12/07/2026
የሲዳማ ቡና ደጋፊዎች ማህበር በፀጥታ እና በሞተር ከሚያስተባብሩ ከሲዳማ ቡና ደጋፊዎች ጋር ውይይት በሀዋሳ አለም አቀፉ ስታዲየም አደረገ!
***
በነገው እለት ለሚደረገው ለሲዳማ ቡና እግርኳስ ክለብ አቀባበል #በፀጥታ ዙሪያ እና በሞተር ከፍለፊት ሆነው ከሚመሩ ልጆች ጋር የሲዳማ ቡና እግርኳስ ክለብ የደጋፊዎች ማህበር በዛሬው እለት ውይይት አድረገዋል።
በውይይቱ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ (Orientation) ከደጋፊዎች ማህበር የተሰጠ ስሆን በነገው እለት የሚደረጉ ፕሮግራሞች ከፀጥታ ሀይሎች ጋር በመቀናጀት ለክለባችን ውበት መስራት እንደሚገባ በመግለፅ የከተማችንን መሠረት ልማት እንዳይወድሙና የፀጥታ ስጋት እንዳይኖር በህብረት መስራት እንደሚገባ በማሳሰብ ከተሳታፊዎች ጋር ትውውቅ ተደረጓል።
በነገው እለት ከጠዋቱ 12:30 ጀምሮ ሁላችንም መለያችንን በመልበስ የተወደደውን እና ታላቁን ክለባችንን ሁላችንም እንድንቀበል ስል የደጋፊዎች ማህበር ለሁሉም ለክለባችን ወዳጆችና ለሀዋሳ ከተማ ህዝብ ጥሪውን አስተላልፏል።
የሲዳማ ቡና ደጋፊዎች ማህበር
12/07/2026
ለሻምፒዮኖቹ የሚደረግ የጀግና አቀባበል መርሃ ግብር ይፋ ሆነ::
ሐምሌ 05/2018 ዓ.ም ሀዋሳ
የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን የሆነው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ የቡድን አባላት በነገዉ እለት ማለዳ ወደ ክልላችን መዲና ሀዋሳ ከተማ ይገባሉ።
ጀግኖቻችን ድላቸውን በሚያበስር ክፍት ባስ በሀዋሳ ጎዳናዎች ላይ ለሕዝብ ይታያሉ::
የሚከተለውን መስመር ተከትለው በታላቅ ድምቀት ወደ ከተማችን ይገባሉ።
ማለዳ 1:00 ፦ ጥቁር ውሃ - ጉዞ ይጀመራል::
ተከታይ መስመር ፦ ሳውዝ ስፕሪንግ -> መድኃኒዓለም -> ሻፌታ አደባባይ -> ፒያሳ -> ሱሙዳ አደባባይ ሆኖ
መዳረሻ ፦ መስቀል አደባባይ ይሆናል።
በመስቀል አደባባይ በሚኖረዉ ታላቅ ፕሮግራም ላይ
የክልላችን ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተወዳጅ አርቲስቶች እና የተጋበዙ እንግዶች የሚገኙ ሲሆን የዕለቱ ፕሮግራም በ4:30 የሚጠናቀቅ ይሆናል።
የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ስራ አመራር ቦርድ ለጀግኖቹ በሚደረገዉ በዚህ ታሪካዊ ዕለት መላዉ ከክልላችን የተወጣጡ የክለባችን ደጋፊዎችና ወዳጆች የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ ጀግኖቻችንን በወጣው መርሃ ግብር መሰረት በነቂስ ወጥቶ እንዲቀበል ዳግም ጥሪ ቀርቧል::
11/07/2026
መኪና ሞተር ያለው በእለተ #ሰኞ ጠዋት 2 ማንም እንዳይቀር🇱🇻!
