31/08/2026
🔴 ከቁጭት ወደ ተስፋ: የኢትዮጵያ ዳኝነት አዲስ መንገድ
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ዳኝነት ውስጥ አዲስ ምዕራፍ እየተጻፈ ይገኛል። ለዓመታት በዳኞች ምልመላ፣ ልማትና እድገት ሥርዓት ላይ የታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከመሠረት (grass root) የጀመረ ስትራቴጂያዊ ለውጥ ተግባራዊ እያደረገ ነው።
የዚህ ትልቅ የለውጥ ጉዞ መነሻ እ.ኤ.አ በ2022 ዩጋንዳ ላይ በተካሄደው የሴካፋ የትምህርት ቤቶች ውድድር ወቅት የተከሰተ አጋጣሚ ነበር። በወቅቱ በስፍራው የነበሩት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ኢትዮጵያ ለውድድሩ የላከቻቸው የፕሪምየር ሊግ ደረጃ ዳኞችን እንደነበር ተመለከቱ። ይህ አጋጣሚ ትልቅ ቁጭት በመፍጠሩ ተተኪዎች ላይ ተግባራዊ ሥራዎች እንዲሰሩ አሳሰቡ።
የብሔራዊ የዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሸዋንግዛው ተባባል ይህን አጋጣሚ ሲያስታውሱ "ያ አጋጣሚ ለዛሬ ሥራችን መነሻ ሆኗል። የተተኪ ዳኞችን ልማት በስትራቴጂ መምራት እንዳለብን ያሳየን ነው" ይላሉ።
የዳኞች ኮሚቴው በአዲስ መልክ ከተደራጀ በኋላ አዲስ ስትራቴጂክ ፕላን ተቀርፆ የዳኛ ምንጮች ትምህርት ቤቶችና ወጣቶች እንዲሆኑ ሰፊ እንቅስቃሴ ተጀመረ። "ቀደም ሲል በታችኛው እርከን ላይ በሚያጫውቱ ዳኞች እና በፕሪሚየር ሊጉ ዳኞች መካከል የተመጣጠነ የዕድሜ ስብጥር አለመኖር ለዳኝነት ማኔጅመንቱ አስቸጋሪ ፈተና ሆኖ ቆይቷል።" ያሉት የዳኞች ዲፓርትመንት ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ምስጋናው ይህንን ችግር ለመቅረፍ አዲስ የዳኝነት ሙያ መመርያ እንዲዘጋጅ መደረጉን ይገልፃሉ። መመርያው አዲስ ወደ ዳኝነት ሙያ የሚገቡ ግለሰቦች ዕድሜያቸው ከ13 እስከ 22 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ብቻ እንዲሆን የሚያደርግ ሲሆን በፌዴሬሽኑ ዝርዝር መስፈርት መሠረት ወደ መረጃ ቋት ገብተው ከሥልጠና ጀምሮ በቅርብ ክትትልና እገዛ ወደ ላይ የሚያድጉበት መስመር እነዲዘረጋ ተደርጓል።
እንደ አዲስ ፖሊሲ ከተቀመጡት ዋና ዋና አቅጣጫዎች መካከል የፌዴሬሽኑ የዕድሜ ውድድሮች በዕድሜ አቻ ወጣት ዳኞች እንዲመሩ ማድረግ መሆኑን አቶ ሸዋንግዛው ይናገራሉ። "ዕድሜያቸው ከ17 ዓመት በታች ባሉ ወጣት ዳኞች ከ15 ዓመት በታች ውድድሮችን ይመራሉ። ከ17 ዓመት በታች ውድድሮችንም ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ወይም በዛ የእድሜ አካባቢ ባሉ ዳኞች ይዳኛሉ። ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የትምህርት ቤት ውድድሮች በተማሪ ዳኞች፣ የዩኒቨርሲቲ ውድድሮች ደግሞ በራሳቸው በዩኒቨርሲቲ ተማሪ ዳኞች እንዲከናወኑ ይደረጋል።"
በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሻምፒዮና የዚሁ አዲስ ፖሊሲ ፍሬ ማሳያ ሆኗል። በውድድሩ ላይ የሚገኙት የጨዋታ አመራሮች ሙሉ በሙሉ በዚህ አዲስ የምልመላ መስፈርት ከተለያዩ አካባቢዎች የተመረጡ ታዳጊ ዳኞች ናቸው። ታዳጊዎቹ የጨዋታ አመራሮች እያሳዩ የሚገኙት የአመራርነት ብቃትም ከፍተኛ ተስፋ የሰጠ ሆኗል።
ዛሬ የተካሄዱ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ላይ በአዳማ አበበ ቢቂላ በአካል ተገኝተው የታዳጊ ዳኞቹን እንቅስቅሴ የተመለከቱት የሴካፋ የዳኞች ኃላፊ ዓሊ አህመድ እና የፊፋ ኢንስትራክተር ሁሴን ጋቦኒ ለተጀመሩት ሥራዎች ያላቸውን ከፍተኛ አድናቆት ገልጸዋል። የሴካፋ የዳኞች ኃላፊ ዓሊ አህመድ በቦታው ተገኝተው ከተመለከቱ በኋላ "ዛሬ እዚህ በመገኘታችን በጣም ደስተኞች ነን። ይህ በእውነት ለኢትዮጵያ ዳኝነት በጣም ጥሩ ተስፋ ያለው ነው። ይህን በመመልከታችን ትልቅ ደስታን ሰጥቶናል። መሰል ፕሮጀክቶች ሁልጊዜ ልናያቸውና ልንደግፋቸው የምንፈልጋቸው ናቸው። ዳኞችን ሁልጊዜ ከመሰረቱ መገንባት አለብን" ብለዋል።
