EAS-Ethiopian Accreditation Service

EAS-Ethiopian Accreditation Service

Share

Ethiopian National Accreditation Office

EAS was established as an autonomous federal government office having its own legal personality.

EAS was established as an autonomous federal gov’t office having its own legal personality will offer accreditation services on a national & Intern' basis for conformity assessment bodies.. The mandate of EAS is to accredit, by formal third-party recognition, the competence of Conformity Assessment Bodies (CABs) to perform specific activities, such as test, calibrations, certifications or inspecti

Photos from EAS-Ethiopian Accreditation Service's post 12/08/2026

ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት እና ከሲቪል ሰርቪስ የሪፎርም ክትትል ኮሚቴ የተውጣጡ የአመራሮች እና የባለሙያዎች ቡድን በኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት (EAS) ተገኝተው የመስክ የሥራ ጉብኝት አደረጉ።

ልዑካኑ በጉብኝታቸው ወቅት የተቋሙን ስማርት ክፍል (Smart Room)፣ የልህቀት እና የታሪክ ምዕራፎች የተሰነዱበትን የኤግዚቢሽን ማዕከል እንዲሁም የተለያዩ የቴክኒክ እና የአገልግሎት መስጫ ክፍሎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ከጎብኚው ቡድን አባላት የተቋሙን አሠራር፣ የሪፎርም እና የዲጂታላይዜሽን እርምጃዎችን፣ እንዲሁም የጥራት መሰረተ-ልማት አገልግሎቶችን በተመለከተ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን፤ ለተነሱት ጥያቄዎች በኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን አንዷለም ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል።

አቶ ወንድወሰን አንዷለም በሰጡት ማብራሪያ ተቋሙ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን፣ የብቃት ማረጋገጫ ሂደቶችን ለማፋጠን እና ሀገራዊ የጥራት ደረጃን ዓለም አቀፍ ተፎካካሪ ለማድረግ እያከናወነ የሚገኘውን ዘመናዊ አሠራር አብራርተዋል።

የጉብኝቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት የተመዘገቡ የዘመናዊነት፣ የዲጂታላይዜሽን እና የተቋማዊ ሪፎርም ሥራዎችን ያደነቁ ሲሆን፤ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች አሠራርን ለማዘመን የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ጥሩ ተሞክሮ መሆኑን ገልጸዋል።

Photos from EAS-Ethiopian Accreditation Service's post 03/08/2026

ያሰበችውን የምታሳካ ሀገር ኢትዮጵያ!

03/08/2026
03/08/2026

ተስፋን እንትከል ፤

አሻራችንን እናሳርፉ
ኢትዮጵያ ሀገራችን ትለምልም !

የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት

Photos from Ethiopian Ministry of Trade and Regional Integration's post 03/08/2026
Photos from EAS-Ethiopian Accreditation Service's post 03/08/2026

የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት (EAS) አመራሮችና ሠራተኞች በስምንተኛው የአረንጓዴ አሻራ። 🌿🇪🇹

Photos from Kassahun Gofe Balami's post 03/08/2026
Photos from EAS-Ethiopian Accreditation Service's post 21/07/2026

3ኛው "የኢትዮጵያን ይግዙ" የንግድ ሳምንት ዝግጅት በይፋ ተጀመረ

(አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም) የሀገር ውስጥ አምራቾችንና ሸማቾችን በቀጥታ በማገናኘት ሰፊ የግብይትና የትስስር ዕድል የሚፈጥረው 3ኛው ሀገር አቀፍ "የኢትዮጵያን ይግዙ" የንግድ ሳምንት ዝግጅት በይፋ መጀመሩን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከነሐሴ 28 እስከ ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚካሄደው ይህ ታላቅ የንግድ ሳምንት፤ የሀገር ውስጥ ምርቶችን ጥራትና ተወዳዳሪነት የሚያሰፋ፣ የአምራቾችን አቅም የሚያሳድግና ህብረተሰቡ የሀገሩን ምርት በስፋት እንዲጠቀም የሚያበረታታ አገራዊ መድረክ ነው።

የኩነቱን ዝግጅትና የቅድመ-ዝግጅት ስራዎች ያሉበትን ደረጃ የመገምገሚያ መድረክ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክቡር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በተገኙበት ከዝግጅት ኮሚቴዎች ጋር ተካሂዷል።

በመድረኩ ላይ ክቡር ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት "የንግድ ሳምንቱ 'የኢትዮጵያን ይግዙ' በሚል ታላቅ አገራዊ መሪ ቃል መዘጋጀቱ የሀገር ውስጥ አምራቾችን ከማበራታት ባሻገር፣ በምርትና በገበያው መካከል ያለውን የአቅርቦት እጥረት ለመቅረፍና አምራችና ሸማችን ያለአላስፈላጊ ደላሎች በቀጥታ ለማገናኘት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።

በነሐሴ ወር መጨረሻ በሚካሄደው በዚህ የንግድ ሳምንት በርካታ የሀገር ውስጥ አምራቾች ምርቶቻቸውን ለህዝብ የሚያቀርቡ ሲሆን፣ ከግብይቱ ጎን ለጎን የንግድ ለንግድ (B2B) ትስስሮች እና የፓነል ውይይቶች እንደሚካሄዱ ተገልጻል።
Kassahun Gofe Balami
Bonsa B Negera
Wondwosen Andualem Abaye
Ethiopian Ministry of Trade and Regional Integration

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


Ring Road
Addis Ababa
3898

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00