ለሀላባ የፈረመው ተጫዋች አንድ ሳምንት ሳይሞላ ለወልዋል ፈረመ
ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ጋር ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ልክ የዛሬ ሳምንት ለአዲስ አዳጊው ሀላባ ከተማ ፈርሞ የነበረው የግራ መስመር ተከላካዩ ኪሩቤል ወንድሙ ዛሬ ደግሞ በወልዋሎ ለመጫወት ውሉን አራዝሟል።
Halaba Tube
Develope on
05/08/2026
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአሰራር ክፍተትና የዝውውር ስርዓቱ መላላት .!
በሀገራችን እግር ኳስ ውስጥ በየጊዜው የምንታዘባቸው አሰራርን የጣሱ ድርጊቶችና የተጫዋቾች ዝውውር ምስቅልቅሎች የስፖርቱን እድገት ወደኋላ እየጎተቱት ይገኛሉ።
ከቀናት በፊት ለአዲስ አዳጊው ሀላባ ከተማ በይፋ ተፈርሞ ማልያ የለበሰው የግራ መስመር ተከላካዩ ፣
ሳምንት እንኳ ሳይሞላው ዛሬ ደግሞ ከቀድሞ ክለቡ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር ውሉን ማራዘሙ ይፋ ሆኗል።
ይህ ድርጊት የተጫዋቹን ሙያዊ ስነ-ምግባር አጠያያቂ የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ፣ በዋናነት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (EFF) ዘመናዊ፣ ግልጽና ጠንካራ አሰራር ባለመዘርጋቱ ምክንያት የተፈጠረ ትልቅ የስርዓት ውድቀት ማሳያ ነው።
ዋና ዋና የአሰራር ጥሰቶችና ድክመቶች
የዲጂታል እና የተማከለ የመዝገብ ስርዓት (TMS/CAMS) ማነስ፦
አንድ ተጫዋች ከአንድ ክለብ ጋር ውል ሲፈራረም ወዲያውኑ በፌዴሬሽኑ የመረጃ ቋት (Database) ውስጥ ተመዝግቦ የዝውውር ሂደቱ ሕጋዊ ጥቃሜ ማግኘት ሲገባው፣ የህጋዊ ምዝገባ ስርዓቱ መላላት ተጫዋቾች በአንድ ጊዜ የሁለት ክለቦችን ማልያ ለብሰው እንዲታዩ እድል ፈጥሯል።
የተጫዋቾችና የኤጀንቶች ሙያዊ ኃላፊነት ማጣት፦
ተጫዋቾች ለፈረሙበት ውልና ለሰጡት ቃል ኪዳን ተገዢ አለመሆናቸው፣ እንዲሁም የክለቦችን የገንዘብና የጊዜ ድካም የፕሮፌሽናሊዝም እጥረት መኖሩን ያሳያል።
የተጠያቂነትና የጠንካራ ቅጣት አለመኖር፦
ፌዴሬሹ በድርብ ውል (Double Contracting) እና በውል መጣስ ዙሪያ አፋጣኝ፣ ግልጽና የማስተማሪያ ውሳኔዎችን የማያስተላልፍ ከሆነ፣ ክለቦች ለፋይናንስ ብክነትና ለስነ-ልቦናዊ መረበሽ መጋለጣቸው ይቀጥላል።
የ J Sport መደምደሚያ፦
የኪሩቤል ወንድሙ አጋጣሚ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ትልቅ የማቂያ ደወል ነው። ፌዴሬሽኑ ሕግና ደንቦችን በጥብቅ የማስፈጸም፣ የዝውውር መስኮቱን በአስተማማኝ ቴክኖሎጂ የመቆጣጠር እና እንዲህ ባሉ ህገ-ወጥ ድርጊቶች ላይ ጠንካራ እርምጃ የመውሰድ ኃላፊነቱን በአስቸኳይ መወጣት አለበት። አለበለዚያ የሊጉ ተሰማኝነት እና የክለቦች ህጋዊ ከበሬታ አደጋ ላይ መውደቁ አይቀሬ ነው።
ሀላባ ከነማ የነባር ተጫዋቾቹን ውል ማራዘሙን ቀጥሏል!!!