የዚህ አዲስ አቅጣጫ ውጤታማነት ቀስ በቀስ እየጎላ መጥቷል። ቀደም ሲል በሴካፋ የትምህርት ቤት ውድድሮች ላይ የተላኩ ታዳጊ ዳኞች ዛሬ ላይ የፊፋ ኤሊት የጨዋታ አመራሮች ስልጠና ደረጃ እስከ መድረስ ችለዋል። ወጣቷ ረዳት ዳኛ ሀና ደመቀ በአንድ ዓመት ውስጥ የሴካፋ ትምህርት ቤቶች ውድድርን ከመምራት ተነስታ በዛሬው ዕለት በተጠናቀቀው የፊፋ ኤሊት የጨዋታ አመራሮች ስልጠና ላይ መካፈሏ የፕሮጀክቱን ትርጉም በሚገባ የሚያሳይ ሆኗል።
አቶ ሸዋንግዛው ተባባል በአዳማ ከ17 ዓመት በታች ውድድር ላይ እያጫወቱ ካሉ ወጣት ዳኞች መካከል የአንድ ወንድና አንድ የሴት ዳኛ በቀጣይ ለሚደረገው የሴካፋ የትምህርት ቤቶች ውድድር መላኩን ገልጸዋል። ፌዴሬሽኑ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የጀመራቸውን የስልጠና እንቅስቃሴዎች በመከተል ሌሎች ከተሞች እና ክልሎች በተመሳሳይ መልኩ ተቀብለው እንዲተገብሩት ጥሪ አቅርበዋል።
ከቁጭት ተነስቶ በስትራቴጂ ታገዞ አዲስ ጉዞ እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ዳኝነት ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚወክሉ ብቁ፣ በእድሜ ለጋ እና በስነ-ምግባር የታነጹ ዳኞችን ለማፍራት ትልቅ መሰረት ጥሏል።
Ethiopian Football Federation
Amhara Football Referees
💥
✍️ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት እና ይቀላቀሉ።
✅ Telegram
https://t.me/Amhara21FootballReferees
✅ page
https://www.facebook.com/AmharaFootballReferees/
💥 Like 🔵 Share 🔴 Follow
30/08/2026
🔴 በባህርዳር ከተማ አስተዳደር እግር ኳስ ፌደሬሽን አስተባባሪነት የ "D License " የአሰልጣኞች ስልጠና ከሰኞ ነሀሴ 25/2018 ዓ/ም ጀምሮ ይሰጣል።
በመሆኑም ከታች ስማችሁ የተዘረዘረ ሰልጣኞች በዕለቱ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ በመገኘት ስልጠናውን እንድትወስዱ ፌደሬሽኑ አሳውቋል።
Amhara Football Referees
💥
✍️ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት እና ይቀላቀሉ።
✅ Telegram
https://t.me/Amhara21FootballReferees
✅ page
https://www.facebook.com/AmharaFootballReferees/
💥 Like 🔵 Share 🔴 Follow
29/08/2026
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከፊፋ ጋር በመተባበር እየተካሄደ የሚገኘው የፊፋ ኤሊት የጨዋታ አመራሮች ስልጠና በንድፈ ሐሳብ እና በተግባር እየተሰጠ አራተኛ ቀኑን አስቆጥሯል።
ስልጠናው በነገው ዕለት ፍጻሜውን የሚያገኝ ይሆናል።
Ethiopian Football Federation
Amhara Football Referees
💥
✍️ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት እና ይቀላቀሉ።
✅ Telegram
https://t.me/Amhara21FootballReferees
✅ page
https://www.facebook.com/AmharaFootballReferees/
💥 Like 🔵 Share 🔴 Follow
27/08/2026
🔴 FIFA new referees course to he held on 25 the to 30th September.
