Sirak Sport Page

Sirak Sport Page

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Sirak Sport Page, Sports, Addis Ababa.

Sirak official sport page– የእግር ኳስና ሌሎች ስፖርቶች በቅርብ የሚከታተሉበት የትክክለኛ እና የፈጣን ዜና ምንጭ።
የቀኑን ጨዋታዎች ትንታኔዎች ውጤቶች እና አስደናቂ እይታዎችን በፍጥነት ያገኛሉ።
👉 ማሳሰቢያ :- ሁልጊዜም ተግቼ የምፅፈው ለእናንተ አዳዲስ መረጃ ለመስጠት ስለሆነ እናንተ ደግሞ like comment share በማድረግ ትተባበሩኝ ዘንድ በአክብሮት እጠይቃለሁ 👏👏

29/05/2026

‎🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿 𝗢𝗙𝗙𝗜𝗖𝗜𝗔𝗟: ባርሴሎና አንቶኒ ጎርደንን ከኒዉካስትል በ€80 ሚሊዮን ዩሮ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል።

20/05/2026

ሰበር

ታዋቂዉ ሬጌ አቀንቃኝ ሳሚ ዳን አርሰናል ሻምፒዮን መሆኑን ተከትሎ ዛሬ ምሸት 12 ሰዐት አርሰናልን የተመለከተ አዲስ ዘፈን እንደሚለቅ ይፋ አድርጓል።😯

20/05/2026

ማክስ ዶውማን የእንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግን ያነሳ በታሪክ በእድሜ ትንሹ ተጫዋች ሆኗል።16 አመት ከ140 ቀን ላይ ይገኛል።🌟🏆️

19/05/2026

ፔፕ ጋርዲዮላ፡- "በማንችስተር ሲቲ እና በቡድኔ ስም፣ ለዚህ ​​የፕሪሚየር ሊግ ድል አርሰናልን፣ ሚኬል [አርቴታን]፣ ሰራተኞቹን፣ የክፍል ውስጥ ሰራተኞች፣ ሁሉም ተጫዋቾች፣ ደጋፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ - ይገባቸዋል!" [SkySportsPL]

19/05/2026

አርሰናል የ 2025/2026 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ሆነ።

አርሰናል ከ22 አመት ጥበቃ በኋላ ሻምፒዮን ሆኗል።

ለመላዉ የአርሰናል ደጋፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ!

19/05/2026

ሰበር

ሳዉዝሀምፕተን ከፕሌይ ኦፍ ፍፃሜ ዉጪ ተደረገ

ሳዉዝሀምፕተን ከፍፃሜ ጨዋታ ዉጪ የተደረገበት ምክንያት የሚድልስብሮውን ልምምድ ሲሰልሉ በመገኝታቸዉ እንደሆነ ተረጋግጧል፤እንደ አወዳዳሪዉ አካል ገለፃ ከሆነ ቡድኑ የሌሎች ክለቦች ልምምድ ማዕከል ሰላይ በመላክ ልምምዳቸዉን ያሰልል እንደነበር ታዉቋል።

ቡድኑ በቀጣይ አመትም 4 ነጥብ ተቀንሶበት ዉድድሩን የሚጀምር ይሆናል፤ሳዉዝሀምፕተን በዚህ የዉድድር ዘመን 80 ነጥቦችን የሰበሰበ ሲሆን ለፕሌይ ኦፍ ፍፃሜም ደርሶ ነበር፤በፍፃሜዉ ጨዋታ ሳዉዝሀምፕተንን በመተካት ሀል ሲቲ እንደሚጫወት ታዉቋል።

19/05/2026

የአርሰናል ደጋፊዎች የማንቸስተር ሲቲ ብራንድ ያላቸው የውሃ ጠርሙሶችን ይዘው ወደ ቦርንማውዝ ስታዲየም ደርሰዋል።

19/05/2026

የ2027ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ድልድል ይፋ ሆነ

‎አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የ2027ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ድልድል በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ በማጣሪያው በምድብ 10 ከሴኔጋል፣ ሱዳን እና ሞዛምቢክ ጋር ተደልድላለች፡፡

ከየምድቡ 1ኛ እና 2ኛ ሆነው የሚያጠናቅቁ ቡድኖች ሦስቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ኬንያ፣ ታንዛኒያ እና ኡጋንዳ በጋራ ለሚያዘጋጁት የ2027ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ማለፋቸውን ያረጋግጣሉ፡፡

በምድብ ማጣሪያው የውድድሩን አዘጋጅ ሀገራት ጨምሮ 48 ሀገራት የሚሳተፉ ሲሆን፥ የምድብ ማጣሪያዎቹ በቀጣዩ ዓመት መስከረም ወር መካሄድ ይጀምራሉ፡፡

12/05/2026

አልናስር ዛሬ በስታዲየም ውስጥ ለሚገኙ ደጋፊዎቹ በሙሉ በነፃ ማልያዎችን እንደሚሰጥ አስታውቃል።

10/05/2026

ኮሞ በክለቡ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ መድረክ መሳተፉን አረጋግጧል።

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Address

Addis Ababa