Champion lege new result

Champion lege new result

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Champion lege new result, Sports League, Addis Ababa.

29/04/2026

በአልጋ ላይ በሞት አፋፍ ላይ የነበሩ አንድ አዛውንት ዶክተራቸውን እንዲህ አሉት፦ "ዶክተር፣ አትጨነቅ። እንደምሞት አውቃለሁ። እዚህ መምጣት አልፈለኩም ነበር ግን እነሱ አመጡኝ። እባክህን ስለእኔ አትጨነቅ፣ ፀጉሬን ተመልከት፣ የለም። እኔ በጣም አርጅቻለሁ አንተ ግን ወጣት ነህ። ከህይወት ብዙ ተምሬያለሁ፣ ቅር ካላለህ ከመሞቴ በፊት ጥቂቶቹን እነግርለሁ።"

- የ4 ዓመት ልጅ እያለሁ ዓለም የእኔ እንደሆነች አስብ ነበር።
- 14 ዓመት ሲሞላኝ ዓለምን መግዛት ፈለኩ። በምድር ላይ ከኖሩ ታላላቅ ሰዎች አንዱ እሆናለሁ ብዬ አስብ ነበር።
- 21 ዓመት ሲሞላኝ ትልቁ ባለጸጋ መሆን ፈለኩ፣
- 25 ዓመት ሲሞላኝ ፍቅረኛ መያዝ ፈለኩ፣
- 40 ዓመት ሲሞላኝ ለሁሉም ጠቃሚ መሆን ፈለኩ።

"አሁን እዚህ ስሆን መሞት እፈልጋለሁ። እንግዲህ፣ በብዙ ጊዜያት ብዙ ነገሮችን ፈልጌ ነበር። ከሁሉም በላይ ደግሞ ደስተኛ መሆን ፈልጌ ነበር። ደስተኛ ለመሆን ምርጡ መንገድ ሌሎችን ማዳመጥ ነው ብዬ አስብ ነበር።"

"ዩኒቨርሲቲ ስገባ የእንስሳት ጥናት (Zoology) መማር ፈልጌ ነበር ነገር ግን ሁሉም ሰዎች ኢንጂነሪንግ እንድማር ነገሩኝ፣ ምርጥ ኢንጂነር እንደምሆን ነገሩኝ። ስለዚህ እነሱን አዳመጥኩ። የትምህርት ክፍያዬን የሚከፍልልኝ ሰው አልነበረኝም፣ መስራት እና ክፍያዬንም መክፈል ነበረብኝ። በሶስተኛ ዓመቴ ከትምህርቴ ጋር መጣጣም አልቻልኩም፣ ማቋረጥ ነበረብኝ። ስተወው እነዚሁ ሰዎች "የእንስሳት ጥናት መማር ነበረብህ!" አሉኝ።

- 28 ዓመት ሲሞላኝ ሁሉም ማግባት እንዳለብኝ ነገሩኝ። ሚስት እንደሚያስፈልገኝ ነገሩኝ። ስለዚህ እነሱን አዳመጥኩ፣ አገባሁ። ትዳሩን ከጀመርን ከ6 ዓመት በኋላ ባለቤቴን ከጎረቤቴ ጋር ተኝታ ያዝኳት። ለምን ብዬ ጠየቅኳት እሷም በጥፊ መታችኝ። ተናደድኩኝ እና ምንም አላልኩም። በሚቀጥለው ቀን ከስራ ስመለስ ልጆቼን ይዛ ሸሽታ ነበር፣ አሁን ብቸኛ ሆኜ እየሞትኩ ነው።

- "በ40 ዓመቴ ትልቅ ኮንትራት ሥራ አገኘሁ። ስሜ በዜና ላይ ወጣ። በሚቀጥለው ቀን ሁሉም ጓደኞቼ እና ቤተሰቦቼ ቤቴ ነበሩ፣ ሁሉም ከባድ ችግር እንደነበረባቸው ነገሩኝ። በአንድ ሳምንት ውስጥ ገንዘቡን እንመልሳለን በሚል ቃል ስለገቡ ለእነሱ ሰጠኋቸው። ነገር ግን ቃል እንደገቡት ገንዘቡን ለመመለስ ፈቃደኛ ስላልሆኑ ኮንትራቱን ማጠናቀቅ አልቻልኩም። ስለዚህ ለ6 ዓመታት ታሰርኩ። እስር ቤት ቆይቼ ወጣሁ። ስወጣ እነዚያ ሰዎች አልነበሩም።"

"በዚህ ሁሉ ጊዜ የሰራሁት አንድ ስህተት አለ። አሁን ለእኔ ግልጽ የሆነልኝ። ስለሱ ልንገርህ። ራሴን ለማዳመጥ ፈቃደኛ አልነበርኩም። የራሴን ማንነት ችላ ብዬ ሌሎችን አዳምጥ ነበር። አሁን እዚህ ስሆን ከእኔ ጋር ያለው ብቸኛው ሰው ራሴ ነኝ።"

"እንግዲህ፣ ሌሎችን ማዳመጥ በጣም ጥሩ ነው። ከሌሎች ምክር መጠየቅ በጣም ጥበብ ነው። ነገር ግን የራስን ማንነት ችላ ማለት በጣም አደገኛ ነው። ለልብህ ትኩረት ለመስጠት እምቢ ማለት በጣም በጣም አደገኛ ነው።"

"ዛሬ ማታ ወደ ቤትህ ስትደርስ ቁጭ በልና አንድ ብርጭቆ ውሃ ጠጣ። ከፈለክ አይንህን ጨፍን ወይም ከፈለክ ክፈተው፣ ከዚያም ከራስህ ጋር ተነጋገር፣ ከራስህ ጋር ተከራከር። ብቻህን መንገድ ላይ መሄድ እና ስትራመድ ከራስህ ጋር ማውራት መጀመር ትችላለህ።"

ከፈጣሪህ ቀጥሎ ራስህን አዳምጥ። አሁን ለአንተ ትርጉም ላይሰጥ ይችላል ነገር ግን ሁልጊዜ የነገርኩህን አስታውስ፣ ራስህን ማዳመጥን ተማሩ።

አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ ማድረግን አትርሱ

ገፅ የተወሰደ

02/09/2024
Photos from Hule Arsenal ሁሌ አርሰናል's post 02/09/2024
02/09/2024

The Gunners

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address


Addis Ababa