20/08/2026
የሰላም ሌሊት ይሁንላችሁ ንጉሳኖች !! ❤️🩹
ይህ ፔጅ ስለ ማንችስተር ዩናይትድ የሚወጡ መረጃዎችን ባማረ መልኩ የሚቀርብበት ቻናል ነው።
20/08/2026
የሰላም ሌሊት ይሁንላችሁ ንጉሳኖች !! ❤️🩹
20/08/2026
ተጨማሪ ምስሎች ❤️
20/08/2026
#𝐎𝐅𝐅𝐈𝐂𝐈𝐀𝐋
የክለባችን ተጫዋቾች የፕሪሚየር ሊግ ፎቶ !! 😍
20/08/2026
አንዳንድ ዝውውሮችን ከፈፀምን ሊኖረን የሚችለው የስኳድ ጥልቀት !!
በማጥቃት ረገድ ደረታችን ነፍተን አጥቂ አለን ብለን መናገር እንችላለን። ምርጥ የሚባሉ አጥቂዎች ስላሉንም ማለት ነው።
ነገርግን ተከላካይ በአሁኑ ዝውውር መስኮት ከተቻለ ወይም በጥር ዝውውር ላይ ግዴታ ያስፈልጋል።
ሁላችሁም እንደምታውቁት በተቃራኒ ቡድን ልንዳከምባቸው የምንችላቸው ግልፅ ክፍተት ልንሰጥ የምንችለው ይሄ ቦታ ላይ ብቻ እና ብቻ ነው።
INEOS በአሁኑ ክረምት ዝውውር፣ በጥር ዝውውር ወይስ በቀጣይ አመት ይሄን ድክመታችንን ይቀርፉታል?
የሁላችንም ጥያቄ ነው ።
የእናንተንም ሀሳብ ? 👇
20/08/2026
"ራሽፎርድ በጥሩ ብቃት ላይ ይገኛል። በሁኔታውም ደስተኛ ነው በጣም ንቁ/ቀልጣፋ ሆኖ እያየነው ነው፤ እንዲሁም ለጨዋታዎች ዝግጁ ነው።
ፊት መስመር ላይ (ግብ አግቢ ሆኖ) መጫወት ይችላል፤ ቀደም ሲልም አድርጎታል። የግድ የሚመርጠው ያ ቦታ ነው ባልልም ነገር ግን እዛ ቦታ ላይ ብቃቱ አለው።
በሁሉም የአጥቂ መስመር ላይ ያንን የመለዋወጥ እድል የሚሰጡን አጥቂዎች አሉን።
ሁሉንም በሚባል ደረጃ በጥቂቱ በተለያዩ ሚናዎች ተጠቅመንባቸዋል፤ እናም ይህ አማራጭ መኖሩ ለውድድር ዘመኑ በጣም አወንታዊ ነው።"
ማይክል ካሪክ
20/08/2026
"ፕሪሚየር ሊጉን ማሸነፍ? ማድረግ እንችላለን ወይም አንችልም ብልም ያን ያህል ለውጥ አያመጣም።
በጭራሽ አንችልም ብዬ አልልም፤ ነገር ግን እኔ ምንም ብናገር ወሳኙ ጉዳን ስራችን፣ ማከናወን የምንችለው ነገር እና ማሳካት እንችላለን ብለን የምናምነው ነገር ነው።
ባለፈው የውድድር ዘመን ያስመዘገብነው ጥሩ የውጤት ጉዞ ትልቅ መተማመን ይሰጠናል ብዬ አስባለሁ፤ ነገር ግን አዲስ የውድድር ዘመን መሆኑንም እናውቃለን።
ታላላቅ ነገሮችን ለማሳካት የሚያስችል አቅም አለን ብዬ አስባለሁ።
ታላላቅ ነገሮችን ማሳካት እንደምንችል ማመን አለብን።"
[ማይክል ካሪክ]
20/08/2026
ካሪክ፡ «የውድድር ዓመቱን መጀመር እና የጨዋታዎች ተከታትለው መምጣት በጉጉት የምጠብቀው ነው።
