09/06/2026
አርሰናል !
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በዚህ ክረምት ቡድኑን የበለጠ ለማጠናከር ከውሳኔ መድረሱ ተነግሯል።
የክለቡ የበላይ ሀላፊዎች በሚኬል አርቴታ እና ቤርታ ጥያቄ ቡድኑ ለረጅም ጊዜ አሸናፊ እንዲሆን ለማገዝ መዘጋጀታቸው ተሰምቷል።
ይህንንም ተከትሎ የጁቬንቱሱን ተጨዋች ኬናን ይልድዝ ለማስፈረም ጠይቀው ነበር።
ይሁን እንጂጨጁቬንቱስ ተጨዋቹ እንደማይሸጥ ያሳወቀ ሲሆን መድፈኞቹ ፊታቸውን ወደ ሌላ ተጨዋች አዙረዋል ተብሏል።
መድፈኞቹ አሁን ላይ ወጣት ተስፈኛ ተጨዋች ለማስፈረም ፍለጋቸውን ማጠናከራቸው ተገልጿል።
ክለቡ ጥሩ ተጨዋች መሆን የሚችል እና ለዋናው ቡድን የሚጫወት አልፍ ሲልም ተሸጦ ትርፍ ማምጣት የሚችል ተጨዋች ማግኘት ይፈልጋል።
አርሰናል አሁን ላይ የሌስተር ሲቲውን ተጨዋች ጄርሚ ሞንጋ ለማስፈረም በጥረት ላይ ይገኛል።
በሌላ በኩል የፒኤስጂውን ተከላካይ ኢማኑኤል ምቤምባ ለማስፈረም እያጤኑ መሆኑ ተገልጿል።
የ 18ዓመቱ ተከላካይ ኢማኑኤል ምቤምባ በዚህ ክረምት ከኮንትራት ነፃ እንደሚሆን ተዘግቧል።
መረጃው የዘ አትሌቲክ ነው።
https://t.me/+w8RCswOtQzs4ZmY8
https://www.facebook.com/wawlovtad
09/06/2026
“ እየተፈጠረ ያለው ነገር እያሳቀኝ ነው ” ኢያን ራይት
በተንታኝነት እያገለገለ የሚገኘው የቀድሞ ተጨዋች ኢያን ራይት ከዓለም ዋንጫው በፊት እየተፈጠሩ ያሉትን ነገሮች ተችቷል።
“ እውነት ለመናገር በጣም እየሳቅኩ ነው ነገርግን ምንም አዝናኝ አይደለም ” ሲል ኢያን ራይት ስሜቱን አጋርቷል።
“ የትኬት ዋጋው ከፍተኛ ነው የጉዞ ወጪውም አይቀመስም “ የሚለው ኢያን ራይስ “ ቪዛዎችም እየተከለከሉ ነው “ ብሏል።
አዘጋጅ ሀገር እንደዚህ አይነት ባህሪ አለው ወይ ሲል የጠየቀው ራይት “ ኳታር እንዴት እንደተተቸች አይተናል አሁን ምንም አልሰማሁም “ ሲል ገልጿል።
https://t.me/+w8RCswOtQzs4ZmY8
https://www.facebook.com/wawlovtad
09/06/2026
ኒኮ ጎንዛሌዝ፣ ሪኮ ሌዊስ፣ ቲጃኒ ሬይንደርስ፣ ኦማር ማርሙሽ፣ ማቲዮ ኮቫቺች፣ ጄምስ ትራፎርድ እና ናታን አኬ በዚህ ክረምት ማንቸስተር ሲቲን ሊለቁ ከሚችሉት ተጫዋቾች መካከል ናቸው።
- Sam lee
https://t.me/+w8RCswOtQzs4ZmY8
https://www.facebook.com/wawlovtad
08/06/2026
ፔፔ ከጆዜ ሞሪንሆ ጋር
የቀድሞ የሪያል ማድሪድ ተከላካይ ፔፔ የአሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆን አሰልጣኝ ቡድን አባል ሊቀላቀል ይችላል።
አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ እና ፔፔ አብረው በሚሰሩበት ሁኔታ ዙሪያ ንግግር ማድረጋቸውን ፋብሪዝዮ ሮማኖ ዘግቧል።
ፖርቹጋላዊው ፔፔ በአሁኑ ሰዓት ወደ ቀድሞ ክለቡ ለመመለስ እያሰበበት እንደሚገኝ ተነግሯል።
ፔሬዝ ምርጫውን ማሸነፋቸውን ተከትሎ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ የሪያል ማድሪድ አሰልጣኝነታቸው ተረጋግጧል።
https://t.me/+w8RCswOtQzs4ZmY8
https://www.facebook.com/wawlovtad
08/06/2026
በፕሪሚየር ሊጉ ምን አዲስ ነገር እናያለን ?
