13/08/2026
ተጨዋቾች ከረጅም አድካሚ የውድድር ዘመን በሁዋላ ምን አይነት ባህል ሊኖራቸው ይገባል !
⚽ የተጫዋችነት ዘመን ከፍ ለማድረግ ዘንድ — እረፍት፣ አመጋገብ እና የሕይወት ስነ-ምግባር ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።
አንድ ፕሮፌሽናል ተጫዋች ከአንድ ከባድ የውድድር ዘመን በኋላ የሚያደርገው እረፍት ለቀጣዩ ሲዝን ዝግጅት አካል ነው። እረፍት ማለት ሙሉ በሙሉ ከእንቅስቃሴ መራቅ ሳይሆን ሰውነትንና አእምሮን መልሶ ማደስ ነው።
በ2025 የFIFPRO የሕክምናና የHigh-Performance ባለሙያዎች የጋራ ምክረ-ሀሳብ ቢያንስ 4 ሳምንት Off-season break እንዲኖር፣ ከዚህም ውስጥ 2 ሳምንት ከክለብና ከብሔራዊ ቡድን ሙሉ በሙሉ ነፃ እንዲሆን እና ከዚያ በኋላ ቢያንስ 4 ሳምንት የgradual re-training እንዲኖር ይጠቁማል።
🧠 እረፍት ማለት “ምንም አልሰራም” ማለት አይደለም
ተጫዋቹ በመጀመሪያ ሰውነቱን እና አእምሮውን ማሳረፍ ይገባዋል። ከዚያ ቀስ በቀስ ወደ Active Recovery እና በመጨረሻ ወደ Pre-season ዝግጅት መሸጋገር ይኖርበታል።
REST → RECOVER → REACTIVATE → RE-TRAIN → PERFORM
ይህ ሂደት በተለይ ከከባድ ሲዝን በኋላ አስፈላጊ ነው።
🥗 አመጋገብ — እረፍት ላይ እንኳን የተጫዋቹ ስራ ነው
“ልምምድ የለም፣ ስለዚህ ምግብም ምንም አይደለም” የሚለው አስተሳሰብ ተጫዋቹን ሊጎዳ ይችላል።
በእረፍት ወቅት፦
* የተመጣጠነ ምግብ መመገብ
* በቂ ፕሮቲን ማግኘት
* አትክልትና ፍራፍሬ ማብዛት
* በቂ ውሃ መጠጣት
* ከመጠን በላይ ስኳር፣ ፈጣን ምግብ እና ከፍተኛ ካሎሪ መመገብን መቆጣጠር
ክብደትና የሰውነት ስብ እንዳይጨምር መጠን መጠበቅ
ያስፈልጋል።
እረፍት ማለት የተጫዋችነት ሕይወትን ማቆም ሳይሆን ሰውነትን ለቀጣዩ ሲዝን መጠበቅ ነው።
🍺 አልኮል —
“እረፍት ነው” ብሎ መጠን ማጣት አይገባም
ተጫዋች በእረፍት ጊዜ ማህበራዊ ሕይወቱን መደሰት ይችላል፤ ግን ከፍተኛ የአልኮል መጠጥን መደበኛ ልማድ ማድረግ ከተጫዋችነት ሕይወት ጋር አይጣጣምም።
በተለይ ከመጠን በላይ መጠጣት የእንቅልፍ፣ የhydration እና የrecovery ሂደትን ሊያበላሽ ይችላል። ስለዚህ ተጫዋቹ የራሱን ጤና፣ አካል እና የሙያ ዕድሜ ከጊዜያዊ ደስታ በላይ ማስቀመጥ አለበት።
🏆 ትልቁ ትምህርት
ተጫዋችነት በሜዳ ላይ ብቻ አይገነባም።
በልምምድ ይገነባል፤
በእረፍት ይጠበቃል፤
በአመጋገብ ይጠናከራል፤
በእንቅልፍ ይመለሳል፤
በስነ-ምግባር ይረዝማል።
* ስለዚህ ወጣት ተጫዋቾች፣ የእረፍት ጊዜያችሁን በጥበብ ተጠቀሙ። ቤተሰብዎን አግኙ፣ ይጓዙ፣ ይዝናኑ፣ በቂ እንቅልፍ ውሰዱ፤ ግን ሰውነታችሁን፣ አመጋገባችሁን እና የተጫዋችነት ስነ-ምግባራችሁን አትተዉ።
“ዛሬ ራሴን በጥበብ አሳርፋለሁ፤ ነገ በጠንካራ አካልና አእምሮ ወደ ሜዳ እመለሳለሁ።”
የተጫዋችነት ዕድሜህን ለማራዘም የምታደርገው እንክብካቤ የዛሬ ልምምድህን ያህል አስፈላጊ ነው። ⚽
09/08/2026
ፍፁም የታዳጊዎች እግር ኳስ ፕሮጀክት, ልጆች እግር ኳስን እንደ መዝናኛ ብቻ ሳይሆን በተደራጀ ስልጠና፣ በዲሲፕሊን እና በሙያዊ አመራር ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ የተቋቋመ መዋቅር ሲሆን ከ6–17 ዓመት የሆኑ ልጆችን በመቀበል በእድሜ እና በችሎታ ደረጃ በመለየት፣ ከመሠረታዊ የኳስ ቁጥጥር ጀምሮ ወደ የተሻለ የጨዋታ ግንዛቤ እና ብቃት ለማሸጋገር እየሰራ ይገኛል::
⚽ የኳስ ቁጥጥርና ቴክኒክ
🏃 ፍጥነትና አካላዊ ብቃት
🧠 የጨዋታ ንባብና ውሳኔ አሰጣጥ
🤝 የቡድን ስራና ዲሲፕሊን
🌱 የግል ችሎታና ተሰጥኦ
እንዲሁም ሌሎች የእግርኳስ ስልጠናዎችን በመስጠት ፕሮጀክቱ የነገ ኮከብ ተጫዋቾችን ለመገንባት እየሰራ ይገኛል።
ዋና አሰልጣኛችን ፍፁም ገ/ ማርያም - የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የቅዱስ ጊዎርጊስ ተጫዋች እንዲሁም የ CAF B license / ፈቃድ ባለቤት፣ ከ15 ዓመት በላይ በአገር ዉስጥና በዉጭ ያካበተውን ልምድ አሁን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ወደ ስልጠና ሜዳ ተመልሷል::
ይህን ፕሮጀክት ለመቀላቀል ወይም መረጃ ለማግኘት በሚከተለው ቁጥር ይደዉሉ::
0963414243
ፍፁም የታዳጊዎች እግር ኳስ ፕሮጀክት
ተተኪ ኮከቦችን እናፍራ!
11/07/2026
ለኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን
በነገው ወሳኝ ጨዋታ ድል በመቀዳጀት ለፊፋ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ዓለም ዋንጫ እንድትበቁ ከልብ እንመኛለን
