TEME DICHA

TEME DICHA

Share

Sport

12/08/2026

የድል (የማሸነፍ) ታሪካቸው
ካዎ ጦና አፄ ምኒልክ ወደ ወላይታ ላኳቸው ተደጋጋሚ የወታደራዊ ዘመቻዎችና ጥሪዎች እጃቸውን ሳይሰጡ ለ7 ዓመታት ያህል (ወደ 6 ጊዜ ያህል የተደረጉ የተበታተኑ ጥቃቶችን) በብቃት መክተውና አሸንፈው መልሰዋል።

አፄ ምኒልክ በላኳቸው አዛዦች ብቻ የካዎ ጦናን ጦር ማሸነፍ ስላልተቻለ፣ ንጉሠ ነገሥቱ ራሳቸው ታላላቅ የጦር አበጋዞቻቸውን (እንደ ራስ ጎበና፣ ራስ ሚካኤል፣ ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ እና አባ ጅፋር II) እንዲሁም ዘመናዊ መሣሪያ የታጠቀ ታላቅ ጦር በግንባር በመምራት መጡ።

09/08/2026

ነሃሴ 3 — ውድ ህይወታቸውን የገበሩ የጀግኖቻችንን የጋራ መስዋዕትነት የምንዘክርበት ቀን ነው። የከፈሉት ዋጋ ዘာሬም ነገም በትውልድ ቅብብሎሽ ውስጥ በክብር ይታወሳል!

​ #የሰማዕታትቀን #ክብርለጀግኖቻችን #አንረሳውም 💪🕊️❤️💛🖤

19/07/2026

ከክለብ ክለብ የምትሄዱ ተጨዋቾች ሰከን በሉ!!

የአንድ ክለብ ማሊያ ዝም ብሎ ጨርቅ ወይም ሜዳ ላይ ለመለያያ የሚለበስ አልባሳት አይደለም። ማሊያ ማለት የሺዎች ደጋፊዎች ኩራትና የዛ የክለብ ማንነት መገለጫ ክቡር እሴት ነው። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ ተጫዋቾች ዘንድ የሚስተዋለው ድርጊት የማሊያን ክቡርነት ያቀለለ ነውር ሆኖ ይታያል። ተጫዋቾች ገና የዝውውር ድርድሩ ሳይጠናቀቅ ወይም ለገንዘብ ብቻ ሲሉ ዛሬ የአንዱን ነገ የሌላውን ክለብ ማሊያ እየለበሱ ፎቶ ለመነሳት የሚቸኩሉበት አካሄድ የስፖርቱን ክብር የሚነካ ነው።

ማሊያ ለብሶ ፎቶ ከመነሳትና ለህዝብ ይፋ ከመሆን በፊት ቆም ብሎ ማሰብ ከዚያ ማሊያ ጀርባ ያለውን የደጋፊውን ስሜት ማስታወስ ይገባል። ያንን ክቡር ማሊያ ለብሶ ፎቶ መነሳት ማለት ከክለቡና ከደጋፊው ጋር ትልቅ የቃል ኪዳን ውል እንደመግባት መሆኑን ዘንግቶ ነገሩን እንደ ፋሽንና እንደ ተራ ነገር መቁጠር ትልቅ ስህተት ነው። ተጫዋቾች ለለበሱት ማሊያ ያላቸው ክብርና ታማኝነት በፎቶ ግብዝነት ሳይሆን በሜዳ ላይ በሚያሳዩት ተጋድሎና ለክለቡ በሚያበረክቱት እውነተኛ ክብር ሊለካ ይገባዋል። ስለዚህ ማንኛውም ተጫዋች የአንድን ክለብ ማሊያ በላዩ ላይ ከመጣሉ በፊት ድርጊቱ የሚያስከትለውን ከባድ የኃላፊነት ስሜት ተረድቶ በብስለት ሊራመድ ይገባል። ምክንያቱም የማሊያ ክብር አይቀለድበትም።

07/07/2026

ቃል መግባት ቀላል ነው፣ ግንባታ መጀመር ግን ወንድነት ነው! የተስፋ ከረጢታችን ሞልቷል፣ አሁን ሜዳችንን ስጡን!"

