FMC Sport

FMC Sport

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from FMC Sport, Sports, Addis Ababa.

Photos from FMC Sport's post 16/08/2026

ባርሴሎና ሮድሪን ከማንቼስተር ሲቲ ለማስፈረም ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ባርሴሎና ስፔናዊውን የመሐል ሜዳ ተጫዋች ሮድሪ ከማንቼስተር ሲቲ ለማስፈረም ተስማምቷል።

ሮድሪ በባርሴሎና ለ4 ዓመታት የሚያቆየውን ውል እንደሚፈራረም ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

የ30 ዓመቱ ተጫዋች በማንቼስተር ሲቲ ቤት ቆይታው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ እና የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን ጨምሮ የተለያዩ ዋንጫዎችን አሳክቷል።

Photos from FMC Sport's post 16/08/2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ 2ኛ ጨዋታውን የሚያደርግበት ቀን ታወቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ 2ኛ ጨዋታውን የሚያደርግበት ቀን ታወቀ፡፡

በዚህም መሰረት በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ 10 ሁለተኛ የምድብ ጨዋታውን ከሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ጋር በባህር ዳር ስታዲየም መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ የሚያከናውን ይሆናል።

ካፍ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የሜዳ ጨዋታውን በባህር ዳር ስታዲየም እንዲያከናውን ጊዜያዊ ፈቃድ መስጠቱ ይታወሳል።

ዋልያዎቹ ለ2027 የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች ዝግጅታቸውን መጀመራቸው ይታወቃል፡፡

Photos from FMC Sport's post 16/08/2026

አርሰናል የኮሚዩኒቲ ሺልድ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አርሰናል ማንቼስተር ሲቲን 3 ለ 0 በማሸነፍ የኮሚዩኒቲ ሺልድ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆኗል።

የአርሰናልን የማሸነፊያ ግቦች ካላፊዮሪ፣ ሀቨርትዝ እና ኦዴጋርድ አስቆጥረዋል።

አርሰናል በታሪኩ 18ኛ የኮሚዩኒቲ ሺልድ ዋንጫውን አሳክቷል።

Photos from FMC Sport's post 16/08/2026

የኮሚዩኒቲ ሺልድ የፍጻሜ ጨዋታ አሰላለፍ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኮሚዩኒቲ ሺልድ የፍጻሜ ጨዋታ አርሰናል እና ማንቼስተር ሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

ሁለቱም ቡድኖች በመጀመሪያ አሰላለፍ ወደ ሜዳ ይዘውት የሚገቡትን አሰላለፍ ይፋ አድርገዋል፡፡

አርሰናል በኮሚዩኒቲ ሺልድ ዋንጫ ታሪክ 17 ጊዜ ሻምፒዮን ሲሆን፤ ተጋጣሚው ማንቼስተር ሲቲ በበኩሉ 7 ጊዜ ዋንጫውን አሳክቷል፡፡

አርሰናል ለመጨረሻ ጊዜ የኮሚዩኒቲ ሺልድ ዋንጫን ያሳካው በ2023/24 የውድድር ዓመት ሲሆን ማንቼስተር ሲቲ ደግሞ በ2024/25 ዋንጫውን ለመጨረሻ ጊዜ ማንሳቱ ይታወሳል፡፡

በኮሚዩኒቲ ሺልድ ዋንጫ ታሪክ ማንቼስተር ዩናይትድ 21 ጊዜ ሻምፒዮን በመሆን ቀዳሚው ክለብ ነው፡፡

የሁለቱ ቡድኖች ተጠባቂ ጨዋታ አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ መደረግ ይጀምራል፡፡

Photos from FMC Sport's post 16/08/2026

አርሰናል ከማንቼስተር ሲቲ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኮሚዩኒቲ ሺልድ የፍጻሜ ጨዋታ አርሰናል እና ማንቼስተር ሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

አርሰናል የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ በማሳካት ማንቼስተር ሲቲ ደግሞ የኤፍኤ ካፕ ዋንጫን በማሸነፍ በኮሚዩኒቲ ሺልድ የፍጻሜ ጨዋታ ተገናኝተዋል፡፡

አርሰናል በኮሚዩኒቲ ሺልድ ዋንጫ ታሪክ 17 ጊዜ ሻምፒዮን ሲሆን፤ ተጋጣሚው ማንቼስተር ሲቲ በበኩሉ 7 ጊዜ ዋንጫውን አሳክቷል፡፡

አርሰናል ለመጨረሻ ጊዜ የኮሚዩኒቲ ሺልድ ዋንጫን ያሳካው በ2023/24 የውድድር ዓመት ሲሆን ማንቼስተር ሲቲ ደግሞ በ2024/25 ዋንጫውን ለመጨረሻ ጊዜ ማንሳቱ ይታወሳል፡፡