Have a nice Cource. We proud of you.
Amhara Football Referees
💥
✍️ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት እና ይቀላቀሉ።
✅ Telegram
https://t.me/Amhara21FootballReferees
✅ page
https://www.facebook.com/AmharaFootballReferees/
💥 Like 🔵 Share 🔴 Follow
27/08/2026
🔴 ለ D- License ስልጠና ፈላጊዎች
በባህር ዳር ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስተባባሪነት የአማራ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር የ" ዲ " ላይሰንስ ስልጠና የሚሰጥ ስለሆነ ከላይ በተጠቀሰው አካውንት ገንዘቡን ገቢ በማድረግ እና የባንክ ደረሰኙን በተጠቀሰው ስልክ ቴሌግራም በማያያዝ ከሰኞ ማለትም ነሀሴ 25/2018 ዓ/ም ስልጠናውን መውሰድ ትችላላችሁ።
የስልጠና ቦታ:- ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ
Amhara Football Referees
Yohannis Temesgen
💥
✍️ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት እና ይቀላቀሉ።
✅ Telegram
https://t.me/Amhara21FootballReferees
✅ page
https://www.facebook.com/AmharaFootballReferees/
💥 Like 🔵 Share 🔴 Follow
27/08/2026
🔴 የፊፋ የኤሊት የጨዋታ አመራሮች ስልጠና በዛሬው ዕለት ነሃሴ 20/2018 መካሄድ ጀምሯል።
በስልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ብሔራዊ የዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሸዋንግዛው ተባባል ባደረጉት ንግግር "የአካል ብቃት ምዘናውን በስኬት አልፋችሁ እዚህ በመገናኘታችን ደስ ብሎኛል። ሁለቱን ኢንስትራክተሮች በማግኘታችን በእውነት እድለኞች ነን፤ እናንተ ከፊፋ ከፍተኛ አሰልጣኞች መካከል ግንባር ቀደም ናችሁ። ስለዚህ ዳኞች ከዚህ ኮርስ እስከ ጥግ እንዲጠቀሙበት እመክራለሁ፤ ማድረግ የምትችሉትን ያህል ከፍተኛ ጥረት አድርጉ። ጥሩ እና አዝናኝ አምስት ቀናት ይኖረናል ብዬ አስባለሁ፤ መልካሙን ሁሉ እመኝላችኋለሁ" ብለዋል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ባሕሩ ጥላሁን በበኩላቸው ለኮርሱ ኢንስትራክተሮች "ወደ ሁለተኛ ሀገራችሁ ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጣችሁ" ካሉ በኋላ በዚህ ዓመት ህይወታቸውን ላጡ ኮሚሽነሮች እና ዳኞች የአንድ ደቂቃ የሕሊና ጸሎት በማስደረግ ንግግራቸውን ቀጥለዋል። አቶ ባሕሩ አክለውም "በሀገራችን የዳኝነት እድገት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቀየረ ነው። ይህ የዳኞች ኮሚቴ ወደ ኃላፊነት ከመጣ ወዲህ የሚችሉትን ያህል ለማድረግ ሞክረዋል። በኢትዮጵያ ዳኝነት ውስጥ ሙያተኝነትን ለማሳደግ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ይህ በፌዴሬሽናችን ውስጥ የወሰድነው በጣም ትልቅ እርምጃ ነው። የዳኝነት እድገቱን በጥሩ መንገድ ላይ ለማስገባት ትልልቅ ውሳኔዎችን በመወሰናቸው የዳኞች ኮሚቴውን እንደገና ማመስገን እፈልጋለሁ" ብለዋል።