16/06/2026

ድራጎን ጀማ የተባለው ግለሰቦ ተያይዟል!!

👉​በሴቶች ላይ የክብር ጥሰት ሲፈጽም የነበረው እና እርቃን ምስሎችን ያለፈቃድ በማሰራጨት ሲያሰቃየን የነበረው ርኾቦት ዘካሪያስ ባካሎ (ድራጎን ጀማ) ከሀገር ሊሰደድ ሲል በቁጥጥር ስር ውሏል።

​ይህ የወንጀል ድርጊት ተፈጻሚ እንዲሆን ከኋላ ሆነው ሲረባረቡ ለነበሩት አካላት ተገቢው የህግ ቅጣት እንዲያገኙና ፍትሕ እንዲሰፍን፣ በቅንጅት ለሰራነው ስራ በቅድሚያ እግዚአብሔር ይመስገን። ይህንን የወንጀል ድርጊት ተከታትዬ፣ በኦሮምያ ክልል፣ ምስራቅ ሀረርጌ ዞን፣ ባቢሌ ከተማ በመገኘት ከፖሊስ አባላት ጋር በመቀናጀት እንዲያዝ አድርጌዋለሁ።

​ለዚህ ድል ስኬት ከሶዶ ከተማ እስከ ፌዴራል ድረስ ለተባበሩን የመንግስት አመራሮች በሙሉ፣ እንዲሁም ይህንን ጉዳይ በባህር ማዶ ሆነው በትኩረት ሲከታተሉ እና ድምጻቸው ሲሆኑ ለነበሩት ታጋይ የዎላይታ ልጆች፣ እና ለባቢሌ ከተማ ፖሊስ አባላት ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

​ለዚህ ድርጊት ተባባሪ የነበሩ ሌሎች አካላትም ከህግ አያመልጡም። ትግላችን ፍትሕ ሙሉ በሙሉ እስኪሰፍን ይቀጥላል!" ማንኛውም ግለሰብ ከሕግ በታች ነው💪

Teme dicha

14/06/2026

🇧🇪💚 🐝 ቀጣይ ጨዋታ ⏭️Next Game🐝
ማን ያሸንፋል ውጤቱን ይገምቱ ??
🇪🇹 CBE የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 35ኛ ሳምንት ጨዋታ
💙ባህርዳር ከተማ ከ ወላይታ ዲቻ💚
ማክሰኞ ሰኔ 9/2018 ዓ.ም
⏰10:00 ሰዓት
🏟 አዲስ አበባ ስታዲየም
🐝ድል ለጦና ንቦች🐝
TEME DICHA💚

13/06/2026

በወላይታ ዞን በገጠሩ ክፍል የዝናብ እጥረት በበልግ ሰብሎች ላይ ከፍተኛ ስጋት ፈጠረ 😭

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን ገጠራማ ወረዳዎች በ2018 ዓ.ም የበልግ ወቅት የተዘሩ ልዩ ልዩ ሰብሎች በደረሰባቸው ከባድ የዝናብ እጥረት ምክንያት ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ እየሆኑ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የዓይን እማኞች በከፍተኛ ኃዘን ገለጹ።

ባለፉት ሁለት ወራት ገደማ የአየር ንብረቱ ምቹ በመሆኑ በበልግ ወቅት የተዘሩት ሰብሎች በክፍል በጥሩ ሁኔታ ላይ የነበሩና ለውጤት ይበቃሉ ተብሎ ትልቅ ተስፋ የተጣለባቸው ቢሆንም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን አካባቢውን የገጠመው አስከፊ የዝናብ መቋረጥ የተስፋውን ጭልንጭል አጨልሞታል።

