ካቶሊክ እምነት ብርሃን

ካቶሊክ እምነት ብርሃን

Share

08/07/2026

“ሕፃኑም አደገ፥ ጥበብም ሞልቶበት በመንፈስ ጠነከረ፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ በእርሱ ላይ ነበረ።”
— ሉቃስ 2፥40

29/06/2026

፤ !!

✍️በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።
ዮሐንስ 3፥16

✍️አሁን ግን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ታይቶአል። እርሱ ሞትን ሽሮአልና እኔ ሰባኪና ሐዋርያ አሕዛብንም አስተማሪ እንድሆን በተሾምሁበት በወንጌል ሕይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን አውጥቶአል።
2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥10-11
ይህ አስተምዕሮ ነው።

# ጸጋ የትምህርት ርዕስ ሳይሆን ማንነት ነው፤ እርሱም ነው።

👉እኛ እውነትኛ አማኞች የዳነው #በጸጋ ነው፤ የሕይወታችን ለውጥም በዚው #ጸጋ ነው።

✍️በአጠቃላይ #ከጸጋው የተነጠለ ሕይወትም ኑሮም የለንም።

#ጸጋው ማንነታችን ነው።

✍️አንድ በእርግጠኛነት ይህንን #የጸጋ አስተምዕሮ በሙሉ ያመነና የተማረ እውነትኛ ክርስቲያን ኃጢአትን እንደፈለገ እያደረገና ልማዱ እያደረገ ፈጽሞ መኖር አይችልም።
ምክንያቱም ...👉

👉1ኛ ዮሐንስ 3፥9
ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኀጢአትን አያደርግም፤ የእርሱ ዘር በውስጡ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደም ኀጢአትን ሊያደርግ አይችልም።
1ኛ ዮሐንስ 3፥9 (አዲሱ መ.ት)

ሕያው ቃልን በደንብ አንብቡት ።

👉ቲቶ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤
¹²-¹³ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤

✍️ይህ ማለት ደግሞ ፈጽሞ ሊደክም አይችልም ማለት እንዳልሆነ ግልጽ ነው ።

ነገር ግን ከዚህ ድካም ማምለጫው ደሞ :-

👉እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።
ዕብራውያን 4፥16

..በዚህ መንገድ ይወጣል።

👉 #በጸጋ ድነናል ፤ ለዘላለም አንጠፋም።
👉 #ጸድቀናል በኃጢአታችን አይደለንም።

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Sodo?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address

Sodo
SODO