የኮርሱ አስተባባሪና የዳኞች ዲፓርትመንት ዳይሬክተሩ አቶ ሙሉጌታ ምስጋናው ስልጠናው እውን እንዲሆን አስተዋጽኦ ላደረጉ በፌዴሬሽኑ የሚገኙ የተለያዩ ክፍሎች እንዲሁም ለተሳታፊዎች የተሟላ ትጥቅ ያቀረበውን ጎፈሬን አመስግነዋል።
የሴካፋ የዳኞች ኃላፊ ዓሊ ሙሐመድ ፌዴሬሽኑ፣ የዳኞች ኮሚቴው እንዲሁም ዲፓርትመንቱ ይህን እድል በአግባቡ ለመጠቀም ያደረጉትን ጥረት አድንቀዋል። ዓሊ ሙሐመድ አክለውም "በዋና ጸሐፊው ፊት መጥቀስ የምፈልገው ነገር ቢኖር ዘንድሮ እና ያለፈው ዓመት ለአፍሪካ ዳኞች በአካል ብቃት በኩል ጥሩ ነበር። ቢያንስ 8፣ 7፣ 9 የፊፋ ዳኞች የሚወድቁባቸው አጋጣሚዎች ነበሩ፤ ይህም በሀገራቱ ውስጥ ትልቅ ችግር ይፈጥራል። በዚህም ካፍ እና ፊፋ ከአካል ብቃት አሰልጣኞች ኃላፊዎች ጋር ተነጋግረው አሰልጣኝ ወደ ሀገሪቱ እንዲልኩ እና ዳኞቹን እንደገና እንዲፈትሹ መጠየቅ ይኖርባቸዋል። አሁን ግን በኢትዮጵያ ምንም አይነት ችግር የለብንም፤ ስለዚህ ለዚያ ማጨብጨብ እንችላለን። ይህ በዋዛ የመጣ ሳይሆን በብቁ ባለሙያዎቻችሁ የተሰራ ጠንካራ ሥራ ነው፤ ለአፍሪካም በጣም ጥሩ አርአያ ነው" ብለዋል።
ይህ ስልጠና እስከ ሰኞ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚቀጥል ሲሆን ዛሬ ረፋድ በተካሄደው የአካል ብቃት ምዘና ከተፈተኑት 31 የጨዋታ አመራሮች መካከል ሁሉንም የፊፋ ዳኞች ጨምሮ ምዘናውን ማለፍ የቻሉ በአጠቃላይ 30 ተሳታፊዎች ስልጠናውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ።
ስልጠናውን በዋነኝነት የሚሰጡት የፊፋ እና የካፍ የአካል ብቃት ኢንስትራክተር ሙሐመድ ሁሴን ጋቦኒ ናቸው።
Ethiopian Football Federation
Amhara Football Referees
💥
✍️ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት እና ይቀላቀሉ።
✅ Telegram
https://t.me/Amhara21FootballReferees
✅ page
https://www.facebook.com/AmharaFootballReferees/
💥 Like 🔵 Share 🔴 Follow
25/08/2026
🔴 በሴፕቴምበር ወር በሚካሄዱ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ እና ኢንተር-ክለብ ውድድሮች ላይ በካፍ የተመደቡ ኢትዮጵያውያን የጨዋታ አመራሮች
Ethiopian Football Federation
Amhara Football Referees
💥 መልካም ጨዋታ
✍️ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት እና ይቀላቀሉ።
✅ Telegram
https://t.me/Amhara21FootballReferees
✅ page
https://www.facebook.com/AmharaFootballReferees/
💥 Like 🔵 Share 🔴 Follow