BizuAthletics

BizuAthletics

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from BizuAthletics, Sport & recreation, Toronto, ON.

ብዙአትሌቲክስ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ላይ በማተኮር የሀገር ውስጥና የውጭ ውድድሮችን እና ተዛማጅ ዜናዎችን የሚያቀርብ ድህረ ገጽ ነው።
BizuAthletics is news website that provides coverage of both local and international competitions, and athletics related news with a special focus on Ethiopian athletics.

08/29/2026

በ2026 ዋንዳ ዳይመንድ ሊግ የወንዶች 5000 ሜትር በነጥብ ደረጃ ለብራሰልሱ የፍፃሜ ውድድር ያለፉት አስር አትሌቶች፡፡ አዲሱ ይሁኔ እና ቢኒያም መሐሪ በርቀቱ ለፍፃሜው ያለፉ ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡

The ten athletes who qualified for the 2026 Wanda Diamond League men's 5,000m final in Brussels based on points standings.

Addisu Yihune and Biniam Mehary are the two Ethiopians who qualified for the final in this event.

Allianz Memorial Van Damme

08/28/2026

15 ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለብራሰልሱ የ2026 የዳይመንድ ሊግ ፍጻሜ ውድድር አልፈዋል።

በአምስት የተለያዩ የውድድር አይነቶች፣ በአጠቃላይ 15 የኢትዮጵያ አትሌቶች (11 ሴቶች እና 4 ወንዶች) ለ2026ቱ የዋንዳ ዳይመንድ ሊግ ፍጻሜ ውድድር ለማለፍ በቅተዋል። የፍጻሜ ውድድሮቹ በቤልጂየም ዋና ከተማ ብራሰልስ፣ ሴፕቴምበር 4 እና 5 ቀን 2026 (ነሐሴ 29 እና 30/2018) ይካሄዳሉ።

15 ETHIOPIAN ATHLETES HAVE QUALIFIED FOR THE 2026 DIAMOND LEAGUE FINAL IN BRUSSELS.

A total of 15 Ethiopian athletes (11 women and 4 men) have qualified for the 2026 Wanda Diamond League final across five different events. The finals will take place in Brussels, the capital of Belgium, on September 4 and 5, 2026 (August 29 and 30, 2018, Ethiopian Calendar).

08/28/2026

BizuAthletics በዙሪክ ዳይመንድ ሊግ ቨርቹዋል ሚክስድ ዞን ቃለ መጠይቅ አድራጊ በኩል ላቀረባቸው ጥያቄዎች ቢኒያም ምላሽ የሰጠበት ቪዲዮ፡፡



🎥 Diamond League AG

Photos from BizuAthletics's post 08/28/2026

ትላንት ምሽት (ኦገስት 27-2026) በስዊዘርላንድ ዙሪክ በተካሄደው Weltklasse Zürich የ2026 ዙሪክ ዳይመንድ ሊግ ስድስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሶስት የውድድር አይነቶች ተሳታፊ ነበሩ፡፡

በወንዶች 3000 ሜትር ላይ ተሳታፊ ከነበሩት አራት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ቢኒያም መሐሪ የግሉን ምርጥ ሰዓት ባሻሻለበት 7፡28.18 ሰዓት አምስተኛ ሆኖ በማጠናቀቅ ከሳምንት በኋላ በቤልጅየም ብራስልስ ለሚካሄደው የወንዶች 5000 ሜትር ፍፃሜ ውድድር ለማለፍ በቅቷል፡፡ መዝገቡ ስሜ የግሉን ምርጥ ሰዓት ባሻሻለበት 7፡35.56 ሰዓት አስረኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ አብድርሰላም ወርቁ (7፡35.70) እና አብዲሳ ፈይሳ (7፡46.23) በቅደም ተከተል 11ኛ እና 13ኛ ሆነው ጨርሰዋል፡፡

ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላ BizuAthletics በዙሪክ ዳይመንድ ሊግ ቨርቹዋል ሚክስድ ዞን ቃለ መጠይቅ አድራጊ በኩል ላቀረባቸው ጥያቄዎች ቢኒያም መሐሪ ምላሽ ሲሰጥ ‹‹ዘንድሮ ካለፈው ዓመት በቁጥር የበለጡ የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች ላይ ተወዳድሬያለሁ፡፡ በእያንዳንዱ ውድድር ላይ ሁልጊዜም የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ። እንደ አለመታደል ሆኖ፣ ውጤቶቹ እኔ ከምጠብቀው ጋር ተመሳሳይ አልነበሩም። በዛሬው ውድድር ላይ ያሳየሁት አቋም ተስፋ ሰጪ ይመስላል። ልምምዴን ከፍ በማድረግ በሁሉ ረገድ ለመሻሻል ባደረግኩት ጥረት አዎንታዊ ውጤትን እያየሁበት ስለሆነ ይህንኑ ማስቀጠል እፈልጋለሁ። ወደዙሪኩ ውድድር ስመጣ ግቤ ከነበሩት ነገሮች አንዱ ለብራልሱ የፍፃሜ ውድድር ለማለፍ የሚበቃኝን ውጤት ማስመዝገብ ነበር፡፡ እናም ያንን አሳክቼዋለሁ ብዬ አስባለሁ›› ብሏል፡፡

በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል የተወዳደረችው አለምናት ዋለ 9፡20.14 በሆነ ሰዓት 11ኛ በመውጣት በነጥብ ፉክክሩም ተመሳሳይ ደረጃን ይዛ ለብራስልሱ የፍፃሜ ውድድር ለማለፍ ሳትችል ቀርታለች፡፡

ስዊዘርላንዳዊቷ ኦድሬ ቬሮ የወቅቱ የርቀቱ ንግስትነቷን ዳግም ባስመሰከረ መልኩ አሸናፊ በሆነችበት የሴቶች 800 ሜትር የተወዳደረችው ሳይዳ ፀሐዬ 1፡57.33 በሆነ ሰዓት አራተኛ ወጥታለች፡፡

ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች በ2026 ዙሪክ ዳይመንድ ሊግ የተሳተፉባቸው ሶስቱም ውድድሮች ሙሉ ውጤቶች በምስል ተያይዘዋል 👇

08/26/2026

በ2026 ዋንዳ ዳይመንድ ሊግ የሴቶች 5000 ሜትር በነጥብ ደረጃ ለብራሰልሱ የፍፃሜ ውድድር የሚያሳልፉትን የመጀመሪያ አስር ቦታዎች ከያዙት አትሌቶች ስምንቱ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡

Eight of the top ten athletes qualifying for the 2026 Wanda Diamond League - Women's 5000 m final in Brussels are Ethiopians.

Allianz Memorial Van Damme

08/25/2026

ሐሙስ ኦገስት 27 ቀን 2026 በሚካሄደው የ2026 ዌልትክላሴ ዙሪክ (ዙሪክ ዳይመንድ ሊግ) ውድድር ላይ አራት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሶስት የውድድር አይነቶች ይሳተፋሉ።

በብራስልስ ለሚካሄዱት የፍፃሜ ውድድሮች ለማለፍ የሚያበቁ ነጥቦች የሚመዘገቡበት የመጨረሻው ውድድር በሆነው የዙሪክ ዳይመንድ ሊግ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሴቶች 800 ሜትር ሳይዳ ፀሐዬ፣ በወንዶች 3000 ሜትር ቢኒያም መሐሪ እና መዝገቡ ስሜ፣ እንዲሁም በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል አለምናት ዋለ የሚፎካከሩ ይሆናል፡፡

Four Ethiopian athletes will compete in three events at the 2026 Weltklasse Zürich (Zurich Diamond League) to be held on Thursday, August 27, 2026.

In the Zurich Diamond League, the final event where points are scored to qualify for the finals in Brussels, Ethiopian athletes will compete in the women's 800 meters, Saida Tsehaye, the men's 3000 meters, Biniam Mehary and Mezgebu Sime, and the women's 3000 meters steeplechase, Alemnat Walle.

