EAS

EAS

Share

EAS በብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ላይ ተዘጋጅቶ የሚቀርብ የስፖርት ፕሮግራም ሲሆን ዘውትር አርብ ምሽት ከ 3፡00 – 5፡00 እና እሁድ ከሰአት ከ 6፡00-7፡00 የሚደመጥ ነው፡፡

02/08/2026

386

ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ!

የአካል ብቃት፣ጤናማ አመጋገብ፣በቂ እረፍት ..

ዕለተ እሁድ ሀምሌ 26/2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል።

የዛሬ ቆይታችን ከተጋባዥ እንግዶች ጋር ይሆናል።ልምዳቸውን ያካፍሉናል።

ስለ ጤናማ የኑሮ ልምምዶች፣አመጋገብ እና የአካል ብቃትን ጨምሮ በሌሎች ሀሳቦች ላይ ቆይታ ይኖረናል።

የሊግ ውድድሮች ሊጀመሩ ጥቂት ሳምንታት ቀርተውታል።ክለቦችም የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን እያደረጉ ይገኛሉ።

👉 ቶተንሀም 2-1 ቼልሲ

👉 አርሰናል 4-1 ጂሮና

👉 ማን ዩናይትድ 2-1 አትሌቲኮ ማድሪድ

👉 ኖርጋርድ ወደ ኤቨርተን ለመዘዋወር ተስማምቷል።ይህም የጉማሬሽ ወደ አርሰናል የሚያደርገው ዝውውር ይበልጥ መቃረቡን የሚያመለክት አይሆንም?

የዛሬ ጭምጭምታዎች

👉 ማን ዩናይትድ ማይልስ ልዊስ ስኬሊን ለማዘዋወር ሁኔታዎችን እያጤነ ነው።

👉 ሲቲ ፔድሮ ኔቶ ላይ አይኑን ጥሏል።

በነዚህ እና በሌሎች ጉዳዮችን ጨምራችሁ ሀሳባችሁን ኮሜንት ሳጥን ውስጥ አካፍሉን?

- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

31/07/2026

385

Delap's Dramatic Drop (3D)

ኢትዮ-አዲስ ስፖርት በዕለተ አርብ ሐምሌ 24/2018 የእኛና የእናንተ መሰናዶ ከምሽቱ 3:00-5:00 አየር ላይ ትውላለች።

በዝውውር መስኮቱ የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ ካሉ የፕሪምየር ሊግ ክለቦች አንዱ ቼልሲ ነው። ሰማያዊዎቹ በተለያዩ ስፍራዎች ራሳቸውን እያጠናከሩ ሲገኙ የአጥቂ መስመራቸውም ከተጠናከሩ ቦታዎቻቸው መካከል ይጠቀሳል። አንጋፋው ዳኒ ዌልቤክ የቡድኑ አዲስ ፈራሚ ሲሆን ኒኮላስ ጃክሰንን ጨምሮ ሌሎች ተጫዋቾችም በዚሁ ስፍራ የሚገኙ አማራጮች ናቸው። በዚህ ሁሉ መካከል ሊያም ዴላፕ ተረስቷል። ከአንድ አመት በፊት እንደእንግሊዝ እግር ኳስ ተስፋ ይታይ የነበረው ዴላፕ አሁን የሚገኝበት ሁኔታና የነገሮች መገላበጥ አሳዛኝ ነው። በዛሬው መሰናዶአችን በዋናነት በዚህ ዙሪያ እናደርጋለን።

✅የተጫዋቾች ዝውውር ጉዳይ የወቅቱ ትልቅ ርዕስ ነው።ሆኖም ሰሞኑን ገበያው ትንሽ ቀዝቀዝ ያለ ይመስላል። ምክንያቱ ምን ይመስላችኋል?
✅ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበርና ፊፋ ተፋጥጠዋል። ምክንያቱ ደግሞ "የዓለም ዋንጫ ለገበያ የሚቀርብ ሸቀጥ አይደለም!" የሚል ነው። የUEFA ሀሳብ ትክክል አይመስላችሁም?
✅የሊግ ውድድሮች ለመጀመር ተቃርበዋል።ምን ያህል ጉጉት አድሮባችኋል?

