ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል

ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል

Share

Get latest informations.

Photos from ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል's post 10/07/2026

✌️የዴቭ ሳንጃው የሀገር ልዩነት፣የቦታ ርቀት ያልገደበው እውነተኛ የክለብ ፍቅር በ Alexandria,va America

✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)ከ Alexandria,va America

✌️ዴቭ ሳንጃው የሚለው ስም ከታላቁ ክለብ ጋር ለዓመታት በደጋፊነት፣በአጋርነት፣በተቆርቋሪነት፣ራስን ለክለብ ያለስስት አሳልፎ ከመስጠት ጋር ዓመታትን አብሮ ተሻግራል፤ህይወት በሌላ አቅጣጫ ወደ ሌላ ሀገር ድንበር አቋርጣ ብትሻገርም ይሄ ፍቅር በሀገር ቤት ተገድቦ አልቀረም፤አብሮ አትላንቲክን አቋርጦ America Alexandria Virginia ገብቶ መሽጓል።

✌️አስገራሚው ነገር ያ ክለብ ፍቅርና ተቆርቋሪነት ዛሬም በሠው ሀገር እንደተንተከተከ፣ከመብረድና ከሠቀዝቀዝ አብሮ እንደጋለ ከአንድ እጅ ጣቶች በላይ አብሮ መክረሙ እንጂ።

✌️በሚኒሶታና በኋላም በ Alexandria Virginia ያገኘነው ዴቭ ሳንጃው የትም ቦታ ቢጓዝ፣ የትም ሀገር ቢኖር፣ የጊዮርጊስ ፍቅር በልቡ ውስጥ ታትሞ መንተክተኩን አላቆመም።

✌️የሚያስገርመው ነገር ዴቭ ሳንጃው ያ የማይበርደው፣ያ አትላንቲክን አብሮት የተሻገረው የቢጫና ቀይ ለባሾቹ ፍቅር በልቡ ብቻ አልቀረም፤ መኪናውንም የጊዮርጊስ ማንነት የሚያንጸባርቅ፣መኪናው ስለ ሀገሪቱ አንጋፋ ክለብ አፍ አውጥታ እንድታወራም አድርጓታል። በአሜሪካ ጎዳናዎች ሁሉ የቅዱስ ጊዮርጊስን ታሪክ፣ ክብር እና ፍቅር በዝምታ ትናገራለች፤ለጠየቋት ሁሉ መልስ ትሠጣለች።

✌️ይህ ቀለም ብቻ አይደለም፣ ይህ መለያ ብቻ አይደለም፣ይህ በተግባር የተገለጸ የማይጠፋ ዕውነተኛ የክለብ ፍቅር ማሳያ ነው።

✌️ጊዮርጊስ ለዴቭ ሳንጃው ክለብ ብቻ አይደለም፤ ማንነቱም፣ ኩራቱም ፣የሕይወቱ አካልም መሆኑን በተግባር አሳይቷል ዴቭ ሳንጃው በሀገረ አሜሪካ።✌️✌️

Photos from ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል's post 10/07/2026

ከተከበሩ ታላላቅ ሠዎች ጋር በUS

10/07/2026

🔴ቆይታ ከታዬ ወግደረስ ጋር...ቆይታ ከታዬ ወግደረስ ጋር...

🔴የደግነት ጥላ፣ የቸርነት ምሰሶ፣ የብዙዎች ተስፋ፣መጠለያና መጽናኛ፤

🔴 የልግስናህ ብርሃን ለብዙዎች ሕይወት ተስፋ ሆኖ ይበራል። ስሙ ከመልካም ሥራው ጋር ለዘላለም ከሚታወሠው ታዬ ወግደረስ ጋር ቆይታ

08/07/2026

♦️ሙሉጌታ ወልደየስ....ሙሉጌታ ወልደየስ....ሙሉጌታ ወልደየስ....
በተለይ ለ #ሀትሪክስፖርትኦፊሺያል

📌1981 ዓ.ም የኢትዮጵያ እግር ኳስ የማይረሳው አንድ አሳዛኝ ታሪክ አስታውሶን ይኖራል፤

📌በልዩ ተሠጥኦው፣በአስደናቂ የጨዋታ ብቃቱ ለሀገሩ ትልቅ ተስፋ የነበረው ቁመተ መለሎው፣7 ቁጥር ለባሹ፣አመለሸጋው ሙሉጌታ ወልደየስ የህይወቱንና የእግር ኳስ ጉዞውን የቀየረውን ዘግናኝ ጉዳት በተጠቀሠው ዓመት 1981 ዓ.ም ለመቀበል ተገደደ።

