10/04/2025
🔥ደሴ ከነማ በቀጣይ አርብ ወሳኝ ጨዋታ ያረጋል🔥
=======================================
✅ደሴ ከነማ ትናንት የሱ ተቀናቃኞች ነጥብ መጣላቸውን ተከትሎ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ለማደግ የሚያረገው ጥረት እንደገና ተነሳስቷል በተለይ በቀጣይ ሀላባ ከ ነገሌ መጫወታቸውን ተከትሎ ደሴ ሌላ ትልቅ እድል ከፊት ተቀምጧል ከኛ የሚጠበቀው ከስከዛሬው በተለየ መልኩ ያሉትን ክፍተቶች በመድፈን ለማሸነፍ በመጣር ነገሮችን በራሳችን መወሰን አለብን!!!
✅በተለይ ቡድኑ ከጫና ወቶ ልክ እንደማንኛውም ወሳኝ ጨዋታ በማየት ያለ ጫና በመጫወት የፊት መስመሩን ከአባካኝነት በመንፃት የተገኙ እድሎችን በአግባቡ በመጠቀም ነገሮችን በመስራት የራሳችንን እድል በራሳችን መወሰን እንችላለን!!!
✅በተለይ የአሰልጣኝ እስታፍ አባላት ቡድኑ የተገኙ እድሎችን በአግባቡ ለመጨረስ የፊት መስመሩ ላይ ትኩረት አድርጋችሁ ብሰሩ የተሻለ ይመስለናል ሌላው ጠንካራ ስለሆነ የፊት መስመሩን አጨራረስ ላይ በደንብ ስሩበት እንላለን!!!
✅ይህ ደጋፊ ከናንተ ጉን ነው ሁሌም አርብም ከናንተ ጋር በስታዲየም ይገኛል በነገሌ ጨዋታ የተከፋ ደጋፊ በቀጣይ በሻሸመኔ ጨዋታ ላይ በመካስ ደጋፊዎች ልታስደስቱ ይገባል የተገኝውን ወርቃማ እድል በአግባቡ መጠቀምም አስፈላጊ ነው ብለን ስለምናምን የአርብ ጨዋታ በትኩረት ሰታችሁ ተዘጋጅበት እኛ ከናንተ ጉን ነን ሁሌም!!!
(ድል እና ስኬት ለቅኝቶቹ ደሴ ከነማ ይሁን)
07/04/2025
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ የ19 ኛ ሳምንት ውጤቶች በኋላ የደሴ ከነማ በደረጃ ሰንጠረዡ ከመሪው አርሲ ነገሌ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት በ2 ነጥብ ዝቅ ብሎ 38 ነጥቦቹን ይዞ ይከተላል። ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ለማደግ በሚደረገው የመጨረሻ ጨዋታዎች ትንቅንቅ የራሱን የቤት ሥራውን በመወጣት በስኬት እንደሚያጠናቅቅ ተስፋ እናደርጋለን።
ጉዞ ወደ ፕሪሚየር ሊግ 🙋♂️
17/03/2025
⚽️የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ16ተኛ ሳምንት ጨዋታ
ደሴ ከነማ ከ ሱሉልታ ክ/ከተማ
ማክሰኞ መጋቢት 9
7 ሰአት-️ በአበበ በቄላ ስታዲየም
መልካም ዕድል ለቅኝቶቹ
17/03/2025
✅በ16 ሳምንት ጨዋታዎች ሀላባ ሽንፈት ሲያጋጥመው ነገሌ አሸንፏል ደሴ ደሞ ነገ ይጫወታል በዛሬው የነገሌ ከ አዲስአበባ ዩኒቨርስቲ ጋር ጨዋታውን ለመከታተል ሞክሬ ነበር አዲስ አበባ ከፍተኛ ሊግ ከቆየ በጣም ይገርመኛል ጭራሽ ለከፍተኛ ሊግ የሚመጥን ቡድን አለመሆኑን በትክክል አይቻለሁ!!!!
✅ወደ እኛ ቡድን ስመል ነገ 7 ሰአት ከሱሉልታ ክ/ከተማ ጋር ወሳኝ ጨዋታ አለበት አቻ ሆነ ድል ማረግ የሚችል ከሆነ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ከሀላባ የሚረከብ ይሆናል በነገራችን ላይ ግን ሱሉልታ በሁለተኛው ዙር ጠንከር ብለው ከመጡ ቡድኖች ዋነኛው ነው ጠንካራ ፍልሚያ ደሴ ይጠብቀዋል በነገው ጨዋታ!!!
✅ደሴ ከነማ የነገው ጨዋታ እና ቀጣይ ሳምንት እሁድ 10 ሰአት ላይ ነገሌ አርሲን የሚገጥምበት ሁለት ጨዋታዎች እጅግ ወሳኝ ናቸው ሁለቱን ጨዋታዎች በብቃት ማስተዳደር ከተቻለ የምናስበውን ለማሳካት ዋነኛ ሁነቶች ሊሆኑ ይችላሉ!!!!
t.me/dessiecity123
17/03/2025
9ኛው የመላው ደሴ ስፖርታዊ ዉድድር "ስፖርት ለሠላም ሠላም ለሁሉም"! በሚል መሪ ቃል ከፍተኛ ፉክክር እየታየበት እንደቀጠለ ነው።
⚽️ በእግርኳስ
👉 አራዳ ክፍለ ከተማ ቁርቁር 3ለ1
👉ሆጤ ክፍለከተማ ቦሩሜዳን 10ለ0 ሲያሸን
🥎በመረብ ኳስ
👉 ሰኞ ገበያ ክፍለከተማ ሆጤ ክፍለከተማ እንድሁም
👉መናፈሻ ክፍለከተማ ገራዶ ክላስተርን በተመሳሳይ 3ለ1 በሆነ ውጤት ሲያሸንፉ የካራቴ፣ የአትሌቲክስ እና የቼስ ስፖርት የማጣሪያ ውድድር እየተካሄዱ ነው።
~•~•
🕊ስፖርት ለሰላም ሰላም ለሁሉም🕊
28/10/2024
ደሴ ከነማ
የወሎነት አርማ
ዛሬ 10 ሰዓት ላይ ከሀላባ ከነማ ጋር ይጫወታል።
መልካም ዕድል ለክለባችን 😍