23/06/2026
አቶ ዮናታን ዲቢሳ መጽሐፋቸውን በአፋን ኦሮሞ ተርጉመው ለንባብ አበቁ
አቶ ዮናታን ዲቢሳ የቀድሞ የኦህዴድ መስራቾች መካከል አንዱ ሲሆኑ፣ በኋላም ለኦሮሞ ህዝብ መብትና ለእውነተኛ ፌዴራሊዝም እንዲተገበር ትግል ለማድረግ ወደ ጀርመን ተሰደው ነበር። ከዚያም በኤርትራ የኦነግ ትግልን በመቀላቀል ከኦነግም ተለያይተው ለ15 ዓመታት በትግል ውስጥ ቆይተዋል።
የረጅምና መራራ የትግል ጉዟቸውን የሚያስታውሰውን “ረጅምና መራራ ትግል” የተሰኘ ግለ ታሪካቸውን በአፋን ኦሮሞ በመተርጎም “QABSOO DHEERAA fi HADHAAWAA” በሚል ርዕስ ለንባብ አብቅተዋል።
መጽሐፉ የባለግለ-ታሪኩን የፖለቲካ ህይወት፣ የስደት ቆይታ፣ የትግል ልምድ እና በተለያዩ ወቅቶች ያጋጠሙትን ተሞክሮዎች የሚያስቃኝ መሆኑ ተገልጿል።
23/01/2026