📌ያንን አስከፊ፣አስደንጋጭ አጋጣሚ 37 ዓመታት በትዝታ ፈረስ ወደ ኋላ ጋልቦ ላስታወሠ ኹነቱ ይሄን ያህል ዓመታትን እንክት አድርጎ የፈጀ ሳይሆን ዛሬ የተፈጠረ ያህል አይረሳውም፤በቁጭት ስሜት ውስጥ ገብቶም ያስተውሠዋል፤

📌ከማላዊ ብ/ቡድን ጋር በነበረው የወዳጅነት ጨዋታ ከግብ ጠባቂው ጋር ተጋጭቶ ሀገር ትልቅ ህልም ያኖረችበት ወጣት ተጫዋች በአንድ አፍታ ከባድና የከፋ ጉዳት ሲወድቅበት ማየት ልብን ይሠብራል፤ጉዳቱ እሱን እስከዘላለሙ ከእግር ኳስ ውጪ እንደሚያደርገው መታወቁ ደግሞ ለክለቡ፣ለመላው የስፖርት ቤተሠብ ከአእምሮ መቼም የማይጠፋ ህመምም ሆኖም ይቀራል።

📌 በቅጡ እንኳን ተጫውቶ ሳንጠግበው የተለየን ሙሉጌታ ወልደየስ ከዚህ ከጉዳቱ ጋር በተያያዘ ብቻ ስሙ ከፍ ብሎ ሲነሳ ቢደመጥም ሙሌ ግን በጉዳቱ ብቻ አይገለፅም።

📌7 ቁጥር ለባሹ፣ቁመተ መለሎው ኮከብ በጥንካሬው፣በትህትናው፣በትልቅ ስብዕናው፣ለሀገሩ ባበረከተው የማይረሳ ውለታው እና በተለይ ኢትዮጵያ ቡና ዛሬ ለደረሠበት ደረጃ መሠረት ከጣሉት ጀግኖች አንዱ ሆኖ ስሙ ሲዘከር ከፍ ብሎ ሲነሳም ይኖራል።

📌ዛሬ ያንን የክብር ጉዞ፣ያንን ፈተና፣ያንን ህመሙንና የኢትዮጵያ ቡና(በቀድሞ አጠራሩ የቡና ገበያ) ቆይታውን ሊያጋራን ከፊታችን የቆመው ሙሉጌታ ወልደየስ የሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል እንግዳ ሆኖ ቀርቧል።

📌ሙሌ ከማላዊው ግብ ጠባቂ ጋር የገጠመው ጉዳት በሙሌ እግር መሠበር ብቻ አላበቃም የብዙ ደጋፊዎችና የስፖረት ቤተሠቦች ልብንም ጭምር አብሮ ተሠበረ እንጂ፤

📌በዚህ ልብ ሠባሪ ሂደት ውስጥ ያለፈው 7 ቁጥር ለባሹ፣ አይረሴው፣አመለሸጋውን ሙሉጌታ ወልደየስን አሜሪካ አርሊንግተን አካባቢ አግኝቼው ትናንትን በዛሬ መነፅር እንዲያስቃኘን #የሀትሪክስፖርትኦፊሺያል እንግዳ አድርጌዋለሁ።

📌በቆይታችን ስለ ኢትዮጵያ ቡና አገባቡ፣ስለደጋፊው፣ሶስት የተለያዩ ዋንጫዎችን ከኢት.ቡና ጋር ስላነሳበት አጋጣሚ፣ስለ ሴካፋ ዋንጫና በሽልማት ያገኙትን ገንዘብ ምን ላይ እንዳዋለው፣ማንን እንደሚያደንቅ፣ስለ ብ/ቡድንና በሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከ #ሀትሪክሰፖርትኦፊሺያሉ ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ ጋር በስልጣኔ ጣሪያ በነካችው ሀገር አሜሪካ ያደረጉት ቆይታ ከዚህ በታች ቀርቧል፣ተከታተሉት፣ሃሳባ፣አስተያየት ስጡበትም ግብዣችነ።

08/07/2026



🔴ከሙሉጌታ ወልደየስ ጋር ከአሜሪካ ከደቂቃዎች በኋላ ይጠብቁን

🔴 በቀጥታ ከአሜሪካ Colombia Pike አካባቢ የሚገኘው ሜዳ የኢትዮጵያ ሬስቶራንት ውስጥ ከጀግናው የኢትዮጵያ ቡናና የኢትዮጵያ ብ/ቡድን ተጫዋቾች አንዱ ከሆነው ሙሉጌታ ወልደየስ ጋር የቀጥታ( )ቃለ-ምልልስ ይኖረናል ተከታተሉን።

🔴በኢትዮጵያ እግር ኳስ ከማይረሱ ጀግና ተጫዋቾች አንዱ የሆነው የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና ባለውለታ ሙሉጌታ ወልደየስ አሜሪካን ሀገር ተገናኝተን ከጥቂት ደቂቃ በኃላ የሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል እንግዳዬ ሆኖ በቀጥታ ይቀርቧል።

