12/01/2020
የኢትዮጵያ 1ኛ ሊግ ምድብ 3 ከ 4ኛ ሳምንት ጨዋታ በኋላ የደረጃ ሰንጠረዡ ይህንን ይመስላል...
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Yeab soccer league one, Sports Event, Gonder, Debark'.
12/01/2020
የኢትዮጵያ 1ኛ ሊግ ምድብ 3 ከ 4ኛ ሳምንት ጨዋታ በኋላ የደረጃ ሰንጠረዡ ይህንን ይመስላል...
12/01/2020
የኢትዮጵያ 1ኛ ሊግ 4ኛ ሳምንት ጨዋታ ውጤቶች....
10/01/2020
የሳምንቱ ተጠባቂ የደርቢ ጨዋታ ዳንግላ ላይ ይደረጋል........
🔶ዳንግላ ከነማ🔶 vs 🔴እንጅባራ ከነማ🔴
🕘9:00
🏟ዳንግላ እስቴዲየም
08/01/2020
ከበዓል መልስ የኢትዮጵያ 1ኛ ሊግ ምድብ 3 ሲቀጥል በርካታ ጨዋታወች ይጠበቃሉ!!!
03/05/2012
🔵 የጁ ፍሬ ወልዲያ ከ ጎጃም ደ/ማርቆስ
የጁ ወልዲያ ባለፈው ሳምንት ከሜዳው ውጭ ያልተጠበቀ ሽንፈት አስተናግዶ እስካሁን ምንም ግብ ያላስተናገደውን ጎጃም ደ/ማርቆስ በሜዳው ይገጥማል።
🔹አውስኮድ ከ ላስታ ላሊበላ
አውስኮድ ባለፈው ሳምንት የምድቡን መሪነት በሽንፈት ሲነጠቅ በአንፃሩ ላሊበላ የመጀመሪያ ድሉን አስመዝግቦ በጥሩ ስነ-ልቦና ላይ ይገኛል።
🔶ዳንግላ ከነማ ከ እንጅባራ ከነማ
ዳንግላ ከሜዳው ውጭ 1ነጥብ ይዞ የተመለሰ ሲሆን እንጅባራ የምድቡ መሪነት የሚያጠናክርበትን ውጤት ያስመዘግባል ተብሎ ይጠበቃል ።
🔷ደባርቅ ከነማ ከ መርሳ ሀብሩ
ደባርቅ ዘንድሮ ጥሩ ግስጋሴ ላይ ይገኛል ባለፈው ሳምንት ከሜዳው ውጭ 1ነጥብ አስመዝግቧል በአንፃሩ መርሳ ባለፈው ሳምንት በሜዳው ነጥብ በመጋራቱ በዚህ ጨዋታ ወደ አሸናፊነት ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል።
✅ዳሞት ከነማ ከ አምባ ጊዮርጊስ
ባለፈው ሳምንት አራፊ የነበረው ዳሞት ለዚህኛው ጨዋታ በቂ ዝግጅት አድርጓል በአንፃሩ አምባ ጊዮርጊስ እስካሁን ምንም ድል አላስመዘገበም።
የሳምንቱ አራፊ ክለብ አማራ ፖሊስ ነው።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
01/01/2020
🤶🎅ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች🎅🤶
እንኳን ለጌታችን ለመደኀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!
በዚህ ሳምንት ሙሉ ጨዋታወች የተራዘሙ ሲሆን የገና በዓልን እንጅባራ ከነማ የምድቡ አናት ላይ ተቀምጦ ይመራል።
ዘንድሮ ምድብ3 በአጓጊ ፉክክር ውስጥ ይገኛል። ከሳምንት ሳምንት አስገራሚና ያልተጠበቁ ሁነቶች የሚከሰቱበት ምድብ ሆናል።
እኛም እነዚህን እውነታወች በትኩሱና በዘመናዊ አቀራረብ ማድረሳችንን እንቀጥላለን። ውድ የፔጃችን ቤተሰቦች የናንተ አስተያየት ትልቅ ዋጋ አለውና ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት ያጋሩን።
🎄🌲🎄መልካም የገና በዓል🌲🎄🌲
31/12/2019
ውድ የ ቤተሰቦች...
ይህ ገፅ በኢትዮጵያ 1ኛ ሊግ ላይ ትኩረቱን በማድረግ ትኩስና ወቅታዊ እንዲሁም የጨዋታ መርሀ ግብሮችን ከትንታኔ ጋር በትኩሱ እያደረሰ ያለና በተለይም ምድብ3 ላይ በዘመናዊ መልኩ ዘገባወችን ለተከታዮቻችን እያቀረብን መሆኑ ይታወቃል።
ስለሆነም በዚህ ገፅ ድርጅትወን ቢያስተዋውቁና እስፖንሰር ቢያደርጉ ትርፋማ ይሆናሉ...
ለበለጠ መረጃ 0940915824 በመደወል ወይም ላይ ይፃፉልን...