11/07/2026
Egenshiisha❗
Apaache Xexxerisu noo'ne baalu Sidaamu Buni irkisaanora፥
Anfumonte gede Kilawenke Sidaamu buni 2018 M.D Ethiyoopiyu pirimeelige Boowe qeele kaayisasi qaangaita ikkitanna
Tenne worba kilawenke miillanna godo'laano Albakenni daganni noo Sanyote barra soodihunni 2:00 saatenni Godo'laano dukkinse haa'nanni. Tenne qixaawora Sidaamu buni lekkate kaase kilawe irkisaanote maamari sidaamu dagoomu qoqqowi mootiimma keerunna ga'labote biiro ledo halamatenni xexxerisi noonsa kilawenke irkisaano Sidaamu buni maaliya udidhe uuyinenansa Borresante gaamo dukkisanno yinoonni daafira..
xexxerisu noo'ne irkisaano Sanyote barra Soodo 2:00 saatenni Leella danditinanni ooso Woronni worommo bilbili kiironni bilbilitinanni borreesantinanni gede sokkanke saayinseemmo.
Qaagishsha ፦ Wollu mottore noohu daa di daadano yaa di ikkitinno!!
Bilblilu kiiro
1.0919666901 Geetu siyumi
2.0916605880 Iyaasu mulugeeta
Dandaami'nero udidhiniro diginbeemmo!
Borresantinoonni ooso Ga'a Sanbata Barrihunni 10:00 saatenni Hawassi International Isatayideeme Sidaamu Buni irkisaanote maamari biiro daggine baaje adhitinanni gede qaagisineemmo.
Assatenni Tuqisse!
11/07/2026
የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ቡድንን ሰኞ ዕለት ሐምሌ 06 ከጥዋቱ 3:00 ጀምሮ የጀግና አቀባበል ይደረግለታል-ቦርዱ
*********
የስዳማ ቡና እግር ኳስ ቡድን ቦርድ የፊታችን ሰኞ የሚደረገውን የስዳማ ቡና የተጫዋቾች አቀባበልን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል ።
በመግለጫውም የ2018 ሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፕዮን የሆነው እና በኢትዮጵያ ዋንጫ የብር መዳሊያ ተሸላሚ መሆን የቻለው የስዳማ ቡና የእግር ኳስ ክለብ ሰኞ ዕለት ሐምሌ 06 ከጥዋቱ 3:00 ጀምሮ በክልሉ መዲና ሀዋሳ ከመግቢያው ከጥቁር ውሃ አንስቶ እስከ መስቀለ አደባባይ የጀግና አቀባበል ይደረግለታል።
የስዳማ ቡና የእግር ኳስ ክለብ የቦርድ ተሰብሳቢ አቶ ጀጎ አገኘሁ እንደገለፁት የስዳማ ቡና በ2017 ዓ.ም የውድድር ዘመን የገጠመው ያልተጠበቀ ክስተት በክለቡና በክልሉ ማህበረሰቡ የነበረውን ቁጭት በድል በመቀየር ስላሳየው ጀግንነት የሚመለከታቸውን ሁሉ አመስግነው በዘንድሮው የ2018 ዓ.ም የተመዘገበው ውጤት ይበል የሚያሰኝና የሚያስደንቅ መሆኑን ገልፀዋል።