🔴ሙሌ ከማላዊ ጋር በነበረ የወዳጅነት ጨዋታ በደረሠበት ጉዳት የእሱ የጨዋታ ዘመን ብቻ ሳይሆን የሀገር ተስፋንም ደበዘዘ፣ በዚያ ቅጽበት በደረሠበት ጉዳት የሙሉጌታ እግር ብብቻ አልነበረም የተሠበረው፤ የብዙ ደጋፊዎች ልብም አብሮ ተሠብሯል፤
በእነዚህና ሳንጠግበው በጉዳት ያጣነው ጀግናው ልጃችን ሙሉጌታ ወልደየስ ዙሪያ የቀጥታ ውይይት ይኖረናል ይጠብቁን።

📌ጥያቄ አስተያየት ካላችሁ በፌስ ቡክ ገፃችን ይላኩሉልን

Photos from ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል's post 08/07/2026

🔴ታሪኩ ጁሃር ለቂርቆስ ለገሃር የጤና ስፖርት ማህበር ላበረከተው አስተዋጽኦና ድጋፍ ተበርክቶለታል

🔴በጨርቆስ ከመጡበት አይደራደርም፣ለጨርቆስ ያለው ልብም በጣም ስስ ነው፤ግን ደግሞ እንደ ሀገር በተለይ ለቅዱስ ጊዮርጊስና ለሀገር ባለውለተኞች ራሱን አሳልፎ የሚሠጥ ነው፤

🔴ያልኖረበትን ዘመን ጀግኖች በማክበር፣ዕውቅና በመስጠትና በተለያዩ ውድድሮች በመዘከር የሚያክለው የለም፤የቅዱስ ጊዮርጊስ የልብ ደጋፊ ቢሆንም ለሀገሩ ውለታ የዋለውን የኢትዮጵያ ቡናው ድንቅ ተጫዋች ሙሉጌታ ወልደየስ ለሀገር ያበረከተውን ውለታ አስታውሶ ዕውቅና ለመስጠት ሁለቴ አላሠበም፤

🔴የ10ኛ አፍሪካ ዋንጫ ባለቤቶችንም "በጨዋታ ዘመናችሁ ለሠራችሁት በጎ ስራ እናመሠግናችኋለን"በማለትም በአደባባይ በመሸለም፤ታላቁን አሠልጣኝ አስራት ኃይሌንና ጀግናውን አጥቂ ሙሉጌታ ከበደን ሁለቱም የእግር ኳሱ ኮከቦች ምንም እንኳን ህይወታቸው ቢያልፍም በሠሩት ታላቅ ስራ እንዲታወሱ የመታሠቢያ ውድድር ጭምር በማዘጋጀትና ስማቸው ከፍ ብሎ እንዲጠራ በማድረግ ውለታ በል አለመሆኑን በተደጋጋሚ ያሳየ ብዙ የሠራ ግን ያልተነገረለት ጀግና ነው፤ታራኩ ጀዋር።

🔴ታራኩ ጀዋር ከላይ ከተዘረዘረው በተጨማሪ ለቂርቆስ ለገሃር የጤና ስፖርት ማህበር ላበረከተው አስተዋጽኦና ድጋፍ በ43ኛው የኢትዮጵያ የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ፕሮግራም በሚኒሶታ በተገኘበት ሠዓት የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል፤በአደባባይ ዕውቅናም ተስጥቶታል ።

🔴አቶ ታሪኩ ጀዋር የምስጋና ምስክር ወረቀቱን በሚኒሶታ ግዛት በአካል በመገኘት በአቶ ሳሙኤል መንገሻ አማካኝነት ተበርክቶለታል ።

🔴ታሪኩ ጀዋር የአንተ በጎ ተግባር ፣ የአንድነት እና የኃላፊነት ምሳሌ ሆኖ ለሌሎች መነሳሳት ሆኗል። በዚህ የተከበረ አገልግሎትህና ለሀገር ባለውለተኞች ላበረከትከው ታሪክ የማይረሳው አስተዋፅኦ የእውቅና ሰርተፊኬትና ክብር በማግኘትህ ክብር ይገባሃል።

Photos from ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል's post 07/07/2026

