Ethiopian Athletics Federation

Ethiopian Athletics Federation

Share

This is the official social media page of the Ethiopian Athletics Federation, bringing you the latest news, updates, and achievements. Her Excellence Mrs.

Although the exact roots of Ethiopian Athletics cannot be retraced back accurately, it is widely believed that the sport was widely practiced in schools and military camps before 1897. The sport was limited to these parts of society only because others did not have access to equipment used for competitions or was not organized in a manner that motivated progress. But after signs that the sport was

Photos from Ethiopian Athletics Federation's post 08/08/2026

Ethiopian 1-2 🤩

Almaz Yohannis powers to 9:15.81 to claim gold in the women’s 3000m steeplechase alongside her Ethiopian comptraiot, Wosane Asefa who finishes second with 9:30.50 🫂

🇰🇪’s Anatasha Cheptoo claims third 🥉 with 9:37.18

World Athletics

Photos from Ethiopian Athletics Federation's post 08/08/2026

በ800 ሜትር የወንዶች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወደ ፍፃሜ ማለፍ አልቻሉም

በአሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ ባለው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ800 ሜትር የወንዶች ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው የተሳተፉት አትሌት የሮሰን ግርማ እና አትሌት ነጋሄ እያሱ ወደ ፍፃሜ ማለፍ አልቻሉም።

በምድብ አንድ የተወዳደረው አትሌት የሮሰን ግርማ በውድድሩ ወቅት የዓለም አትሌቲክስ የውድድር ሕግ ጥሰት በመኖሩ ውጤቱ ተቀባይነት አላገኘም።

በሌላ በኩል አትሌት ነጋሄ እያሱ 800 ሜትሩን 1:50.86 በሆነ ስዓት በመግባት 7ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

በዚህም ውጤት ወደ ፍፃሜው ማለፍ አልቻለም።

የሴቶች 3ሺ ሜትር መሰናክል ፍፃሜ ውድድር ከደቂቃዎች ብኃላ የሚካሄድ ይሆናል።

Photos from Ethiopian Athletics Federation's post 08/08/2026

በ3,000 ሜትር መሰናክል ኢትዮጵያ ወርቅና ብር ሜዳሊያ አስመዘገበች

እንኳን ደስ አለን!

በአሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ ባለው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 3,000 ሜትር መሰናክል ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተከታትሎ አንደኛና ሁለተኛ በመውጣት ድንቅ ድል አስመዝግበዋል።

🥇 አትሌት አልማዝ ዮሐንስ 9:15.81በውድድሩ አንደኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኝታለች።

አትሌት ወሰኔ አሰፋ 9:30.50 ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኝታለች።

ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው የሜዳሊያ ድምርዋን እያሳደገች ትገኛለች።

በቀጣይ ውድድሮችም ወደ ፍፃሜ ያለፉት አትሌቶቻችን ተጨማሪ ድሎችን እንደሚያስመዘግቡ ታላቅ ተስፋ ተጥሎባቸዋል።

እንኳን ደስ አለን!

🇪🇹

Photos from Ethiopian Athletics Federation's post 08/08/2026

በሴቶች 800 ሜትር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለፍፃሜ ደረሱ

በአሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሦስተኛ ቀን፣ የሴቶች 800 ሜትር ግማሽ ፍፃሜ ውድድር ተካሂዷል።

በዚህም ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው የተሳተፉት አትሌቶች ደራርቱ ሽብሩ እና ሀብታም ገበየሁ ለፍፃሜ ውድድር አልፈዋል።

አትሌት ደራርቱ ሽብሩ በምድብ ሁለት ተወዳድራ በ2:03.41 በመግባት 3ኛ ደረጃን በመያዝ ለፍፃሜ አልፋለች።

አትሌት ሀብታም ገበየሁ በምድብ ሶስት የተሳተፈች ሲሆን፣2ኛ ደረጃን በመያዝ የፍፃሜ ውድድርን ተቀላቅላለች።

በተመሳሳይ ርቀት በወንዶች ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው የተወዳደሩት አትሌት ዮሮሰን ግርማ እና አትሌት ነጋሄ እያሱ ወደ ፍፃሜ ለማለፍ ያደረጉት ጥረት ሳይሳካላቸው ቀርቷል።

Photos from Ethiopian Athletics Federation's post 07/08/2026

ማስታወቂያ !!

Photos from Ethiopian Athletics Federation's post 07/08/2026

የሜዳልያ አሰጣጥ ስነ ስርዓት :-

በዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 5ሺ ሜትር የብር ሜዳልያ አሸናፊ አትሌት ሽቶ ጉሚ እና በወንዶች 5ሺ ሜትር ነሀስ ሜዳልያ አሸናፊ አትሌት ዳምጠው ከበደ

Photos from Ethiopian Athletics Federation's post 07/08/2026

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በ1500 ሜትር በሁለቱም ጾታ ለፍጻሜ አለፉ

ነሐሴ 01/2018 ዓ.ም

በአሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ ባለው 21ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና፣ በ1500 ሜትር የማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው የተሳተፉ አትሌቶች በሁለቱም ጾታ ወደ ፍጻሜ ውድድር አልፈዋል።

በወንዶች 1500 ሜትር
አትሌት ደስታው ታዴ በ3:43.03 የውድድር ጊዜ በማስመዝገብ አራተኛ ደረጃን ይዞ ወደ ፍጻሜ ውድድሩ አልፏል።

