01/10/2026
አንተነህ ተስፋዬ ፋሲል ከነማን ተቀላቅሏል!
ከአርባምንጭ ከነማ የእግር ኳስ ህይወቱ የጀመረው እና በተለያዩ የሀገሪቱ ክለቦች መጫወት የቻለው ፡ በሚያስጨበጭብ እና ታክቲካዊ በሆነ የመከላከል ብቃቱ በበርካቶች አድናቆት የሚቸርለት አንተነህ አጼዎቹን በትላንትናው ዕለት ሊቀላቀል ችሏል።
በመጠነኛ ፊዚካሉ በየትኛውን ግዙፍ አጥቂዎች መረታት የማይችለው እና ብልሀት በሞላው የመከላከል ስልቱ በብዙሀኖች ዘንድ አድናቆትን ያስቸረዋል።
የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን ከስሁል ሽረ ጋር ካሳለፈ በኋላ ዘንድሮ በጥሩ ግንባታ ላይ የሚገኘው ፋሲል ከነማን ሊቀላቀል ችሏል።
መልካም እድል አንትዬ 👏👏