በእነዚህና በሌሎች ስፖርታዊ ጉዳዮች ሀሳባችሁን እያጋራችሁ ጠብቁን።

- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

26/07/2026

384

የዝውውር ዝምታ በሊቨርፑል

ዕለተ እሁድ ሀምሌ 19/2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል።

የአውሮፓ የ 2026/2027 የሊግ ውድድሮች ሊጀመሩ አንድ ወር ብቻ ቀርቶታል።

ክለቦችም የቅድመ ውድድር ጊዜያቸውን በልምምድ፣በአቋም መፈተሻ ጨዋታዎች እንዲሁም ክፍተቶቻቸውን ለመድፈን በዝውውሩ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የእንግሊዙ ሊቨርፑል ግን እስከ አሁን ድረስ በንቃት ተሳትፎ እያደረገ አይገኝም።

ምንም እንኳን የዝውውር መስኮቱ ክፍት ቢሆንም የሊጉ ጅማሮ መቃረብ ተከትሎ ክለቡ በዝውውር ላይ መቀዛቀዙ ደጋፊዎችን አሳስቧል።

ሊቨርፑል ለምን ዝምታን መረጠ?

👉 ፔዤ ተጠባባቂ ተጨዋቾቹን ለሌሎች ክለቦች ማከፋፈሉን ቀጥሏል።ጎንካሎ ራሞስ ወደ ሚላን፣ ካንግ ኢን ሊ ወደ አትሌቲኮ ተቀላቅለዋል።

👉 ቪኒ፣አልቫሬዝ እና ጉማሬሽ ከ አርሰናል ጋር ስማቸው የተነሱ ተጨዋቾች ናቸው።መድፈኞቹ ማንን ማስፈረም ይችላሉ?

👉 ፓልመር፣ጇ ፔድሮ፣ሞርጋን ሮጀርስ፣ስቲቫኦ፣ፔድሮ ኔቶ እና ሌሎች።ቼልሲ ጠንካራ የአጥቂ ስብስብ ያለው ቡድን ነው ማለት እንችላለን?

በነዚህ እና በሌሎች ጉዳዮችን ጨምራችሁ ሀሳባችሁን ኮሜንት ሳጥን ውስጥ አካፍሉን?

- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

24/07/2026

383

የርገን ክሎፕ- አዲሱ የጀርመን አለቃ

ኢትዮ-አዲስ ስፖርት በዕለተ አርብ ሐምሌ 17/2018 የእኛና የእናንተ መሰናዶ ከምሽቱ 3:00-5:00 አየር ላይ ትውላለች።

በዓለም ዋንጫው አሳፋሪ ቆይታ የነበራት ታላቋ የእግር ኳስ ሀገር ጀርመን ከገባችበት የውጤት ማጣት አዘቅት ያወጣኛል ብላ ያሰበችውን ባለግርማ ሞገስ የርገን ክሎፕ ዛሬ በይፋ ቀጥራለች። በሊቨርፑልና በዶርትሙንድ በሰሩት ተአምር ከፍተኛ ግምት የሚሰጣቸው ክሎፕም ስራውን ለመቀበል ሳያንገራግሩ ለ 2030 የዓለም ዋንጫ የታለመውን ፕሮጀክት ተቀብለዋል። በዛሬው መሰናዶአችን በዋናነት በዚህ ዙሪያ እናደርጋለን።

ከአለም ዋንጫው መጠናቀቅ መልስ የተጫዋቾች ዝውውር ጉዳይ ተፋፍሟል።
✅ አርሰናል ብሩኖ ጊማሬሽን ማስፈረሙ የሚቀር አይመስልም።
✅ቼልሲ ላክሮአን ከፓላስ መንትፏል።
✅ሲቲ ወጣቱ አዩብ ቡአዲ ላይ አይኑን ጥሏል።
✅የዘንድሮው ዩናይትድ ድምፁን አጥፍቶ እየሰራ ነው።
✅ሊቨርፑል እስካሁን ሳላህን አልተካም።

የዝውውር ገበያውን እንዴት እያያችሁት ነው? በእነዚህና በሌሎች ስፖርታዊ ጉዳዮች ሀሳባችሁን እያጋራችሁ ጠብቁን።

- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

19/07/2026

382

ቆይታ ከ ተጋባዥ እንግዳ ጋር

ዕለተ እሁድ ሀምሌ 12/2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል።

የአለም ዋንጫ ፍፃሜ ዛሬ ምሽት ይከናወናል።አርጀንቲና እና ስፔን ለሌላ ክብር ፊትለፊት ይፋጠጣሉ።

የልዊስ ዴላ ፎንቴ እንደ ቡድን የሚንቀሳቀሰው ስፔን ጠንካራ አልሸነፍ ባይነትን መገለጫው ካደረገው አርጀንቲና

የሮድሪ እና ጓደኞቹ የኳስ ፍሰት ከ ፓራዴዝ እና ጓደኞቹ የሜዳ ላይ ተጋዳይነት

አይን ውስጥ የሚገቡት ሜሲ እና ያማል?