የድል ቀኑን በጋራ ለማክበር የስዳማ ቡና ደጋፊዎች፣የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች፤ ባለድርሻ አካላትን ጨምሮ የሚመለከታቸው ሁሉ በነቂስ በመውጣት ለክለቡ የጀግና አቀባበል እንዲያደርጉም የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጄጎ አገኘው ጥሪ አቅረበዋል።
የስዳማ ቡና የስፖርት ክለብ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ከነዓን በለጠ በበኩላቸው ክለቡ በዘንድሮው አመት ያስመዘገበው ድል የሚያስደንቅ መሆኑን ገልፀው ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ የነበረው ትግል ፍሬ በማፍራቱ የተሰማቸው ደስታ ላቅ ያሌ እንደሆነና ሰኞ ዕለት ለክለቡ በሚደረገው የጀግና አቀባበል ላይ የሚመለከታቸው ሁሉ በመርሃግቡሩ ላይ በመገኘት ከክለቡ ጎን በመቆም የደስታ ቀን እንድያከብር ጥሪ አቅርቧል።
ክለቡ ወደ ስፍራው ስደርሰ የምስጋና፣የእውቅናና የሽልማት መርሃግብር እንደሚካሄድ የተገለፀ ስሆን ከእርስም ጎንለጎን የስዳማ ቡና በጣይ ኢትዮጵያን በመወከል በአፍሪካ መድረክ ላይ ስለሚኖረው ውድድርና በአጠቃላይ የክለቡ ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ በርካታ ስራዎች እንደሚከናወን ነው ከመድረኩ የተገለፀው።
የሲዳማ ቡና እግርኳስ ክለብ
11/07/2026
አልጋ ወራሹ አሰልጣኝ - አምሃ ዘውዱ
****************
ውልደቱና ዕድገቱ በሲዳማ ክልል አለታ ወንዶ ከተማ ነው። ባልተሳካው የተጫዋችነት ህይወቱ ተስፋ ያልቆረጠ፣ ነገውን አስቦ ለእያንዳንዷ ስኬት ዋጋ የከፈለ ትጉህ ሰራተኛ ነው። ከትምህርቱ ጎን ለጎን ጥሩ እግር ኳስ ተጫዋች መሆን ይሻ የነበረው አምሃ በአንድ ወቅት ያስተናገደው ጉዳት በፈለገው ልክ የሚወደውን እግር ኳስ እንዳይጫወት ማነቆ ሆነበት።
አገግሞ ለመመለስ የተቻለውን ሁሉ ቢያደርግም ነገሮች ግን ያንን ያክል ቀላል አልሆኑም።እንደ ቀልድ ስር የሰደደው ጉዳት እግር ኳስ መጫወትን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲያቆም አስገደደው። ገና የሦስት ዓመት ልጅ ሳለ ነበር የትውልድ ቀዬውን ለቆ ወደ ሀዋሳ የመጣው። የአክስቱ ልጆች ጋርም ተቀምጦ ኑሮን አንድ ብሎ የጀመረባት ከተማ ወትሮም የሰው ፍቅርን ታውቅበታለችና አምሃንም በዋዛ አለቀቀችውም።
የወላጅ ናፍቆት ሲበረታ ክረምትን ጠብቆ ወደ አለታ ወንዶ ከተማ ያመራል። ምስጋና ለአሁኑ የሀዋሳ ከተማ አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ይሁንና አምሃ ለመጀመሪያ ጊዜ ኳስን ማንከባለል የጀመረው በሸዋ ጨርቃጨርቅ ፕሮጀክት ነበር።ያ ጊዜ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የኤም አር አይ ምርመራ የሚደረግበት ወቅት በመሆኑ የዚህ ፕሮጀክት ታዳጊዎች በአግባቡ ተመዝነው ለተለያዩ የእግርኳስ ታዳጊ ቡድኖች የመጫወት ዕድልን አግኝተዋል።