በአዲሱ የውድድር ዘመን ጠንካራ እና ተፎካካሪ ቡድን ለመገንባት የቅድመ ዝግጅት ስራዎቹን አጠናክሮ የቀጠለው ሀላባ ከነማ የአዳዲስ ተጫዋቾች ዝውውር ጎን ለጎን የነባር ተጫዋቾቹን ውል በማራዘም ላይ ይገኛል።
በዛሬው ዕለትም የሶስት ቁልፍ ተጫዋቾቹን ውል ያራዘመ ስሆን ውላቸውን ከራዘሙት ውስጥም ሰይድ ግርማ፣ አብዲልከሪም ራመቶና ክሩቤል ፍቅረማርቆስ ይገኙበታል።
ክለቡ በቀጣይ ዓመት በውድድሩ ስኬታማ እና ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን የሚያስችሉትን የተለያዩ ዝግጅቶች በተጠናከረ መልኩ ቀጥሏል።
04/08/2026
የሀላባ ከነማ ግብ ጠባቂውን ውል አራዘመ!!!
ባሳለፍነው ውድድር ዓመት ከሀላባ ከነማ ጋር ድንቅ ግዜን ያሳለፈው ግብ ጠባቂ አባቱ ጀርሶ ከሀላባ ከነማ ጋር የሚያቆየውን ውል አራዝሟል።
03/08/2026
የኳስ ስፔሻሊስቱን ትልቅ ዜና እየጠበቅን ነው
Tsega D Royal Fam
03/08/2026
ሀላባ ከነማ የነባር ተጫዋቾቹን ውል ማራዘሙን ቀጥሏል!!!
በአዲሱ የውድድር ዘመን ጠንካራ እና ተፎካካሪ ቡድን ለመገንባት የቅድመ ዝግጅት ስራዎቹን አጠናክሮ የቀጠለው ሀላባ ከነማ የአዳዲስ ተጫዋቾች ዝውውር ጎን ለጎን የነባር ተጫዋቾቹን ውል በማራዘም ላይ ይገኛል።
በዛሬው ዕለትም የሶስት ቁልፍ ተጫዋቾቹን ውል ያራዘመ ሲሆን ውላቸውን ካራዘሙት ውስጥም ሰይድ ግርማ፣ አብዲልከሪም ራመቶና ክሩቤል ፍቅረማርቆስ(ሳከር) ይገኙበታል።
ክለቡ በቀጣይ ዓመት በውድድሩ ስኬታማ እና ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን የሚያስችሉትን የተለያዩ ዝግጅቶች በተጠናከረ መልኩ ቀጥሏል።
በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የክረምት ወራት እግር ኳስ ሻምፒዮና በድምቀት ጀምሯል።
ሀላባ ከነማ ሴኔጋላዊውን የተከላካይ አማካይ በዛሬው ዕለት የግሉ አድርጓል።
ለ2019 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በጠንካራው ለመቅረብ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘው ሀላባ ከነማ ሴኒጋላዊውን ሴክ ሳምባን ለማስፈረም ተስማምቷል
ሴክ በሲኔጋል ሊግ ለUS ouakam ከ2022 ጀምሮ በቋሚነት ቡድኑን ሲያገለግል የነበረና ባሳለፍነው የውድድር አመት በ26 ጨዋታዎች በቋሚነት በመሰለፍ 2,100 ደቂቃዎችን መጫወት የቻለ በcenteral midfielder እንዲሁም defensive midfielder ሆኖ መጫወት የሚችል ተጫዋች መሆኑን የተጫዋቹ ስታትስቲክስ ያሳያል።
01/08/2026
በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የክረምት ወራት እግር ኳስ ሻምፒዮና በድምቀት ጀምሯል።
ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የክረምት ወራት እግር ኳስ ሻምፒዮና በዛሬው ዕለት በድምቀት ጀምሯል።
የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ገመዳ መሀመድ በቦታው በመገኘት የዕለቱን ጨዋታ አስጀምረዋል።
በዚህ መክፈቻ ጨዋታ ከ15 ዓመት በታች ቀይ ዛላ ከዋንጃ አቻው ጋር እየተጫወቱ ይገኛሉ።
በአጠቃላይ በዚህ ጨዋታ ከ30 በላይ የእግር ኳስ ቡድኖች የሚሳተፉ ስሆን ብቃት ያለቸውን ተጨዋቾች ለማፍራት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተገልጿል።
01/08/2026
በመክፈቻ ጨዋታ ቀይ ዛላ ዋንጃን 4 - 2 በሆነ ውጤት አሸነፈ።
በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የክረምት እግር ኳስ ሻምፕዮና ውድድር በዛሬው ዕለት መጀመሩ ይታወሳል።
በዚሁ መክፈቻ ጨዋታ የቀይ ዛላ ከ15 ዓመት በታች ቡድን ከዋንጃ አቻው የተጫወተ ስሆን ጨዋታው በዛላ 4 - 2 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
Alaba K'ulito