በኮሚዩኒቲ ሺልድ ዋንጫ ታሪክ ማንቼስተር ዩናይትድ 21 ጊዜ ሻምፒዮን በመሆን ቀዳሚው ክለብ ነው፡፡

በአርሰናል እና ማንቼስተር ሲቲ መካከል የሚደረገው የኮሚዩኒቲ ሺልድ የፍጻሜ ጨዋታ አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ ይደረጋል፡፡

Photos from FMC Sport's post 15/08/2026

የባሕር ዳር ስታዲየም ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ማስተናገድ የሚያስችለውን የካፍ ፍቃድ አገኘ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የባሕር ዳር ስታዲየም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ዝቅተኛ መመዘኛ በማሟላት ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ማስተናገድ የሚያስችለውን ፍቃድ አግኝቷል፡፡

የአማራ ክልል ባሕል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ጋሻው ተቀባ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፥ የካፍን መስፈርቶች በመከተል ስታዲየሙ ለዓለም አቀፍ ውድድሮች ብቁ እንዲሆን በርካታ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡

በተለይም የተጫዋቾች ማረፊያ ክፍል ደህንነት፣ የልዩ እንግዳ ቦታዎች (ቪ አይ ፒ) ደህንነትና የሜዳ ጥራት በከፍተኛ ትኩረት የተከናወኑ ተግባራት መሆናቸውን አስታውሰዋል፡፡

በዚህም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጪው መስከረም ወር ከሴኔጋል ጋር የሚያደርገው የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ መርሐ ግብር በዚሁ ስታዲየም እንደሚካሄድ ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይም የፊፋ እና የካፍን ተጨማሪ መስፈርቶች ለማሟላት የሚከናወኑ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ነው ያሉት፡፡

ስታዲየሙ የካፍን ዝቅተኛ መመዘኛ በማሟላት ያገኘው ፍቃድ ለስፖርቱ እድገት እና ለአካባቢው የቱሪዝም እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡

14/08/2026

ኮሚኒቲ ሺልድ-አርሰናል ከማንቼስር ሲቲ

ከደቂቃዎች በኋላ በኤክስትራ ታይም ስፖርት ቀጥታ ስርጭት ይጠብቁን


#ፖድካስት #ፋናፖድካስት #ፋናሚዲያኮርፖሬሽን فانا_عربي_بودكاست

Photos from FMC Sport's post 13/08/2026

አቶ እያሱ ወሰን የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው ዳግም ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 07፣ 2018 ዓ.ም (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ባካሄደው 20ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አቶ እያሱ ወሰን ለቀጣይ አራት ዓመታት ፌዴሬሽኑን እንዲመሩ በድጋሚ መርጧል።

ፌዴሬሽኑ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን በሀገር ውስጥ ማካሄድና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉ የተገለጸ ሲሆን፤ የዳኞች አሰራርና የአሰልጣኝነት ፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓት እንዲስተካከል አቅጣጫ ተቀምጧል።

የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ እያሱ ወሰን አዲሱ አመራር በኦሊምፒክና በዓለም አቀፍ መድረኮች ውጤታማ የሚሆኑ አትሌቶችን ለማፍራትና ፌዴሬሽኑን በፋይናንስ ራሱን እንዲችል በቁርጠኝነት እንደሚሠራ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን 20ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ከፕሬዚዳንቱ በተጨማሪ ስድስት የሥራ አስፈፃሚ አባላትን በመምረጥ ተጠናቅቋል።

Photos from FMC Sport's post 12/08/2026

ፒኤስጂ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፒኤስጂ በአውሮፓ ሱፐር ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ አስቶንቪላን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆኗል።

የፒኤስጂን የማሸነፊያ ግቦች ኪቪቻ ክቫረትስኬሊያ እና ዴዝሪ ዱዌ አስቆጥረዋል።

አስቶንቪላን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ብቸኛ ግብ ብሪያን ማጆ ከመረብ አሳርፏል።

ፒኤስጂ በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ዋንጫን አሳክቷል።

Photos from FMC Sport's post 12/08/2026

የአውሮፓ ሱፐር ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ አሰላለፍ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ሱፐር ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ አሰላለፍ ይፋ ሆኗል፡፡

የአውሮፓ ሱፐር ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ አሸናፊው ፒኤስጂ እና በዩሮፓ ሊግ አሸናፊው አስቶንቪላ መካከል ይደረጋል፡፡

ጨዋታው ምሽት 4 ሰዓት ላይ በኦስትሪያ ሬድ ቡል አሬና መደረግ ይጀምራል፡፡

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address

Addis Ababa