዘመናዊ ተርሚናል፣ ቀደም ሲል በግጭት ከደረሰበት ጉዳት አገግሞ ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ መጠናቀቁ ተጠቁሟል።
አዲሱ ተርሚናል የባሕር ዳር ከተማን የቱሪዝም መዳረሻዎች እና የስፖርት ውድድሮች በማስተናገድ ለአካባቢው ኢኮኖሚና ለህዝብ አገልግሎት ትልቅ ድርሻ እንደሚኖረው ይጠበቃል።