የአካባቢው አርሶ አደሮች ሕይወትና መተዳደሪያ በሆኑት እንደ በቆሎ እና ቦሎቄ ባሉ የእህል ሰብሎች፣ እንዲሁም ቦዬ፣ ጎዳሬ፣ ካሳቫ፣ ስኳር ድንች፣ ድቡልቡል ድንች፣ ዱባ እና ሌሎች በርካታ የተለያየ የጓሮ አትክልቶች ላይ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል። በዞኑ ባሉ ገጠራማ አካባቢዎች የሚኖሩት አርሶ አደሮቻችን ሕይወት ሙሉ በሙሉ በእነዚህ ሰብሎች ላይ ብቻ የተመሠረተ በመሆኑ፣ አሁን ላይ ተስፋ በሚያስቆርጥ ሁኔታ ዝናብ በመቅረቱ ምክንያት ሰብሎቹ በሙሉ በዓይን እያዩ ከጥቅም ውጪ ሆነው መቅረታቸውን እኛ ራሳችን ምስክሮች ነን።

ይህ ያጋጠመው ድንገተኛ የተፈጥሮ ፈተና በአካባቢው ላይ የከፋ የምግብ ዋስትና እጥረት እንዳያስከትል እና የአርሶ አደሩን ሕይወት አደጋ ላይ እንዳይጥል ከፍተኛ ስጋት የፈጠረ ሲሆን፣ አርሶ አደሩም ካለው የከፋ ጭንቀት የተነሳ ፈጣሪ ምህረቱን እንዲያወርድለት በፀሎትና በትሕትና እየተማጸነ ይገኛል። በመሆኑም ይህ የተደቀነው አደጋ በሰው ሕይወት ላይ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት፣ የረድኤት ድርጅቶችና በጎ አድራጊዎች ለአርሶ አደሩ አስቸኳይ ድጋፍ ለማድረግ ከወዲሁ እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ ቀርቧል።

በተያያዥም መላው ሕዝብና ቅዱሳን በሙሉ ይህንን አስቸጋሪ ወቅት በሰላም እንድንሻገር በፀሎትና በሐሳብ ከወላይታ አርሶ አደሮች ጎን እንዲቆሙ መልዕክት ተላልፏል።

ፈጣሪ አምላክ ምህረቱን ይላክ፤ ምድሪቱንም በዝናብ ይጎብኛት። 🙏

በኤሳሁን ተክሌ

12/06/2026

የልማት ጥሪ፦ ከዳሞት ሶሬ ወረዳ የሶሬ ቅልና ቀበሌ ተወላጆችና ወጣቶች የተላለፈ መልዕክት

ለሶሬ"ቅልና ቀበሌ እናቶችና ሕፃናት ንጹሕ ውሃና የኤሌክትሪክ ኃይል (ማብራት ይደርሳቸው ዘንድ ድምፅ እንሁን!"

በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የምትኖሩ ውድ የቅልና ቀበሌ፣ የዳሞት ሶሬ ወረዳ እና የወላይታ ዞን ተወላጆች፣ ወጣቶች፣ ምሁራን እንዲሁም የሚመለከታችሁ የልማት አጋሮች በሙሉ፤

እኛ የሶሬ ቅልና ቀበሌ ተወላጆችና ወጣቶች፣ ማኅበረሰባችን አሁንም ድረስ በ21ኛው ክፍለ ዘመን እጅግ መሠረታዊ የሆኑ የመሠረተ-ልማት አቅርቦቶች በመታጣታቸው ምክንያት እየደረሰበት ያለውን እንግልትና ስቃይ በጋራ ለመቅረፍና ለሚመለከተው አካል ድምፃችንን ለማድረስ ይህንን የልማት ጥሪ አቅርበናል።

09/06/2026

የተከበራችሁ የሥራ ኃላፊዎች፤

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሕዝቡን መሠረታዊ የልማትና የመሠረተ-ልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ጥረቶችን እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል። ይሁን እንጂ በወላይታ ዞን በዳሞት ሶሬ ወረዳ ሥር የሚገኘው የቅልና ቀበሌ ማኅበረሰብ አሁንም ድረስ እጅግ መሠረታዊ የሆኑትን የንጹሕ መጠጥ ውሃ እና የኤሌክትሪክ ኃይል (ማብራት) አቅርቦቶችን ሳያገኝ በመቅረቱ ምክንያት ለአስከፊ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተዳርጎ ይገኛል።

በቀበሌው ውስጥ የሚታዩት ዋና ዋና ተግዳሮቶች የሚከተሉት ናቸው፦

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Sodo?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address

ወላይታ
Sodo
ደጀ