በሙሉ ልብ፣ በጽናትና በኩራት ተጫወቱ። ኢትዮጵያ ከእናንተ ጋር ናት!
መልካም ዕድል! ድል ለኢትዮጵያ! 🇪🇹⚽
05/06/2026
Football is often seen as a game of reactions, but the best players do much more than react — they anticipate. Pep Guardiola’s quote highlights one of the most valuable qualities in modern football: the ability to identify solutions before problems appear.
When a player scans the field, understands the positioning of teammates and opponents, and predicts what will happen next, he gains a crucial advantage. He doesn't need extra speed because he is already mentally one step ahead.
This is what separates elite players from average ones. The elite do not wait for pressure to arrive before deciding what to do. They have already identified the next pass, the next movement, or the next opportunity before receiving the ball.
Developing this ability requires more than technical training. It requires encouraging players to observe, think, analyze, and understand the game. The more they learn to read situations early, the more effective their decisions become.
👉 Football intelligence is not about having all the answers. It is about recognizing the right solution before everyone else sees the problem.
👉 In your opinion, what is more important in football: technical ability or the ability to see the game one step ahead?
29/05/2026
🎁💸 ይገምቱ ይሸለሙ 💸🎁
🎉🎉ታላቅ እድል 500 ብር🎉🎉
የአርሰናል ኦርጅናል ማልያ
ወይም የፒኤጂ ማልያ
ይሸለማሉ
ቅዳሜ ግምቦት 22 በሀንጋሪ ቡዳፔስት አሬና የሚደረገውን የአርሰናል እና ፒኤስጂ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋት ትክክለኛ ውጤት ገምተው ይሸለሙ!!
ልክ ከዚህ በፊት እንደምናደርገው ጨዋታውን በትክክል ለገመቱ 3ሰዎች የምንሸልም ይሆናል!!
🔴ተሸላሚ ለመሆን እነዚህን ነገሮች ማድረጎን አይርሱ ግዴታ ነው!!
1. ውጤቱን ከዚህ ፖስት ስር ኮመንት ላይ መገመት
2. ይህንን ፖስት ላይክ ማድረግ
3. ይህንን ፖስት ለ5 ግሩፖች እና ሰዎች ሼር ማድረግ
4. ፔጁን Follow ማድረግ
5. የሰጡትን ግምት EDIT ማድረግ የተከለከለ ነው
6. ውጤት ደጋግሞ መገመት አይቻልም
7. ጨዋታው ከጀመረ በኋላ መገመት አይቻልም
ከጨዋታው በኋላ ደንብ አሟልተው ትክክለኛ ግምት የገመቱ አሸናፊዎችን ለይተን የምናሳውቅ ይሆናል።
መልካም ዕድል ለሁላችሁም!❤️
22/02/2026
“If a child is afraid to make mistakes, they will never become creative.” – Pep Guardiola
Creativity in football is born from courage, not perfection.
When a child plays with fear, they choose the safe pass. They avoid risk. They hide from responsibility.
But when they feel safe to try, fail, and try again, something changes.
They attempt the through ball.
They try the dribble.
They invent solutions.
Mistakes are not a problem — they are information.
They show intention. They show initiative. They show imagination.
As coaches and parents, our role is not to eliminate mistakes, but to normalize them.
Correct with clarity. Encourage with patience. Protect their confidence.
Because creative players are not formed by criticism —
they are formed by freedom.