የፔሩ ህጻናት ስያሜ ሆኗል ሃላንድ 👶🇵🇪
በፔሩ ከተወለዱ ህጻናት አብዛኛዎቹ ሃላንድ የሚል ስያሜ እንዲወጣላቸው ተሰማ።
𝐇𝐚𝐚𝐥𝐚𝐧𝐝 𝐢𝐬 𝐞𝐯𝐞𝐫𝐲𝐰𝐡𝐞𝐫𝐞. 🔥
#𝐇𝐚𝐚𝐥𝐚𝐧𝐝 #ሃላንድ #ፔሩ #እግርኳስ #አለምዋንጫ
Buna Furniture
Sport Channel that focus on Football news specially premier league, laliga, bundesliga,Seri A amd French league A and...to Ethiopian target audiences
12/07/2026
አርጀንቲና ስዊዘርላንድን በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ተሸጋገረች
በ23ኛው የዓለም ዋንጫ አርጀንቲና ስዊዘርላንድን 3ለ1 በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ተሸጋግራለች።
በካንሳስ ሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አሌክሲስ ማካሊስተር ለአርጀንቲናን ፣ ዳን ንዶይ ደግሞ ለስዊዘርላንድ ግብ አስቆጥረው መደበኛው 90 ደቂቃ 1ለ1 ተጠናቋል።
ጨዋታው ወደ ጭማሪ 30 ደቂቃ ሲያመራ ሁሊያን አልቫሬዝ እና ላውታሮ ማርቲኔዝ አስቆጥረው ጨዋታው በአርጀንቲና 3ለ1 አሸናፊነት ተደምድሟል።
በጨዋታው አጥቂው ብሪል ኢምቦሎ 72ኛው ደቂቃ ላይ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ መውጣቱ ስዊዘርላንድን ዋጋ አስከፍሏል።
የ2022ቱ የኳታር ዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ አርጀንቲና በግማሽ ፍፃሜው ከእንግሊዝ ጋር ትጫወታለች።
#አርጀንቲና #ሜሲ
09/07/2026
አርሰናል ግብ ጠባቂ አስፈረመ
አርሰናል ከሊድስ ዩናይትድ በቅርቡ የለቀቀውን ግብ ጠባቂ፣ ኢላን መሊሬን በነፃ ዝውውር አስፈረመ።
በሊድስ ዩናይትድ ቤት ሰባት የውድድር ዘመናትን ያሳለፈው መሊሬ፣ 215 ጨዋታዎችን በማድረግ ክለቡ ወደ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ ትልቅ እገዛ አድርጓል።
ባለፈው የውድድር ዘመን ማጠናቀቂያ ላይ ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ክለቡን መልቀቁ ይታወሳል።
የእርሱ ወደ መድፈኞቹ ቤት መምጣት ከዳቪድ ራያ እና ኬፓ አሪዛባላጋ ጎን ለጎን የአርሰናልን የግብ ጠባቂ አማራጮች ይጨምራል።
በተጨማሪም ይህ ዝውውር ከወጣቱ እንግሊዛዊ ግብ ጠባቂ ቶሚ ሴትፎርድ ተጨማሪ የመጫወት ዕድል እንዲያገኝ፣ ለቀጣዩ የውድድር ዘመን በውሰት ውል ለቆ እንዲወጣ ያደርገዋል ተብሎ ይጠበቃል።
#አርሰናል #ዝውውር
08/07/2026
የጉማሬሽ አርሰናል ዝውውር
#አርሰናል 💞😘👑🙌
የትሮሳርድ ዝውውር
#አርሰናል #አርሰናል
ጉማሬሽ ወደ አርሰናል #አርሰናል #ዝውውር
25/06/2026
አርሰናል ፒዬሮ ሂንካፒዬን በቋሚነት አስፈረመ
አርሰናል ፒዬሮ ሂንካፒዬን ከባየር ሌቨርኩሰን በውሰት ካመጣበት ውል ላይ የነበረውን ቋሚ የማድረግ አማራጭ (option) ተግባራዊ አድርጓል።
ተከላካዩ ባለፈው ክረምት ከሌቨርኩሰን በውሰት አርሰናልን የተቀላቀለ ሲሆን፣ ክለቡ ከ22 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን እንዲያነሳ አግዟል።
ስካይ ስፖርትስ ኒውስ እንደተረዳው ከሆነ፣ ለሂንካፒዬ የተከፈለው የዝውውር ዋጋ 34.5 ሚሊዮን ፓውንድ ገደማ የ24 ዓመቱ ተከላካይ የ5 ዓመት ኮንትራት ፈርሟል።
ሂንካፒዬ ባለፈው የውድድር ዓመት በሁሉም ውድድሮች 39 ጨዋታዎችን ለአርሰናል ያደረገ ሲሆን፣ አርሰናል እና ፓሪስ ሴንት ዠርሜንን (PSG) በተጋጠሙበት የሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ላይም በቋሚነት ተሰልፎ ተጫውቷል።
#አርሰናል #የዝውውርዜና #ፒዬሮሂንካፒዬ #የእንግሊዝፕሪሚየርሊግ
የአልቫሬዝ ዝውውር #አልቫሬዝ #አርሰናል #ባርሴሎና #ማድሪድ
የሮጀርስ ዝውውር
#ሞርጋንሮጀርስ #አርሰናል #አርሰናል
Click here to claim your Sponsored Listing.