ከወር በላይ ቆይታ በነበረው የ 48 ሀገራት ውድድር ዛሬ ከሁለቱ አንዱ በአሸናፊነት ይሞሸራሉ።አርጀንቲና ወይስ ስፔን?

እንግሊዝ እና ፈረንሳይ በጋራ 10 ጎሎችን አስቆጥረው ደረጃቸውን ለይተው ወጥተዋል።

ኪሊያን ሁለት ጎሎች አስቆጥሮ ከሜሲ ፊት ተቀምጧል።አሁን የምንግዜው የአለም ዋንጫው ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ እርሱ ነው።

ዛሬ ቆይታ የምናደርገው ከእንግዳ ጋር ይሆናል።

ማን አሸናፊ ይሆናል?

ሀሳባችሁን ኮሜንት ሳጥን ውስጥ አካፍሉን?

- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

17/07/2026

381
የአድማጮች ቀን በዓለም ዋንጫው ዙሪያ
ኢትዮአዲስ ስፖርት በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 የአርብ ምሽት መሰናዶ ከምሽቱ 3:00-5:00 አየር ላይ ይቆያል።

ከረጅም ሳምንታት ቆይታ በኋላ EAS በዕለተ አርብ የእኛና የእናንተ መሰናዶ ተመልሷል። በአለም ዋንጫ ጅማሮ ምክንያት ሳይተላለፍ የቆየው ፕሮግራማችን ሲመለስ የዓለም ዋንጫው የፍፃሜው ጨዋታ ላይ ደርሶ ነው። እሑድ ምሽት በኒውዮርክ ሜትላይፍ ስታዲየም የአውሮፓ ሻምፒዮኗ ስፔን ከዓለም ሻምፒዮኗ አርጀንቲና ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ፍፃሜውን ያገኛል?

ዛሬ ለአድማጮች አብዛኛውን ክፍለ ጊዜ የምንሰጥበት ቀን ነው። ✅የዓለም ዋንጫውን እንዴት አያችሁት?
✅ግምታችሁ ምን ያህል ስኬታማ ነበር?
✅ማን ሻምፒዮን ይሆናል?
✅የትኛው ቡድን አስገረማችሁ?
✅የትኛው ቡድን ከጠበቃችሁት በታች አቋም አሳየ?

ሀሳባችሁን አጋሩን።

- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

12/07/2026

380

ጊልቤርቶ ሞራ ..
አሌሀንድሮ ጋርናቾ ..

ዕለተ እሁድ ሀምሌ 05/2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል።

የአለም ዋንጫው ወደ ወሳኝ ምዕራፍ መሻገሩን ተከትሎ በአለም ዋንጫ የተመረጡ ጉዳዮች ላይ እና የጋርናቾ ከቼልሲ ለመልቀቅ መቃረብ የዛሬ ጉዳያችን ነው።

እንደ አርጀንቲና እያንዳንዱ የጥሎማለፍ ጨዋታዎች የተፈተነ ቡድን የለም ማለት ይቻላል።

አነጋጉ ላይም በስዊዘርላንድ ተፈትኖ መጨረሻ ላይ ግን አሸንፈው ወጥተዋል።አርጀንቲናዊያን ተፋልመው ማሸነፍን ለምደውበታል።

ቀጣይ ከ እንግሊዝ

በውድድሩ ሁሉም የሚስማማበት የፈረንሳይ ያልዋዥቀ አቋም ነው።በመንገዱ ያሉትን እየሰባበረ ግማሽ ፍፃሜ ተገኝቷል።

ቀጣይ - ባለፈው የአውሮፓ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ላይ ካሸነፈቻት ስፔን

ማን ለፍፃሜ ይበቃል?