በሴቶች 1500 ሜትር
አትሌት ሀረገወይን ካላዩ ከምድብ ሁለት 4:12.54 በሁለተኛነት በማጠናቀቅ ወደ ፍጻሜ ውድድሩ አልፋለች።

በተመሳሳይም አትሌት ኤልሳቤት አማረ በ4:18.24 በመግባት ምድብ ሦስትን በአንደኝነት በማጠናቀቅ ለፍጻሜ ውድድሩ አልፋለች።

ፎቶ ከፋይል


Photos from Ethiopian Athletics Federation's post 06/08/2026

ኢትዮጵያ በዓለም ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና የብርና የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች

ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም

በአሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሴቶችና በወንዶች 5000 ሜትር ውድድር የብር እና የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች ።

በሴቶች 5000 ሜትር ፍጻሜ አትሌት ሽቶ ጉሚ 15:07.21 በሆነ ሰዓት 2ኛ በመግባት ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች።

በተመሳሳይ ውድድር የተሳተፈችው አትሌት እመቤት ጥላሁን 6ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። የውድድሩ አሸናፊ ደግሞ ዩጋንዳዊቷ አትሌት ቼሮፕ ሆናለች።

በወንዶች 5000 ሜትር ፍጻሜ አትሌት ዳምጠው ከበደ 13:35 በሆነ ሰዓት 3ኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የነሐስ ሜዳሊያ አስገኝቷል።

የውድድሩ አሸናፊ ኬንያዊው አትሌት ፍራንክሊን ሲሆን፣ አትሌት ማማሩ ጎዴ የግል ምርጥ ሰዓቱን በማስመዝገብ 5ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

በሌላ በኩል በሻምፒዮናው የተካሄዱ የማጣሪያ ውድድሮችም ተካሂዷል ።

በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል የመጀመሪያ ማጣሪያ አትሌት አልማዝ ዮሀንስ 9:42.45 በሆነ ሰዓት 1ኛ በመውጣት ወደ ፍጻሜ አልፋለች። እንዲሁም አትሌት ወሰኔ አሰፋ 9:56.36 በሆነ ሰዓት 2ኛ በመግባት የፍጻሜ ተፎካካሪ ሆናለች።

ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው በሜዳሊያ ውጤቷን እያሳደገች ሲሆን፣ ወደ ፍጻሜ ያለፉት አትሌቶችም በቀጣይ ውድድሮች ተጨማሪ ድሎችን እንደሚያስመዘግቡ ተስፋ ተጥሎባቸዋል።

Photos from Ethiopian Athletics Federation's post 05/08/2026

በ800 ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወደ ግማሽ ፍጻሜ አለፉ

ሐምሌ 29/2018 ዓ.ም

በአሜሪካ ኦሪገን በሚካሄደው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ በተካሄዱ የ800 ሜትር የማጣሪያ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ማለፍ ችለዋል።

በወንዶች 800 ሜትር የመጀመሪያ ማጣሪያ የተሳተፈው አትሌት ነጋሄ እያሱ 1:51.16 በሆነ ሰዓት ውድድሩን በ1ኛ ደረጃ በማጠናቀቅ ወደ ግማሽ ፍጻሜ አልፏል።

በሌላኛው የወንዶች 800 ሜትር የማጣሪያ ምድብ የተሳተፈው የሮሰን ግርማ 1:47.57 በሆነ ሰዓት 4ኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ተቀላቅሏል።

በሴቶች 800 ሜትር የመጀመሪያ ማጣሪያ የተሳተፈችው ደራርቱ ሽብሩ 2:10.28 በሆነ ሰዓት 5ኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችላለች።

እንዲሁም በሴቶች 800 ሜትር ምድብ 4 የተወዳደረችው ሀብታም ገበየሁ 2:04.66 በሆነ ሰዓት 1ኛ ደረጃን በመያዝ በአስደናቂ ብቃት ወደ ግማሽ ፍጻሜ አልፋለች።

በዚህም ኢትዮጵያ በ800 ሜትር ውድድር በሁለቱም ፆታዎች ተስፋ ሰጪ ውጤት በማስመዝገብ በቀጣይ ዙሮች ለሜዳሊያ የሚደረገውን ፉክክር በጠንካራ መንፈስ ይቀጥላሉ።

Photos from Ethiopian Athletics Federation's post 04/08/2026

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ቡድን በሰላም ኦሪገን ደርሷል

ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም

በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት፣ ዩጂን ከተማ ከሐምሌ 29 እስከ ነሐሴ 3/2018 ዓ.ም በሚካሄደው 21ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች (World Athletics U20 Championships) አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን በሰላም ወደ ኦሪገን ደርሷል።

ሻምፒዮናው በዓለም አትሌቲክስ ታሪክ ታዋቂ በሆነው ሄይዋርድ ፊልድ (Hayward Field) ስታዲየም የሚካሄድ ሲሆን፣ ይህ ስታዲየም በርካታ ዓለም አቀፍ ውድድሮችንና ታሪካዊ የአትሌቲክስ ውድድሮችን ያስተናገደ የዓለም ታዋቂ የአትሌቲክስ ስቴዲየም ነው።

በዘንድሮው የዓለም ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በ5000 ሜትር፣ 3000 ሜትር፣ 1500 ሜትር፣ 800 ሜትር (በሁለቱም ፆታዎች)፣ 3000 ሜትር መሰናክል (በሴቶች)፣ 400 ሜትር (በሴቶች) እንዲሁም በርምጃ ውድድር (በሁለቱም ፆታዎች) በመሳተፍ ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ በተጠናከረ ዝግጅት ቀርባለች።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለመላው ቡድን የተሳካ ውድድርና የድል ጉዞ ይመኛል።

መልካም ዕድል!

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Address


Addis Ababa