አምሃ 2006 ላይ ከገጠመው ጉዳት በፊት ከሸዋ ጨርቃጨርቅ ፕሮጀክት በተጨማሪ ያኔ ትልቅ ስም ለገነቡት ለሴንትራል ሆቴል ፣ ለአለታ ወንዶ ተክሌ ሆቴል እና ለሌላኛው የአለታ ወንዶው ልዩ ሆቴል ተጫውቶ በዋንጫ የታጀቡ ዓመታትን አሳልፏል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ31 ዓመታት ትዕግሥት በኋላ ሱዳንን አሸንፎ ለአፍሪካ ዋንጫ ሲበቃ አምሃ እንደ ኢትዮጵያዊነቱ ደስታውን መቋቋም አቅቶት አልቅሷል።ያ የአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ቡድን ለእርሱም ቢሆን አዲስ የህይወት መንገድ ፈጥሮለታል። "አሰልጣኝ መሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የተመኘሁት ያንን ብ/ቡድን ስመለከት ነው።" የሚለው አምሃ "መምህር የነበሩት ጋሽ ሰውነት ያመጡት ስኬት ህልሜን በእውን አሳይቶኛል።" ይላል።
እርግጥ ነው ይህ በወሬ ብቻ የቀረ ምኞት አይደለም።ቀስ በቀስ እየተተገበረ የሚገኝ መሻት እንጂ።አምሃ ከመጀመሪያም የሰው እጅ አልጠበቀም። ገና የ17 ዓመት ታዳጊ እያለ ነበር ቢ ቤስት የተባለ የታዳጊ ፕሮጀክት በዛ ለጋ ዕድሜው በማቋቋም ሙያውን የተቀላቀለው። ቀን ቀን ተማሪ፣ አመሻሽ ደግሞ የእግር ኳስ አስተማሪ የሆነው አምሃ ከዓመታት ቆይታ በኃላ 2011 ላይ ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ እና ማኔጅመንት ኢንጅነሪንግ በመጀመሪያ ድግሪ ተመርቋል።
ወዲያውም በሙያው ስራ አግኝቶ ሀገሩን እያገለገለ ጎን ለጎን ደግሞ ብዙ የለፋበትን ቢ ቤስት ቡድኑን ያሰለጥናል። ይህን እያደረገ እንደምንም አንድ ዓመት ሞላው። "ሰዎች ስራህን እንደቀልድ እንዴት ታቆማለህ።"ይሉኛል።"እኔ ግን ልክ እንደ ስራው ሁሉ ኳሱን ማሰልጠን ማቆም አልችልም።"የሚለው አምሃ የተመረቀበትን ሙያ ሙሉ ለሙሉ ትቶ የሙሉ ጊዜ አሰልጣኝ ሆነ።
የማይታመን ተግባር ቢመስልም እርሱ ለእግር ኳሱ ተሰጥቷልና ሳያቅማማ አድርጎታል። ያመናት እግርኳስ አልካደችውም።ቀስ በቀስ ለተሻለ ማዕረግ አበቃችው እንጂ።ሀዋሳ ከተማን በሲዳማ ልዩ ልዩ ሻምፒዮና አሸናፊ ያደረገው አምሃ፣ የሲዳማ ከ17 ዓመት በታች ቡድንን ደግሞ 2016 ላይ በሀገር አቀፍ ውድድር ለፍፃሜ አብቅቶ በኢትዮ ኤሌክትሪክ በመለያ ምት ተሸንፎ 2ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
ይህ ሰው ከ2 ዓመት በፊት 2014 ላይ የተወለደባትን ከተማ አለታ ወንዶን በአሰልጣኝነት ይዞ በኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ውጤታማ በማድረግ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ሊግ አብቅቷል። ይህም በአካባቢው የጀግና ያክል ተቆጥሮ እንዲወደድ አድርጎታል። ከአምሃ አፍ ሁሌም የማይጠፋ አንድ አሰልጣኝ አለ። "እሱ ሙያዬን እንዳሻሽልና ሙሉነት እንዲሰማኝ ዋጋ ከፍሎልኛል።"ይላል።ይህ የተባለው ሰው የወቅቱ የመቻል እግርኳስ ክለብ አሰልጣኝ የሆነው ሙሉጌታ ምህረት ነው።
የሀዋሳው ፍሬ ሙሉጌታ ምህረት አምሃ ለፈለገው ነገር ሁሉ ቅርቡ ነበር።አንዳንዴማ የራሱን ቡድን እንዲያሰለጥንና ሙያውን እንዲያሳድግ ያደርገው ነበር። አንዳንዴ ደግሞ ከአምሃ ቡድን ጋር የራሱን ቡድን የወዳጅነት በማጫወት ለታዳጊዎች ልምዱን ያካፍላል። "ለዛሬ መድረሴ አንድም በእርሱ ነው።" ሲል አምሃ ተናግሯል።
