TikTok · Scorpion 🦂 fitness Check out Scorpion 🦂 fitness’s post.
Scorpion Martial Art Club
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Scorpion Martial Art Club, Martial Arts School, Addis Ababa.
🥊 በScorpion Martial Arts Club የቀረበ: የማርሻል አርት ስፖርቶች ልዩነት እና አንድነት!
የየትኛውን ስፖርት መምረጥ እንዳለባችሁ ግራ ገብቷችኋል? እስኪ እንያቸው:
🔹 ሚክስድ ማርሻል አርት (MMA): ሁሉንም የማርሻል አርት ዓይነቶች (መትቶ መጣል፣ ግብግብ እና መሬት ላይ መታገል) ያቀፈ ዘመናዊ ስፖርት ነው።
🔹 ቴኳንዶ: በከፍተኛ እና ፈጣን የእግር ምቶች የሚታወቅ የኮሪያ ማርሻል አርት ነው።
🔹 ጂጂትሱ (BJJ): በትናንሽ ሰዎች በትልልቅ ሰዎች ላይ ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል፣ በመሬት ትግል እና በመቆለፍ ላይ ያተኮረ ነው።
🔹 ካራቴ: በእጅ እና በእግር ምቶች፣ በጠንካራ መከላከያዎች የሚታወቅ የጃፓን ማርሻል አርት ነው።
🔹 አይኪዶ: የባላጋራን ኃይል ወደ ራሱ በመመለስ፣ በመቆለፍ እና በመጣል ላይ ያተኮረ ሰላማዊ ማርሻል አርት ነው።
🔹 ዊንግ ቹን: በቅርብ ርቀት ፍልሚያ፣ በፈጣን ቡጢዎች (Chain Punches) የሚታወቅ የቻይና ኩንግፉ ዓይነት ነው።
✨ አንድነታቸው: ሁሉም ስፖርቶች ስነ-ስርዓትን፣ ራስን መቆጣጠርን እና አካላዊ ብቃትን ያዳብራሉ።
🔥 Scorpion Martial Arts Club - ምርጫዎን ዛሬ ይጀምሩ!
ኢንስትራክተር ቢንያም ብርሃኑ 💪!!
26/04/2026
በቅድሚያ ለሁለቱም ተጋጣሚዎች ክብር አለኝ።
👏👏
ሁሉን ማርሻል አርቲስት እቀጠቅጣለው የሚለው ንግግር ትክክል አይደለም።
#ሲጀመርም ሚክስድ ማርሻል አርት እና ማርሻል አርት ለብቻው አንድ ላይ አይሄዱም። ምክንያቱም የሁለቱም ቴክኒክ የተለያያ በመሆኑ። እንደ ንቃተህሊና
ረዘም ላለ ጊዜ ልምምድ ማድረግ ነበረበት።
ሲቀጥል የጆኒ እንቅስቃሴ በአብዛኛው ማቀፍ እና አፍርጦ ጥሎ ተጋጣሚውን እንቅ አድርጎ ፋታ ማሳጣት ነው።
ማርሻል አርት ላይ ሲመጣ ደግሞ 50% እግር 50% እጅ እየተጠቀምክ ተጋጣሚውን በተለያዩ የስንዘራ ታክቲክ (በተርን : በራውን : በሳይድ ኪክ እና መሰል እንቅስቃሴዎች ) የታጀበ ነው። እናም አረ በጣም ብዙ ልዩነት አለው።
ስለሁለቱ ተፋላሚዎች ግን መናገር ምፈልገው ለመላው ኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ ስፖርተኞች ትልቅ መነቃቃት ነው የፈጠሩት። በዛ ሊመሰገኑ ይገባል።
ነገር ግን ከፍልሚያው ይልቅ የቃላት ጦርነቱ ብቻውን ቀድሞውኑ ውድድሩ እንዲያልቅ አድርጎታል ያ ማለት ከልክ ያለፈ ዛቻ እና ተረባ ከወሬ በዘለለ ምንም መፍጠር ያልተቻለበት ነው የሆነው።
🙌አሁንም ሙያ በልብ ቢያደርጉ ባይ ነኝ።
ከዚህ ብኋላ ሌሎች መወዳደር ሲፈልጉ ...About MMA Fighting Technique ማወቅ መሠልጠን ያስፈልጋል። የማታው ፍልሚያ ሚያሳየን ዋናው ክፍተት አየር ላይ ስለበረረ ማንም ውድድር ማሸነፍ እንደማይችል ነው።
በተጨማሪ :- የነ መሥፍን : የነ ሳኒ ፍልሚያ ይበል ይቀጥል ሚያስብል ነው ደግሞም ደስስስስ የሚልም ነበረ።
በመጨረሻ አንድ ነገር ማለት ምፈልገው ለዚህ ውድድር ብቁ የሚሆኑ ልጆችን ከሥር መሠረቱ ማሰልጠን ተገቢ ነው።
20/03/2026
የሆሊውድ ፊልሞች ፈርጥ ቻክ ኖሪስ ከዚህ አለም በሞት ተለየ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ታዋቂው አሜሪካዊ የሆሊውድ ፊልሞች ተዋናይ እና የማርሻል አርቲስት ቻክ ኖሪስ በ86 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡
በፈረንጆቹ 1940 በኦክላሃማ የተወለደው ኖሪስ በማርሻል አርት ከመታወቁ በፊት በአሜሪካ አየር ኃይል አገለግሏል፡፡
በአክሽን ፊልሞቹ የሚታወቀው ኖሪስ ዎከር እና ቴክሳስ ሬንጀር በተሰኙ ተከታታይ ፊልም በልዩነት እንዲሁም በወጣቶች ዘንድ ፎሬቨር ሞርታላይዝድ በሚለው ፊልሙ ይታወቃል፡፡
ባገጠመው ህመም በሃዋይ የህክምና ክትትል ሲደረግለት የቆየው ቻክ ኖሪስ÷ በተወለደ በ86 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡
Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Kibreab Abera, Aklilu Zakwos, Muluneh Thomas
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
8787