Oromoo KOO

Oromoo KOO

Share

Gaarummaan Ofumaaf✍️

29/08/2026

Confidensish temechegn Wly😆❤️

29/08/2026

በአባይ ቲቪ አስተያየት የሰጠችው ቲክቶከር ጃኒ ህጋዊ ተጠያቂነት ሊኖርባት እንደሚችል ጠበቃ ሰብለ አሰፋ ገለጹ

በኢትዮጵያ የማርሻል አርትስ (EtFC 2) ውድድር ወቅት ቲክቶከር ጃኒ ከአባይ ቲቪ ጋር ባደረገችው ቃለ ምልልስ ተወዳዳሪው ሴዶን በተመለከተ የሰጠችው አስተያየት ከህግ አንጻር ተጠያቂነት ሊያስከትልባት እንደሚችል ጠበቃ ሰብለ አሰፋ ተናግረዋል።

እንደ ጠበቃ ሰብለ ማብራሪያ፣ ግለሰቧ የሰጠችው አስተያየት በሁለት መልኩ ሊታይ ይችላል፦

• ተወዳዳሪው የውድድሩን የተጋፋጭነት ባህሪ እና ቴክኒክ ለመግለጽ ከሆነ፣ ግለሰቧ ተወዳዳሪውን በተክኒኩ ያሸንፋል ብላ የገመተችበት በመሆኑ የታሰበ ጉዳት የለውም ሊባል ይችላል።

• ነገር ግን አባባሉ የተወዳዳሪውን ስምና ክብር የሚመለከት ሆኖ ከተገኘ፣ በህግ ማዕቀፍ መሠረት ተጠያቂ ልታደርጋት ይችላል። ይህ ጉዳይ አግባብ ባለው ህግ መሠረት በግለሰቦች መካከል የሚታይ መሆኑን ጠበቃዋ ጠቁመዋል።

በኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 615 መሠረት በስድብ እና ማዋረድ ወንጀል ሊያስጠይቃት ይችላል። ይህ ወንጀል በቀሊል እስራት (እስከ 3 ወር በሚደርስ) ወይም በመቀጮ ሊያስቀጣ እንደሚችል ጠበቃዋ ጠቁመዋል።

ተጎጂው ወገን ጉዳዩን ወደ ህግ ከወሰደው፣ ግለሰቧ በይፋ ይቅርታ በመጠየቅ ጉዳዩን ማስተካከል የምትችል ሲሆን፤ ተወዳዳሪው ሴዶም በተመሳሳይ ደረጃ ምላሽ የሰጠ ከሆነ ፍርድ ቤቶች ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት የተጠያቂነት ደረጃውን ሊያቃልሉ እንደሚችሉ ተገልዟል።

ጠበቃ ሰብለ አሰፋ አክለውም፣ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ አካላት በማህበራዊ ሚዲያም ሆነ በዋና ዋና መገናኛ ብዙኃን የሚናገሯቸውን ንግግሮች በጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በተጨማሪም እንደ አባይ ቲቪ ያሉ የመገናኛ ብዙኃን የሰዎችን ስም ሊነኩ የሚችሉ የቃለ ምልልስ ክፍሎችን ሳይቆርጡ በቀጥታ ማስተላለፋቸው ከጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር አኳያ ጥያቄ የሚያስነሳ እና ግለሰቧንም ላልተፈለገ ውዝግብ የዳረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

Via ጠበቃ ሰብለ አሰፋ

ጉርሻ page

🌴🌴🌴

Photos from Addis Ababa Police's post 27/08/2026
Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Shashemene?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address

Ethiopian
Shashemene
1000