Amhara Table Tennis

Amhara Table Tennis

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Amhara Table Tennis, Professional Sports Team, Bahir Dar.

Photos from Amhara Table Tennis's post 05/12/2022

የክልላችን እንቁ አሰልጣኞቻችን የሆኑት
ኢንስትራክተር ሀይለሚካኤል አወቀ
ኢንስትራክተር ተስፋየ ሙሉጌታ
የ 1st level international olompic soldarity training ጥሩ ዉጤት በማምጣት በማለፋቸዉ
ለ 2nd level international olompic soldarity training ስልጠና ለመዉሰድ ወደ ቦታዉ ተንቀሳቅሰዋል ለአሰልጣኞቻችን መልካም የስልጠና ጊዜ እንመኛለን

20/02/2022
17/02/2022

የአማራ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ቢሮ ዘንድሮም በጠረጴዛ ቴኒስ ስፖርት ላይ እያደረገ ያለዉን ስፖርቱን የመግደል(የማጥፋት) ስራ አጠናክሮ ቀጥሏል ።
ቢሮዉ ባለፈዉ አመት በተደጋጋሚ ጊዜ የጠረጴዛ ቴንስ ስፖርትን ብቻ ተለይቶ የአገር አቀፍ ዉድድሮችን እና የኢትዮጲያ ሻምፒዮና ዉድድሮችን ለብዙ ጊዜ እየዘጋብን እና በዉድድሩ እንዳንሳተፍ እያደረገን እንደሆነ በአማራ ቲቪ እና በሶሻል ሚዲያ ለህዝብ ማሳዎቃችን ይታዎቃል
አሁንም በድጋሚ የጠረጴዛ ኳስ ስፖርትን ብቻ በመለየት ዘንድሮ የሚደረገዉን የኢትዮጲያ ሻምፒዮና ዉድድር የተለያዩ ምክንያቶች በመስጠት ላለመሳተፍ መወሰኑን ለስፖርቱ ተቆርቋሪ የሆኑ የቢሮዉ ሰራተኞች ነግረዉናል
ከኢትዮ ጠረጴዛ ኳስ ፌደሬሽን ከወር በፊት ደብዳቤ የተላከ ቢሆንም ቢሮዉ ደብዳቤዉ ዘግይቶ ስለደረሰን ለመዘጋጀት አጭር ጊዜ ስለሆነ ላንሳተፍ እንችላለን ይላሉ አንዴ ደግሞ ተሳታፊ ዞኖች ካሉ እንሳተፋለን ካሉ በኋላ ለዞኖች በደብዳቤም ሆነ በስልክ እስካሁኗ ሰአት ድረስ አለማሳዎቃቸዉን በየዞኖች ባደረግነዉ ማጣራት ደርሰንበታል ይሄ ማለት ሆን ብለዉ ዞኖችን ሳያሳዉቁ ተሳታፊ ዞኖች ባለማግኘታችን ዉድድሩን መሳተፍ አልቻልንም ሊሉ አንደሆነ መረጃዉ ቀድሞ ደርሶናል
በመሆኑም ይህን ክልላችን በዉጤታማነት የሚታወቅበትን ስፖርት የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ቢሮ ሀነ ብሎ ዉድድሮችን በመዝጋት ስፖርቱን እየገደለዉ መሆኑን ዘንድሮም በድጋሚ ለህዝባችን እና ለስፖርቱ አፍቃሪዎች ማሳዎቅ እንዎዳለን ።

ግልባጭ - ለአማራ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር እና ም/ ኮሚሽነር ቢሮ
- ለአማራ ክልል ጠረጴዛ ቴኒስ ፌደሬሽን
- ለኢትዮጲያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌደሬሽን
- ለአማራ ማስሚዲያ ኤጀንሲ
- ለሁሉም የስፖርት ሚዲያ አካላት
የአማራ ክልል ጠረጴዛ ቴኒስ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች ።

Photos from Amhara Table Tennis's post 06/06/2021

የፌደራል ት/ት ሚኒስቴር እና የኢትዮጲያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌደሬሽን በጋራ በመተባበር ያዘጋጁት የአንደኛ ደረጃ የጠረጴዛ ቴኒስ የአሰልጣኝነት ስልጠና ከግንቦት 18-2013 እስከ ግንቦት 29-2013 በባህርዳር ከተማ በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ፔዳ ካምፓስ ሲሰጥ ቆይቶ ዛሬ ተጠናቋል ።
ስልጠናው የወሰዱ ከምስራቅ አማራ የመጡ የHigh School የስፖርት ሳይንስ(Physical Education) 15 መምህራን ሲሆኑ ስልጠናውም
ስልጠናዉ በኢንስትራክተር ሀይለሚካኤል አወቀ ተሰጥቷል ።

22/10/2019

የኢትዮጲያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከኢትዮጲያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌደሬሽን ጋር በመተባበር በጋራ ያዘጋጁት 1st level olompic soldarity coaching course ስልጠና ከጥቅምት 9,2012 እስከ ጥቅምት 18,2012 በአዲስ አበባ ስፓርት አካዳሚ ግቢ ውስጥ በቱኒዚያዊው Ramzi እየተሰጠ ይገኛል በዚህ ስልጠና ክልላችን በመወከል
ኢንስትራክተር ሀይለሚካኤል አወቀ እና
ኢንስትራክተር ተስፋየ ሙሉጌታ
ስልጠናውን እየወሰዱ ይገኛሉ ለአሰልጣኞቻችን መልካም ስልጠና መልካም ውጤት እንመኛለን ።

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Bahir Dar?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Bahir Dar