በቅድመ-ውድድር ዝግጅት ወቅት በሰራነው ሥራ በጣም ተደስቻለሁ፤ በጣም በጥሩ ሁኔታ እንደሄደ አስባለሁ። የመጀመሪያውን ጨዋታ ለማድረግም ጓጉቻለሁ።»
ካሪክ፡ «ለውድድር ዓመቱ ቀላል የሚባል መክፈቻ ጨዋታ የለም። ለሁለቱም ቡድኖች አስቸጋሪ ጨዋታ ነው። ከአዲስ አዳጊ ቡድን ጋር ከሜዳ ውጪ የሚደረግ ጨዋታ በጣም በጣም አስቸጋሪ ጨዋታ ነው።
ቀደም ሲል ተሞክሮው ስለነበረኝ ቅዳሜ ዕለት ምን እንደሚጠብቀን በደንብ አውቃለሁ። ስለዚህ ለእኔ ቀላል ጅማሮ አይደለም"
20/08/2026
ካሪክ የግራ መስመር ተከላካይ ስለማስፈረም
"ቡድኑን ለማጠናከር እየሰራን ነው ብዬ አስባለሁ። በእርግጥም እየሰራን ነው ያለነው፤ ሁኔታዎችን በአግባቡ በመጠቀም ነገሮችን ለማሻሻል እና ወደፊት ለመራመድ እየሞከርን ነው።
የዝውውር መስኮቱን ስንጀምር ከነበርንበት ይልቅ ጠንካራ ሆነን ለማጠናቀቅ እድሎችን በአግባቡ ለመጠቀም በሚገባ እየጣርን ነው። እስካሁን ባለው ሁኔታም በጥሩ መንገድ ላይ ነን ብዬ አስባለሁ።"
ካሪክ ስለተጋጣሚ:-
"ሀል? ወደ ፕሪሚየር ሊጉ በማደጋቸው ምክንያት በክለቡ ዙሪያ ትልቅ መነቃቃት አለ። ፈተናውን በደንብ እንረዳዋለን። በአእምሮም ሆነ በአካል ዝግጁ እንሆናለን።
ይህ ጨዋታ ምን እንደሚሰጠን እና የሚፈለገውን ውጤት ለማግኘት ማድረግ ያለብንን እናውቃለን።"
20/08/2026
«ካርል ዳርሎው በዚህ ሳምንት ልምምድ ሰርቷል። ወደ ልምምድ ተመልሷል፤ ስለዚህ በጥሩ ብቃት ላይ ይገኛል። ዴ ሊክት ለረጅም ጊዜ ከሜዳ ውጪ እንደነበር ግልጽ ነው ነገር ግን አሁን ልምምድ እየሰራ ነው፤ በድጋሚ መመለሱም በጣም ደስ ይላል።
እርግጥ ነው በሀል ጨዋታ ላይ አይሳተፍም፤ ነገር ግን በጥሩ ብቃት ላይ ይገኛል በጥሩ አቅጣጫም እየተጓዘ ነው።
ስለዚህ በዚህ ደረጃ የሱ መመለስ ለእኛ በእርግጥ ትልቅ ተጨማሪ ጥቅም ነው። ሼስኮም ወደ ልምምድ ተመልሷል።
ስለዚህ ይህም ሌላው አዎንታዊ ነገር ነው። ወደ ቡድኑ ተመልሶ ጥቂት እንደሚጫወት እንጠብቃለን።
ሌላው የሜሰን ማውንት ነገር በጥንቃቄ የተያዘ ነው፤ ነገር ግን ለመመለስ በጣም ተቃርቧል፤ ስለዚህ ለሳምንቱ መጨረሻ ጨዋታ የመሰለፉ ነገር የተረጋገጠ አይደለም (50/50 ነው)፤ ካልሆነ ግን ወደሚቀጥለው ሳምንት ይሸጋገራል።»
ማይክል ካሪክ
20/08/2026
#ሰበር
"ማንችስተር ዩናይትድ ስለ ባልዴ ሁኔታ ለመጠየቅ ከጆርጅ ሜንዴስ ጋር ተገናኝቷል።"
[ ፋብሪዚዮ ሮማኖ ]