በአለም ዋንጫው ያየነው ወጣቱ የሜክሲኮው ጊሊቤርቶ ሲልቫ ላይ ታላላቅ ክለቦች አይናቸውን ጥለዋል።

ጋርናቾ ከቼልሲ ውጪ ብሎ ማንችስተር ዩናይትድን ለቆ ሰመያዊዎቹን በተቀላቀለ በአንድ አመቱ ክለቡን ሊለቅ ነው።

ወጣቱ ባለ ተስፈኛ የእድገት ጉዞው እያሽቆለቆለ ይመስላል።

👉 ጁድ ቤልንግሀም 6ኛ የአለም ዋንጫ ጎሉን አስቆጥሯል

👉 የኢምቦሎ አሳፋሪ ዳይቭ

👉 የአልቫሬዝ ድንቅ ጎል

ሀሳባችሁን ኮሜንት ሳጥን ውስጥ አካፍሉን?

- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

05/07/2026

379

የአለም ዋንጫ ጉዳዮች ..

ዕለተ እሁድ ሰኔ 28/2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል።

የአለም ዋንጫው ወደ ወሳኝ ምዕራፍ መሻገሩን ተከትሎ በአለም ዋንጫ የተመረጡ ጉዳዮች ላይ ዛሬም ቆይታ እናደርጋለን።

ወደ ሩብ ፍፃሜ ለማለፍ የሚደረጉ ጨዋታዎች ተሟሙቀው ቀጥለዋል።ሞሮኮ እና ፈረንሳይ ከ 8ቱ ሀገራት ውስጥ ሁለቱ ሆነዋል።

ቀጣይ ደግሞ እርስበርስ ይፋለማሉ። ፈረንሳይ ከ ሞሮኮ

አንዷ አዘጋጅ ሀገር ካናዳ ወድቃለች።ለአሰልጣኙ ጄሺ ማርሽ ግን የተሻለው ቡድናቸው እንደነበር ያምናሉ።

የቡድናቸው ኮከብ ጆናታን ዴቪስ በጁቬንቱስ በየሳምንቱ አለመጫወቱ እንደጎዳው እየተደመጠ ይገኛል።

ለናንተ

👉 እንደተጠበቀው ያላገኛችሁት ወይንም ከተጠበቀው በላይ ያገኛችሁት ሀገር ማነው?

👉 የኮከብ ጎል አስቆጣሪ አሸናፊስ ማን ሆኖ ያጠናቅቃል?

👉 ሞሮኮ ፈረንሳይን ማሸነፍ ትችላለች?ከሆነ ለዋንጫ ትጠበቅ?

👉 የሜክሲኮ በሜዳዋ ጠንካራ መሆን ለእንግሊዝ ፈተና ይሆናል?

👉 ያልተወራላት ድምጿን ያጠፋችው ኮሎምቢያስ?

ሌሎች ትዝብታችሁን ጨምራችሁ በኮሜንት ሳጥን ውስጥ ሀሳባችሁን አካፍሉን?

- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

28/06/2026

378

የአለም ዋንጫ ጉዳዮች ..

ዕለተ እሁድ ሰኔ 21/2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል።

የአለም ዋንጫው የምድብ ጨዋታዎች ተጠናቀው ወደ ጥሎማለፉ የተሻገሩ ሀገራት ተለይተዋል።

32 ሀገራት ተጋጣያቸውን አውቀዋል።ብዙዎቹ ታላላቅ ሀገራት ቀለል ያለ የሚመስል ተጋጣሚ ደርሷቸዋል።

ኔዘርላንድ ከ ሞሮኮ ጋር የሚያደርጉት ፍጥጫ በትልቅነት የሚነሳ ነው።

ብራዚል ከ ጃፓንም ሳይዘነጋ

እኛም በተመረጡ የአለም ዋንጫ ጉዳዮች ላይ ቆይታ ይኖረናል

የለሊቱ አበይት ጉዳዮች እንዴት ነበሩ?

👉 የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን በተሰጥኦ የተሞላ ነገርግን ዋንጫ ለማንሳት ብዙ ስራ የሚፈልግ መሆኑ

👉 ሜሲ በ 3 ጨዋታ 6ኛ ጎሉ

👉 ዊሳ የኮንጎ አዳኝ ..

👉 የኦስትሪያ እና አልጄሪያ የመጨረሻ ደቂቃ ድራማዎች

እናንተስ ምን ታዘባችሁ?

በኮሜንት ሳጥን ሀሳባችሁን አካፍሉን?

- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

25/06/2026
Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Lideta
Addis Ababa