25/07/2026
kamil jemal
kamil jemal
25/07/2026
24/07/2026
የሳምንቱ የሰላም ፕሮፋይል! 🕊
ሰላም ለኢትዮጵያችን! 🇪🇹
-
The weekly Peace Profile! 🕊
Peace for our Ethiopia! 🇪🇹
23/07/2026
ሴቶች ሰዎችን ወደ ውይይት በመጥራት እና በማስማማት ግጭቶችን በሰላም እንዲፈቱ የማድረግ አቅማቸው አይተኬ ነው።
ሴቶች ሀገራዊ የሆነ የጋራ ግብን ለመደገፍ፣ መረጋጋትን እና ዕድገትን ለማረጋገጥ ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው።
ሴቶች በሁለንተናዊ ጉዳዮች ላይ ዜጎች በአንድነት እና በአብሮነት ፀንተው እንዲቆሙ፤ ግጭቶች በተከሰቱበት ወቅት በማረጋጋት መግባበት ላይ እንዲደረስ አስተዋፆዋቸው የጎላ ነው።
ሴቶች
🤝 በማህበራዊ ትስስር ግንባታ፣
🤝 በማህበረሰብ ውስጥ መተማመንን በማጎልበት እና
🤝 ልዩነቶችን በማጥበብ አብሮነትን ለማጠናከር ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ ነው።
ሰላም ለኢትዮጵያ ! 🕊
22/07/2026
ማስታወቂያ
የሰላም ሚኒስቴር በፌዴራል አስፈፃሚ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1263/2014 መሰረት የተቋቋመ ተቋም ሲሆን ከተሰጡት ተግባር እና ሃላፊነቶች መካካል በወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግባባት እንዲፈጠር አግባብነት ያላቸውን አካላት ያስተባብራል። በመሆኑም የዘላቂ ሰላም ግንባታ እና ሀገራዊ መግባባት መሠረት ሊሆን የሚችል የሰላም በጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራም ነድፎ ተግባራዊ በማድረግ ጉልህ ውጤቶችን ማስመዝገብ ችሏል። ይህንኑ ተግባር በመቀጠል ለ15ኛ ዙር ወጣት በጎ ፈቃደኞችን አሰልጥኖ ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ለሰላም አምባሳደርነት ለማሰማራት ዝግጅቱን አጠናቋል። በዚሁ መሰረት ጅማ እና ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደባችሁ ሰልጣኝ የሰላም በጎ ፈቃድ እጩ አምባሳደሮች ከሐምሌ 23-25/2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት ሶስት (3) ተከታታይ ቀናት ውስጥ በተመደባችሁበት የስልጠና ማዕከል በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ እና ስልጠናውን እንድትጀምሩ እየጠየቅን ከተጠቀሱት ቀናት ቀድመው እንዲሁም ዘግይተው የሚመጡ ሰልጣኞችን የማንቀበል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
ወደ ተመደባችሁበት ሰልጠና ማዕከል ስትመጡ የፋይዳ መታወቂያ፣ የትምህርት ማስረጃ(ዋናዉን)፣ አንሶላ፣ ብርድልብስ እና የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ እንድትገኙ እያሳወቅን የተመደበችሁበት ዩኒቨርስቲ ዝርዝር በተቋማችን የቴሌግራም ገፅ https://t.me/mopethiopia የተለቀቀ መሆኑን እንገልፃለን።
ሰላም ለኢትዮጵያ! 🕊
22/07/2026
ብሔራዊ የሰላም በጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራም መርሆዎች ከሰላም ጋር ቀጥታ የሆነ ግንኙነት አላቸው፡፡
እነዚህ መርሆዎች፡-
♟ አብሮነት እና መግባባትን ይፈጥራሉ
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሆዎች ሰዎች የተለያየ ባህል፣ ሃይማኖት እና አስተሳሰብ ቢኖራቸውም እንኳ በአንድ ጉዳይ ዙሪያ እንዲሰባሰቡ እና በጋራ እንዲሰሩ እድል ይሰጣቸዋል። ይህ ደግሞ በሰዎች መካከል መግባባት እና መተማመን እንዲፈጠር ያግዛል።
በመሆኑም ወደ ግጭት ሊያመሩ የሚችሉ አለመግባባቶችን እና ልዩነቶችን በማጥበብ ሰላማዊ መፍትሄዎችን እንዲያገኙ ያደርጋል።
♟ ፍትሃዊነት እና መቻቻልን ያመጣሉ
ፍትሃዊነትን መሰረት ያደረገ በጎ ፈቃድ አገልግሎት በማህበረሰብ ውስጥ የእኩልነት ስሜት እንዲኖር ያደርጋል።
ይህ ሁኔታ ደግሞ ወደ ግጭት ሊያመሩ የሚችሉ የሀብት እና የስልጣን ክፍፍል ችግሮችን ይቀንሳል። በመሆኑም ማህበራዊ መረጋጋትን እና ሰላምንም ያረጋግጣል።
♟ የዜጎች ተሳትፎ እና ኃላፊነትን ያበረታታሉ
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሆዎች ዜጎች በሀገራቸው እና በማህበረሰባቸው ጉዳዮች ላይ በንቃት እንዲሳተፉ እና የኃላፊነት ስሜት እንዲሰማቸው ያበረታታል።
ይህ የኃላፊነት ስሜት በሀገር ውስጥ ያሉ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ እና ዘላቂ መፍትሄዎችን እንዲፈልጉ ያነሳሳል።
ሰላም ለኢትዮጵያ! 🕊
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
Addis Ababa