08/25/2026

በ2026 ዋንዳ ዳይመንድ ሊግ - በሴቶች 1500 ሜትር ለብራሰልሱ ፍጻሜ ውድድር ያለፉ አትሌቶች፡፡

08/24/2026

ታዋቂዋ የኢትዮጵያ የረጅም ርቀት ሯጭ ጥሩነሽ ዲባባ Tirunesh Dibaba ሴፕቴምበር 13 ቀን 2026 በሚካሄደው የኤጄ ቤል ግሬት ኖርዝ ራን Great North Run የግማሽ ማራቶን ውድድር ላይ እንደምትሳተፍ የውድድሩ አዘጋጆች ይፋ አድርገዋል። ጥሩነሽ ከ2012ቱ የለንደን ኦሊምፒክ የ10 ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳልያ ድሏ ከ44 ቀናት በኋላ በግማሽ ማራቶን የመጀመሪያ ተሳትፎዋን ያደረገችው እና በአሸናፊነት ያጠናቀቀችው በዚህ ውድድር ላይ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በመጀመሪያ የግማሽ ማራቶን ተሳትፎዋ ያሸነፈችበት 1:07:35 የሆነ ሰዓትም በወቅቱ በታሪክ ከተመዘገቡት ፈጣን የመጀመሪያ የግማሽ ማራቶን ተሳትፎ ሰዓቶች አንዱ ነበር። በግሬት ኖርዝ ራን የሴቶች ግማሽ ማራቶን ውድድር ላይ ጥሩነሽ ዲባባ በ2012 ያስመዘገበችው ድል በኢትዮጵያዊ ሴት ተወዳዳሪ የተመዘገበ የመጨረሻው ድል ነበር፡፡ ከዛ ወዲህ የተካሄዱትን 12 ውድድሮች በሙሉ ያሸነፉት ኬንያውያን አትሌቶች ናቸው፡፡

በዘንድሮው የግሬት ኖርዝ ራን ግማሽ ማራቶን ላይ ከጥሩነሽ በተጨማሪ ከኢትዮጵያ በወንዶች ደረሰ ገለታ በሴቶች መልክናት ውዱ እንደሚሳተፉም ተገልጿል፡፡

08/23/2026

በ Memoriał Kamili Skolimowskiej ሲሌሲያ ዳይመንድ ሊግ የሴቶች 1500 ሜትር ውድድር ፅጌ ዱጉማ የግሏን ምርጥ ባሻሻለችበት እና የወቅቱ ፈጣን በሆነ 3፡55.06 ሰዓት አሸንፋለች፡፡ በዚህ ውድድር ላይ የተሳተፉት ብርቄ ሀይሎም (3፡56.76) እና ሳሮን በርሔ (4፡01.15) በቅደም ተከተል 8ኛ እና 11ኛ ሆነው አጠናቀዋል፡፡

ፅጌ ውድድሩን በአንደኛነት ለማጠናቀቅ የበቃችው በመጨረሻዎቹ አንድ መቶ ሜትሮች ውስጥ ከፊቷ የነበሩትን አራት አትሌቶች ከኋላቸው በመምጣት በፈጣን አጨራረስ ሩጫ በማለፍ ነው፡፡

ፅጌ ከውድድሩ በኋላ ለአዘጋጆቹ በሰጠችው አስተያየት ‹‹እኔ በዋናነት የ800 ሜትር ተወዳዳሪ ነኝ፡፡ ይህ ውድድር በ1500 ሜትር ለሁለተኛ ግዜ የተሳተፍኩበት ነው፡፡ ውድድሩ ቴክኒካዊ ብቃትን የሚጠይቅ ሩጫ የነበረ ሲሆን የመጨረሻዎቹ 200 ሜትሮች በጣም ከባድ ነበሩ፡፡ ውጤቴ በጣም ጥሩ ነው፡፡ ባስመዘገብኩት ድልም በጣም ደስተኛ ነኝ። በሚቀጥለው ሳምንት በዙሪክ በሚደረገው የዳይመንድ ሊግ ውድድር በ800 ሜትር እንደምወዳደር ተስፋ አደርጋለሁ›› ብላለች።

08/23/2026

ገመቹ ጎዳና በ Memoriał Kamili Skolimowskiej ሲሌሲያ ዳይመንድ ሊግ በወንዶች የ3000 ሜትር መሰናክል ውድድር ላይ ካሸነፈ በኋላ በውድድር ቦታው በሚገኘው የቃለ-መጠይቅ ስፍራ (Mixed Zone) የሰጠው አስተያየት።



🎥 Credits: Diamond League AG

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Toronto?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


Toronto, ON