2017 ላይ የሲዳማ ከ20 ዓመት በታች ቡድን ዋና አሰልጣኝ ተደርጎ የተሾመው አምሃ ለታመነበት ቦታ የሚመጥን ሰው መሆኑን ለማሳየት ጊዜ አልወሰደበትም። አሰላና ቡራዩ ላይ በነበረው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡናን እየመራ ምድቡን በአንደኝነት አጠናቀቀ።
ሀዋሳ ላይ በነበረው የማጠቃለያ ውድድር ደግሞ በፍፃሜው አዳማ ከተማን 2 ለ 1 በማሸነፍ ሲዳማ ቡናን ለዋንጫ አበቃው። በዓመቱ ዳግም ቡድኑን ለዋንጫ ያበቃው አምሃ ታዳጊ ቡድኑ በመድረኩ ወጥነት ያለውና ኢ-ተገማች እንዲሆን በማድረግ ስኬትን በስኬት ላይ ደርቧል።
የዲ ላይሰንስ ፍቃድ ያለው አምሃ አንድ አሰልጣኝ የሲ ላይሰንስ ፍቃድ እንዲኖረው ክለብ መያዝ አለበት የሚለው የፌዴሬሽኑን ህግ ጠብቆ ከወራት በኋላ ደግሞ ደረጃውን ወደ ሲ ላይሰንስ ያሳድጋል። ለዚህ ዕድገት ሲዳማ ቡና መንገድ ጠርጎለታል።
አምሃ በ2 ዓመት ውስጥ 12 ተጫዋቾችን ለሊጉ ክለቦች አብቅቷል። ዛሬ በሲዳማ ቡና ዋናው ቡድን ውስጥ የሚገኙት አስቻለው ሙሴ ፣ ፍቃዱ ማጃ ፣ አላዛር እያሱና እያሱ ሮንዴ የእርሱ ሙያ ያረፈባቸው ታዳጊዎች ናቸው። በኢትዮጵያ ቡና የሚገኘው ናትናኤል ፍሬው እና ለሀዋሳ ከተማ የሚጫወተው ናትናኤል ሸገሙ እንዲሁ ከሚጠቀሱት መካከል ናቸው።
አምሃ ይናገራል "ህልሜ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በአሰልጣኝነት እየመራሁ ለዓለም ዋንጫ ማብቃት ነው" ይላል። መማር የማይሰለቸው፣ ለማወቅ የሚጥርና የተማረውን ለመተግበር እንቅልፍ የሚያጣ ሰው መሆኑ ህልሙ ሊሳካ በትክክለኛው መንገድ ላይ ለመገኘቱ ያሳለፈው ህይወት ምስክር ይመስላል።
EBC Sport !
10/07/2026
የሲዳማ ቡና ደጋፊዎች ከክልላችን መንግስት የሚጠብቁት ሌላኛዉ ዋንጫ !!
የ2018 ዓ.ም የኢትዮጲያ እግር ኳስን በበላይነት ያጠናቀቀዉ ክለባችን ሲዳማ ቡና የሊጉን ዋንጫ ከፍ ማድረጉ ይታወሳል።
ከየትኛዉም ጊዜ በላይ ለሊጉ ክስተት ሆነዉ የነበሩ የሲዳማ ቡና ደጋፊዎችን እየመራ በማስጨፈር አስደናቂ የዉድድር ዘመንን ላሳለፈዉ ለሲዳማ ቡና ባለዉለታ እያሱ የክልላችን መንግስት ምን አይነት ዋንጫ (ሽልማት) ሊያበረክት ነዉ በማለት የሲዳማ ቡና ደጋፊዎች እና የስፖርቱ ቤተሰብ በጉጉት በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።
የክልላችን መንግስት በእያሱ በኩል የክለቡ የጀርባ አጥንት ለሆኑ ደጋፊዎች ትልቅ እዉቅና በመስጠት ለክለቡ ባለዉለታ ድንቅ ስጦታ ያበረክታል ብዬ በተስፋ እጠብቃለሁ።
በታሪካዊዉ ዕለት ባለታሪካችንን እናመሰግናለን !!
09/07/2026
የ2018 የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች - ያሬድ ባየህ ( ሲዳማ ቡና )
የዋንጫ እና የ250 ሺህ ብር ተሸላሚ 🇱🇻❤!!
09/07/2026
በኢሊሌ ሆቴል እየተካሄደ በሚገኘው 2018 የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከቦች የሽልማት መርሐግብር ላይ የተወሰዱ ምስሎች!!