♦️ጉዞአችንና ጉብኝታችን አልተጠናቀቀም፤ከሚኒሶታ+ቺካጎ+ኦሀዮ ኮሎምበስ=በመጨረሻም ዋሽንግተን ዲሲ

♦️ምሽት እንግዶቹን በልባዊ ፍቅር ወደ ቤቱ ያስገባው የሎጥ ታሪክ በኦሀዮ ኮሎምበስ

✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል) ከኦሀዮ ኮሎምበስ

♦️ከሚኒሶታ VICKING LAKES HOTEL የተጀመረው ጉዞአችን ከቺካጎ ጉዞአችን የተፈጥሮ ውበት፣ ታሪክ፣ ሥነ-ጥበብ እና ዘመናዊ የከተማ ሕይወትን በአንድ ላይ ወደ ምታቀርበው ወደ ኦሀዮ ኮሎምበስ ሆኗል፤የወዳጃችን አሠፋ ክፍሌ ቤተሠቦች(የታናሽ እህቱ ቤት) ሁለቱም ባልና ሚስት ዶክተሮች ሠዓት እላፊ እኩለ ሌሊት ብንመጣም የፍቅር እጃቸውን ዘርግተው በፍቅር ተቀብለው የማትረሳ ሌሊት በእነዚህ ሠው እንደ ምግብ በራባቸው ዶክተሮች ቤት አሳልፈናል።

♦️በዛ ውድቅት ሌሊት በራችሁን ስናንኳኳ በደስታ ስሜት ውስጥ ሠምጣችሁ፣ የተቀበላችሁበትን ፍቅርና ክብር ስናስብ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ምሽት እንግዶቹን በልባዊ ፍቅር ወደ ቤቱ ያስገባው የሎጥ ታሪክ ድቅን ብሎብናል ።

♦️Dr Yeshiareg Kifle,Dr Steven Vincent እና Ms Victoria Vincent በዕለቱ ቤታችሁን ብቻ ሳይሆን ልባችሁንም ከፍታችሁልን ያቀረባችሁልን እራት ስጋችንን አጠገበ፣ ያሳያችሁን ፍቅር ግን ነፍሳችንን አረካ።

♦️ይህ የኢትዮጵያዊ ወገናዊነትና የክርስቲያናዊ ፍቅር ውብ ምስክር ሆኖ ለዘላለም በልባችን ይኖራል፤ፈጣሪ ያሳያችሁንን ፍቅር በበረከት ይመልስላችሁ።

ፎቶ;(ከግራ ወደቀኝ)Dr Yeshiareg Kifle፣አሠፋ ክፍሌ፣Ms Victoria Vincent፣ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ፣ኮች ኤልያስ እንዳለ፣Dr Steven Vincent፣የሀገር ኩራት የሆነው ኢንተርናሽናል አርቢትር በአምላክ ተሠማ እና በዕድሜው ትንሽ በአስተሳሰቡ በጣም ትልቅ የሆነው ወጣት ነፃነት ምህረቴ

06/07/2026

በኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ ስም እናመሰግናለን።

On behalf of ESFNA we want to say thank you!

Photos from ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል's post 05/07/2026

🔴ለስምንት ቀናት እቅፍ ድግፎ አድርጎ ምቾትን ሲያዘንብብን የነበረውን የሚኒሶታውን Omni Viking Lakes Hotel በጠዋት ተሠናብተን በአሁን ሠዓት ቺካጎ ገብተናል

🔴በአስደናቂ የሕንፃ አርክቴክቸር፣ ሕያው በሆኑ ጥበባት እና አስቂኝ ትዕይንቶች፣ በስፖርት ታሪክ እና በአስደናቂ የምቾት ምግቦቿ፣በሚቺጋን ሐይቅ ዳርቻ ላይ በተቆረቆረችው፣ የዓለም ትልቁ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ የትውልድ ቦታ በሆነችው፣ እንደውሃ በምትፈሠውና የ2026 ስሪት በሆነችውና ኮች ኤልያስ እንዳለ(የመጀመሪያ ፕሮጀክት በመገናኛ መስራች)በሚነዳት Mazda መኪና ተንፈላሠን Chicago ከተማ ደርሠናል።

🔴ሀገሩን ከእግር እስከራሱ እየጎበኘን ወደ መጨረሻ መዳረሻችን (Destination)ዋሽንግተን ዲሲ መፍሠሳችን ይቀጥላል

🔴ፎቶ:ከግራ ወደ ቀኝ እጅግ የምናከብረው የጊዮርጊስ ባለውለታ አሠፋ ክፍሌ፣ኮች ኤልያስ እንዳለ፣ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ፣ሀገሩን በአለም አቀፍ መድረክ ያኮራው ኢንተርናሽናል አርቢትር በአምላክ ተሠማ እና የሜሪላንድ ቡድን ግብ ጠባቂና(Co pilot) ነፃነት ምህረቴ።

📌አስገራሚው ነገር ፎቶ በማንሳት የተባበረን በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንደሚሠራ በነገረን ፓኪስታናዊ መሆኑ ሌላኛው የቺካጎ ትውስታችን ይሆናል

05/07/2026
Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Address


Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 00:00 - 23:01
Sunday 00:00 - 23:00