19/07/2026
ከ170 ሚሊየን በላይ ህዝብ ለሁለተኛ ሀገሩ አርጀንቲና ሲል አዉራጎዳናዎች ለማጥለቅለቅ ነገን እየጠበቀ ይገኛል ...
አሁን የማስነብባቹ ታሪክ ስለ ኮከቡ ዉልደት ከተማ ሮዛሪዮ አይደለም ስለ ቦነስ አይረስም ሆነ አርጀንቲና ዉስጥ ስለሚገኙ ከተማዎች አይደለም በደቡብ ኤዥያ ስለምትገኘዉ ባንግላዴሽ ነዉ።
ያቺ ሰፊ መሬት የያዘቿ 90% ሙስሊም ህዝባ ያላት ሲሆን ቀሪዎች 10% ያህሉ በብዛት ሂዱ እና የተወሰነ ክሪስቲያን ያለባት በሙሀመድ አብዱል ሀሚድ የምትመራዋ እና በአርጀንቲናዉያን ፍቅር የቀለጠ ልብ ያላዉ የባንግላዴሽ ህዝቦች።
አርጀንቲና በአለም ዋንጫዉ የምድብ ጨዋታዎች ሲኖሩባት ሀገሪቷ ዉስጥ ያሉ ከተማዎች ቀድመዉ በአልባሴሊስቴዎቹ ባንዲራ ያሸበርቃሉ ዋና ከተማዋ ዳካር ላይ የአርጀንቲናን መለያ ያለበሰ ይገዳል የተባለ ይመስላል ሁሉም በደቡብ አሜሪካዋ ሀገር መለያ ደምቀዉ ይታያሉ።
ከዜና አንባቢ እስከ ፀጉር ቆራጭ ከሱቅ ሻጭ እስከ ገዢ ከህፃን እስከ ትልቅ ድረስ በአርጀንቲና መለያ አምረዉ እና አሸብርቀዉ ጨዋታዉን ይከታተላሉ።
ከዚህ በላይ ደግሞ በአለም ዋንጫዉ ጨዋታዎች ላይ በአርጀንቲና ጨዋታ ላይ ከተሸጡ ቲኬቶች መካከል አብዛኛዎቹ የተገዙት በባንግላድሽ ሰዎች መሆኑ ምን ያህል ለቡድኑ ፍቅር እንዳላቸዉ ያሳያል።
ባንግላድሽ ለረዥም ጊዜ በቀኝ ግዛት የተገዛች ሀገር ነበረች በ1940 ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ደግሞ በእንግሊዝ የቀኝ ግዛት ስር የወደቀችዉ በወቅቱ 1986 አለም ዋንጫ በሀገረ ሜክሲኮ ነበር የተዘጋጀዉ በፍፃሜዉ ጨዋታ አርጀንቲና በማራዶና "Hand Of God " ተጠቅማ በማሸነፍ የዋንጫዉ ባለ ቤት በሆነችበት ወቅት የባንግላዴሽ ህዝቦችም እንግሊዝን ማሸነፍ እንጀሚችሉ ትልቅ ብርታት ሆናቸዉ።
በዚያዉ ዓመት ባንግላዴሽ ለአርባ ስድስት ዓመታት ከገዛቻት እንግሊዝ ስር ነፃ መዉጣቷን አወጀት የአርጀንቲና እና የባግግላዴሽ ወዳጅነትም ያኔ የጀመረ ነዉ።
ሊዮኔል ሜሲ በነገዉ ጨዋታ ከ45 ሚሊየን በላይ ስለሆኑት የአርጀንቲና ህዝቦች ሸክም ብቻ አይደለም ወደ ሜዳ ይዞ የሚገባዉ ከ180 ሚሊየን በላይ ህዝቦች የሚኖሩባትን የባንግላዴሽንም አደራ እና ሸክም እንጂ።
የአርጀንቲናው አሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒም በመግለጫዎቹ መካከል ስለ ባንግላዴሾች ሳያመሰግን እና ሳያወድስ ቆይቶ አያዉቅም እና በነገዉ ጨዋታ ደስታቸዉን ሙሉ ለማድረግ እንደሚሞክር ተናግሯል።