ገፃችን sher በማድረግ አጋርነታችሁን አሳዩን...
የፌስቡክ ገፃችንም ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/110719157075157/posts/124447822368957/?app=fbl
በቴሌግራም ቻናላችን t.me/yeabsoccerleaguone ይቀላቀሉ
29/12/2019
በኢትዮጵያ 1ኛ ሊግ ምድብ3 ሶስተኛ ሳምንት ጨዋታወች ያልተጠበቁ ውጤቶች ተመዝግበዋል..
የተጠበቀው የደርቢ ጨዋታ በ1አቻ ውጤት ተጠናቋል በበርካታ ደጋፊወች የታጀበው ጨዋታ ተመጣጣኝና አዝናኝ ደጋፊወችን ቁጭ ብድግ ያደረገ ጨዋታ ነበር በጨዋታው ደባርቅ ከነማ ቀድሞ ግብ በማስቆጠር መምራት ቢችልም አምባ ጊዮርጊሶች በሜዳቸው ነጥብ መጋራት ችለዋል።
ሌላኛው ጨዋታ እንጅባራ ከነማ የምድቡን መሪ የነበረውን አውስኮድን አስተናግዶ ምድቡን መምራት የቻለበትን ውጤት አስመዝግቧል። በጨዋታው እንጅባራ የተሻለ የማጥቃት እንቅስቃሴ አሳይቷል በአንፃሩ አውስኮድ ጨዋታውን ለመቆጣጠር ሙከራ ቢያደርግም ከሜዳው ውጭ ሽንፈት አስተናግዷል።
በበርካታ ደጋፊወች ድባብ የታጀበው የጎጃም ደ/ማርቆስና አማራ ፖሊስ ጨዋታ ጠንካራ ፉክክር ተስተናግዶበታል ሆኖም አ.ፖሊስ የደጋፊውን ድባብ ተቋቁመው ነጥብ መጋራት ችለዋል።
መርሳ ከነማ ዳንግላን አስተናግዶ ነጥብ ሲጋራ ዳንግላ ከነማ የተሻለ እንቅስቃሴ አሳይቶናል በአንፃሩ መርሳ በሜዳው ነጥብ ያገኛል ተብሎ ቢጠበቅም አልተሳካም።
በሳምንቱ ያልተጠበቀው ውጤት ላሊበላ ላይ ተመዝግቧል። ዘንድሮ ጥሩ ብቃት ላይ ያልነበረው ላስታ ላሊበላ በሜዳው ጠንካራውን የጁ ፍሬ ወልዲያ አስተናግዶ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል።
በሳምንቱ ዳሞት ከነማ አራፊ ነበር
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ የቴሌግራም
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
29/12/2019
በኢትዮጵያ 1ኛ ሊግ ምድብ3 3ኛ ሰምንት ጨዋታወች:-
ተጠባቂው የደርቢ ጨዋታ 1አቻ ሲጠናቀቅ እንጅባራ መሪ የሚያደርገውን ውጤት አስመዝግቧል ጎጃም ደ/ማርቅስ እና መርሳ ከነማ በሜዳቸው ነጥብ ተጋርተዋል ላስታ ላሊበላ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል።
ሙሉ ዘገባውን ከደረጃ ሰንጠረዥ ጋር 2ሰዓት ይጠብቁን....
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ የቴሌግራም
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
25/12/2019
የኢትዮጵያ 1ኛ ሊግ 3ኛ ሳምንት ጨዋታወች በተለያዮ ከተሞች ይጠበቃሉ...
