90 ደቂቃ ስፖርት

90 ደቂቃ ስፖርት

Share

90 ደቂቃ ስፖርት ...
- ከእሁድ እስከ እሁድ ትኩስ ትኩስ የሀገር ውስጥ እና ውጪ ስፖርታዊ ዜናዎች የምታገኙበት የፌስቡክ ፔጃችን ነው!

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👇
https://t.me/+hi2jirs8uC9hMTQ0

Photos from 90 ደቂቃ ስፖርት's post 28/06/2026

🚨🇵🇹 ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ክርስቲያኖ ሮናልዶን ስለማሳረፍ:

🗣️ “ክርስቲያኖ ሁልጊዜ በትክክለኛው ቦታ እና በትክክለኛው ሰዓት መገኘትን የለመደ ተጫዋች ነው። በቦታው ላይ በጣም ዲሲፕሊን ያለው ሲሆን፣ ለቡድን አጋሮቹም ቦታ ይፈጥራል።”

“የእሱ የአካልም ሆነ የአእምሮ ዝግጁነት ላይ ምንም ጥያቄ የለም። በቀጣዩ ጨዋታ አንዳንድ ለውጦችን ማድረግ ሊያስፈልገን ይችላል፣ ነገር ግን እያንዳንዱን ውሳኔ የምንወስነው ባለን መረጃ እና ዳታ መሰረት ነው።”

27/06/2026

ግራኒት ዣካ የቼልሲ ተጫዋች ሊሆን ይችላል!

ዣካ ከቀድሞ አሰልጣኙ ዣቪ አሎንሶ ጋር በድጋሚ መስራት ይፈልጋል::

[Fabrizio Romano]

27/06/2026

💔 አሳዛኝ ዜና:

🇳🇱 ኮዲ ጋክፖ እና የሕይወት አጋሩ ኖአ ቫን ደር ቤይ በእርግዝና ወቅት ልጃቸውን በማጣታቸው አሳዛኝ ዜናውን አጋርተዋል።

🕊️ በዚህ ከባድ ጊዜ ለኮዲ፣ ለኖአ እና ለመላው ቤተሰባቸው ጥንካሬና መጽናናትን እንመኛለን። 🤍

26/06/2026

ናኒ 🗣፡ የፖርቹጋል ህዝብ እና ተጨዋቾች ሁሌም ክርስቲያኖ ሮናልዶን እንደሚተቹት ተስፋ አደርጋለሁ እውነቱን ለመናገር እሱ ለፖርቹጋል ጥሩ አይደለም "

ጋዜጠኛ 🗣 : ናኒ ለምን እንዲህ ታወራለህ? ጓደኛሞች አይደላችሁም እንዴ?

ናኒ 🗣 ፡ አንተ ሮናልዶን አታውቀውም ትችቶች እንዲወሩበት አይፈልግም ከተወሩ ደግሞ ሜዳ ላይ ምርጥ መልስ ይሰጣል። ባይተች ኖሮ እነዚያን 2 ጎሎች ያገባ ነበር? ለዛም ነው ሁሌም ፖርቹጋሎች ሮናልዶን መተቸት ያለባቸው በጣም ጥሩ እንዲጫወት" 😂😂😂

25/06/2026

ሀላንድ እና ሚስቱ ኢዛቤል በዲሴምበር 2024 ላይ ወንድ ልጅ ወልደዋል ነገር ግን እስከዛሬ ድረስ ሀላንድ ስለ ልጁ ምንም አልተናገረም በሶሻል ሚዲያ ላይ ራሱ ልጁን አላሳየውም ማንም ሰው ስለልጁ ምንም ነገር አያውቅም ከቤተሰቡ በስተቀር

አብዛኛው ታዋቂ ግለሰቦች ሙሉ ህይወታቸውን ሶሻል ሚዲያ ላይ በሚያሳዩበት ጊዜ ሀላንድ ግን የቤተሰቡን ህይወት ሚስጥራዊ እና ከማንም እይታ የራቀ እንዲሆን መርጧል 👏

24/06/2026

" ሜሲን ለመጀመሪያ ጊዜ ሳገኘው እንደዚህ አልኩት ሊዮ በህይወቴ ካየኋቸው ሁሉ አንተ ምርጥ ተጨዋች ነህ አልኩት። እናም እሱ ፈገግ አለ እና ጨበጠኝ እኔም ደስ ብሎኝ ነበር

ከዛም ወደ እረፍት ስንሄድ ከእንደገና ወደ እሱ ሄጄ እንዲህ አልኩት ሊዮ ከምሬን ነው ወደ ሲቲ ና ጋርዲዮላ ሁሌ እኛ ላይ ይጮህብናል እንደ ሜሲ አይነት ተጨዋች የለም እያለ ስለዚህ አንተ ከመጣክ አይጮህብንም

ከዛ ሜሲ እንደገና ፈገግ አለና ሄደ ነገር ግን ሮድሪ ስናወራ እያየን ነበር እና ወደ እኔ መጣና ሜሲን ስለምንድነው የምታወራው አለኝ እኔም ያወራሁትን ነገርኩት

ሮድሪም መልሶ እየሳቀ ስፓኒሽ ቋንቋ ታውቃለህ ወይ አለኝ እኔም አይ አላውቅም አልኩት እሱም አንተ ደደብ ሜሲም እንግሊዘኛ አያውቅም አለኝ"😂

ጃክ ግሪሊሽ 🗣

23/06/2026

ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በ6 የተለያዩ አለም ዋንጫዎች ላይ ጎል በማስቆጠር ቀዳሚው እና ብቸኛው ተጨዋች ሆኗል

🐐

Photos from 90 ደቂቃ ስፖርት's post 23/06/2026

" ሮናልዶ ለማንም ምንም ማረጋገጥ አይጠበቅብክም አንተ ሮናልዶ ነክ ያኔ በ2016 ከፖርቹጋል ጋር የዩሮ ዋንጫን ለመጀመሪያ ጊዜ አንስተካል እናም ፖርቹጋል ከሮናልዶ በፊት የትነበረች እና በኋላስ?

ስለዚህ ተረጋጋ ተጫወት ዘና በል "👏

የቢን ስፖርት ተንታኝ እና የግብፅ ሌጀንድ አቡ ታሪካ 🗣

22/06/2026

" ልጅ እያለሁኝ ጓደኞቼ ራሳቸውን እኔ ሜሲ ነኝ ፣ ፊጎ ነኝ ፣ ዴኮ ነኝ ብለው ያወሩ ነበር ነገር ግን እኔ ሁሌ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ነኝ ብዬ አወራ ነበር "

ብሩኖ ፈርናንዴዝ 🗣

22/06/2026

ቀሪ 6 ደቂቃዎች ተደረጉ

የስታዲየም መብራት በመጥፋቱ ምክንያት 90ኛው ደቂቃ ላይ ተቋርጦ ዛሬ ለ6 ደቂቃዎች ያህል የተደረገው የምድረገነት ሽረ እና የፈረሰኞቹ ጨዋታ 0ለ0 ተጠናቋል።

የተወሰኑ ደጋፊዎች ስታዲየም ተገኝተው የስድስቱን ደቂቃ ተመልክተዋል።

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Address


Addis Ababa
Addis Ababa
01