በሚቀጥለው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመት አዳዲስ የዳኝነት ህጎችን እንደምንመለከት ተገልጿል።
በቀጣይ የሚደረጉ የዳኝነት ውሳኔ ህጎች ሰዓት ለመቆጠብ በማሰብ መሆኑ ተነግሯል።
ምን አይነት ለውጥ ይኖራል ?
- ቡድኖች ኳስ መልሶ ለመጀመር የሚያዘገዩ ከሆነ ለተቃራኒ ቡድን የማዕዘን ምት ይሆናል።
- የእጅ ውርወራ የሚያዘገዩ ከሆነ ውርወራው ሌላኛው ቡድን ይሰጣል።
-ተቀያሪ ተጨዋች ሜዳውን በአስር ሰከንድ ውስጥ ለቆ የማይወጣ ከሆነ ተቀያሪው ተጨዋች አንድ ደቂቃ ለመቆየት ይገደዳል።
- በዚህም ምክንያት ቡድኑ ለአንድ ደቂቃ በአስር ተጨዋቾች ይጫወታል።
https://t.me/+w8RCswOtQzs4ZmY8
https://www.facebook.com/wawlovtad
08/06/2026
ቲምበር ከዓለም ዋንጫ ውጪ ሆነ !
የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን የመስመር ተጨዋች ጁሪየን ቲምበር ከአለም ዋንጫ ውጪ ሆኗል።
ተጨዋቹ በጉዳት ምክንያት ከውድድር ውጪ መሆኑን የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን አሳውቋል።
በምትኩ የሰንደርላንዱ ተጨዋች ጌርትሩይዳ ለኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ቀርቦለታል።
ኔዘርላንድ በአለም ዋንጫው ከጃፓን ፤ ስዊድን እና ቱኒዚያ ጋር ተደልድላለች።
https://t.me/+w8RCswOtQzs4ZmY8
https://www.facebook.com/wawlovtad
08/06/2026
በርናርዶ ሲልቫ ከባርሴሎና ጋር ስምምነት ላይ ደርሶ የነበረ ቢሆንም.. አሁን ግን ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ የመዛወር ዕድሉ ከፍተኛ ሆኗል።
አትሌቲኮ ማድሪድ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለተጫዋቹ ቀዳሚ ትኩረት ሰጥቶታል።
[Totcost]
https://t.me/+w8RCswOtQzs4ZmY8
https://www.facebook.com/wawlovtad
08/06/2026
🤯🇪🇸 አይታና ቦንማቲ በ28 ዓመቷ በዓለማችን ከፍተኛ ተከፋይዋ ሴት እግር ኳስ ተጫዋች ናት።
ነገር ግን በ41 ዓመቱ የሚገኘው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከእሷ በ260 እጥፍ የሚበልጥ ገቢ አለው። 💰
ይህንን በግልጽ ለመረዳት ያህል፣ የሮናልዶ የአንድ ወር ደመወዝ ከቦንማቲ የ21 ዓመታት ገቢ ጋር እኩል ነው።
https://t.me/+w8RCswOtQzs4ZmY8
https://www.facebook.com/wawlovtad
08/06/2026
🚨ሆዜ ማሪዮ ዶስ ሳንቶስ ሞሪኒዮ ፊሊክስ የሪያል ደ ማድሪድ አሰልጣኝ ሆነው ዛሬ ይሾማሉ።
በእለተ ረቡእም በስታዲዮ ሳንቲያጎ በርናቢው አቀባበል የሚደረግላቸውም ይሆናል።
https://t.me/+w8RCswOtQzs4ZmY8
https://www.facebook.com/wawlovtad
08/06/2026
"ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ አሸንፏል።"
FLORENTINO PEREZ.
2000 - 2030
ፔሬዝ ለሪክሌሜ
"ትንሽ ብትፎካከረኝ ጥሩ ነበር ብቻ ከኔ ጋር በዚህ በመብቃትህ ብቻ ኩራት ሊሰማህ ይገባል።"😁
https://t.me/+w8RCswOtQzs4ZmY8
https://www.facebook.com/wawlovtad