🔶አምባ ጊዮርጊስ vs ደባርቅ ከነማ
ይህ ጨዋታ ከሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታወች ዋነኛው ነው አምባ ጊዮርጊስ ከሽንፈት መልስ በሜዳው ጣፋጭ ድል ያስመዘገበውን ደባርቅ ከነማን ያስተናግዳል ከምባ ጊዮርጊስ በሜዳውና ደጋፊው ፊት የሚያደርገው ጨዋታ ቢሆንም ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የደባርቅ ከነማ ደጋፊወች የጨዋታው ድምቀት ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል በተጨማሪም ጨዋታው የደርቢነት ስሜት የተላበሰ ነው።
🔷መርሳ ከነማ vs ዳንግላ ከነማ
ዘንድሮ መርሳ ተጠናክሮ ቀርቧል ባለፈው ሳምንት ባህርዳር ላይ ሽንፈት ቢያስተናግድም ቡድኑ አሳማኝ ወቅታዊ ብቃት ላይ ይገኛል ዳንግላ ባንፃሩ በሜዳው ድል ማድረግ ቢችልም ከሜዳው ውጭ የሚያደርውን ጨዋታ ነጥብ ይዞ ለመመለስ ጠንካራ ዝግጅት ላይ ነው።
🔴እንጅባራ ከነማ vs አውስኮድ
በሳምንቱ ከሚጠበቁ ጨዋታወች አንዱ ነው እንጅባራ ባለፈው ሳምንት ከሜዳው ውጭ ሽንፈት አስተናግዶ ምድቡን በመምራት ላይ የሚገኘውን አውስኮድ ይጋብዛል ጨዋታው ጠንካራ ፉክክር ይታይበታል።
🔸ላስታላሊበላ vs የጁ ፍሬ ወልዲያ
ላሊበላ ዘንድሮ ጥሩ ብቃት ላይ አይገኝም ሁለቱንም ጨዋታወች ተሸንፋል በተለይ የተከላካይ ክፍሉ መሳሳት በጉልህ ታይቷል ይህ ደግሞ በፈጣን ማጥቃት ለሚንቀሳቀሰው የጁ ትልቅ አጋጣሚ ነው።
❇️ጎጃም ደብረ ማርቆስ vs አማራ ፖሊስ
ባለፈው ሳምንት አራፊ የነበረው ደብረ ማርቆስ በሜዳው የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደርጋል በተለይ ጨዋታ በናፈቀው ደጋፊ ፊት የሚያደርገው ጨዋታ በሁለተኛው ሳምንት በጎል ተንበሽብሾ ድል ያደረገውን አማራ ፖሊስ ያስተናግዳል ጨዋታው ተጠባቂ ነው።
✅ዳሞት ከነማ የሳምንቱ አራፊ ቡድን ነው
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ የቴሌግራም
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
ዘገባወቻችን ከተመቻችሁ sher ያድርጉ
24/12/2019
🔷🔶 አቶ ጀማልና ቤተሰቦቹ ለዳንግላ ከነማ ሙሉ የመጫወቻ ታኬታ ድጋፍ አደረጉ!
በተጨማሪም አቶ ጀማልና ቤተሰቦቻቸው ከክለቡ ፕሬዘዳንት ጋር ባደረጉት ውይይት ከዚህ በኋላ ከክለቡ ጎን በመቆም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።
©Dangla kenema fc
ከፌስ ቡክ ገፃችን በተጨማሪ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
23/12/2019
👉የኢትዮጵያ 1ኛ ሊግ በኢትዮጵያ የእግር ኳስ ደረጃ 3ኛው እርከን ላይ ይገኛል።
ሊጉ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙትን ክለቦች በማገናኘት የመጀመሪያው እከን ላይ ነው።
🎯የህ ሊግ በርካታ ክለቦች በጠንካራ ፉክክር አመቱን ሙሉ የሚዘልቁበት ሊግ ነው።
🎧ሆኖም ሊጉ አስፈላጊውን ሽፋን እየተደረገለት አልነበረም...
🧩ውድድሩን ሽፋን ለመስጠት የተለያዮ ገፆች በተለያየ ጊዜ በራስ ተነሳሽነት ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል።
ከእነዚህም ውስጥ 🔵 አንደኛው ነው... ይህ የግል የፌስቡክ አካውንት ከ2004 ጀምሮ ሊጉን ሽፋን በመስጠት 8ዓመታትን ከሊጉ ጋር በብዙ ፈተናወች መሀል ተጉዟል።
🔴 ይህ ሊጉን የተሻለ ሽፋን በመስጠትና ተከታታይ ዘገባወችን በማቅረብ ታማኝና ወቅታዊ የሆኑ መረጃወችን የሚያደርስ የተደራጀ ገፅ ነው።
⚫️ ይህኛው ገፅ የሊጉን ሽፋን የተሻለ ዘመናዊ አድርጎ ለማስቀጠል የተከፈተ አዲስ ገፅ ነው።
🔔ሁሉም ገፆች በራስ ተነሳሽነት የተጀመሩም ከመሆናቸው በላይ መረጃን ለተጠቃሚወች በፍጥነትና በጥራት ለማድረስ ብዙ መስዋትነት ተከፍሎበታል።
💣ይሁንና ከነዚህ ገፆች አንዱ የሆነው በተለይም በወጪ ምክንያት ስራውን ለማቆም እየተገደደ ይገኛል።
ገፁ ለሊጉ ትልቅ ባለውለታ ወሆኑ የማይዘነጋ ነው ሆኖም ያለምንም እስፖንሰርነት በማገልገሉ አሁን ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ላይ ይገኛል። ገፁም የርዳታ ጥሪውን በይፋ አሳውቋል።
ዛሬ ይህንን ገፅ አየን እንጅ ሌሎቹም ገፆች ተመሳሳይ እጣፋንታ ውስጥ ናቸው።
ስለሆነም ለእስፖርት ቤተሰቡም ሆነ ለባለሀብቱ ማስተላለፍ የምንፈልገው እነዚህን ገፆች እስፖንሰር በማድረግ የኢትዮጵያ 1ኛ ሊግን ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት ያግዙ ስንል እንጠይቃለን።
like comment sher ያድርጉ