11/06/2026
ወገን ዛሬ የወጣውን ማስታወቂያ ደግሞ ተመልከቱ የመንገድ ሥራው ይቀጥላል ተብሏል
በወላይታ ሶዶ ከተማ አስፓልት ለመሥራት የተረከበው የChina First Highway Engineering ኮንስትራክሽን ድርጀት ዛሬ ሌላ አዲስ ማስታወቂያ መለጠፉ ተሰምቷል። በትላንትናው ዕለት ሥራው ይቆማል የተባለው በነበረበት እንደሚቀጥል በማስታወቂያ አስታውቋል።
ቆይ ምን እተሰራብን ነው? አሁንም ለማዘናጋት ይሁን? 🤔
ለማንኛውም እያንዳንዱን እርምጃ መከታተል አስፈላጊ ነው🤝
11/06/2026
............... .... 👇👇..... ................
ዳስና ድንኳን ጥለን ማልቀስ ወይም ታጥቀን መታገል❗️❗️
ኮርደር በይፋ ተቋርጧል፣ ህዝብ ተክዷል❕❕
👉እንደ ማሽላ ማሳ በሰባቱም በሮች አረሱና ገደል ካደረጉ በኋላ ቤታቸው ገብተው ተኝተዋል፣ አንቀላፍቷል። ለልብስ፣ ለግብዣ፣ ለማስተናግድና ለአበል በሚሊዮን ብሮች ያወጡ፣ በህዝብ ቆዳ የተጣበቁ መዥገሮች ለልማት ስሆን ግን መክፈል አቃተን በለዋል። በሁሉም አቅጣጫ በተቆፈረው ጉድጓድ እንግዲ የዘንባባ ዛፍ ይተከል ወይስ እነርሱ ይቀበሩ? መልሱ ለህዝብ ነው።
✍️እንግዲ ከፊት ሁለት አማራጮች አሉን። እጆችን አጣጥፈን መቀመጥ ወይም ለመታገል እንደጦና ንቦች መቆጣት፣ መነሳት፣ ሰይፍና ጎራደ መታጠቅ❗️❗️
🗡ሰይፍና ጎራድያችን ደግሞ የሀሳብ ነው፤ ሰላማዊ የመጠየቅ ሰይፍ ነው። ሰይፋችን በሁለት በኩል ስል መሆን አለበት። አንዱ ጎን ወደ ውስጥ የሚቆርጥ፣ ሌላኛው ደግሞ ወደውጭ የሚቆርጥ መሆን አለበት።
🔨🗡ከውስጥ በህዝብ ጫንቃ ቁጭ ያሉ ቀንበሮችን በስል መጥረቢያ መቆራረጥ፣ መሰባበር ነው መፍትሄው። ከውጭ ደግሞ ቀንበሩን በመጠቀም የሚያርሱን እጃውን መቁረጥ አለብን። የጋራ ትግል ያስፈልጋል❕❕
👉ለሁሉም ግን ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ አለበት፣ መቁረጫችንና መጥረቢያችን በሚገባ የተቀጠቀጠ፣ የተሳለ፣ ያልዛገ መሆን አበት። ቆራጭ ክንዶችም የፈረጠሙ መሆን አለባቸው። መፈርጠም ብቻ ሳይሆን ብልሃትም የተካኑ ልሆን ይገባል። መቼና እንደት መቁረጥ እንዳብን ማወቅ ደግሞ ወሳኝ ጉዳይ ነው። መቁረጥ ያለብን ስስ ቦታ መለየት ግዴታ ነው። በትክክለኛው ቦታ፣ በትክክለኛው ሰዓት በፈርጣማው ክንድ፣ በተሳለ መጥረቢያ በፍጥነት ቆርጠን መጣል አለብን።
🕚ጊዜው አሁን ነው። ማንና እንደት መቁረጥ አለብን ሌላ ጥያቄ ነው። ዜደውን የህዝብ ልጆች በውስጥ መናበብ አለባቸው❕❕
👉በሶዶ ከተማ ውስጥ በህዝብ ላይ የተቀመጡ ቀንበሮች የሶዶ ከተማ ፊት አመራሮች ናቸው። አንዷ የዋና ሰው ቀኝ እጅ ናት። የመንግሥት ዋና ተጠሪው ደግሞ፣ የፓርቲው ሰው የቅርብ ዘመድ ነው። ሁለቱም፣ በተለያየ መንገድ ለሁለቱ አለቆቻቸው እየተገዙ፣ ከተማዋን ይዞ ወደ ሞት ጥላ እየተጓዙ ነው። ሩጫቸው በአጭሩ ካልተቀጨ፣ የከተማው ልማት ቀብር የሚፈጸምበት ቀን ቅርብ ነው። ህዝቡ መንቃት አለበት። ይሄ ቀይ መስመራችን ነው❗️❗️
✍️የህዝብ የልማት ጥያቄዎችን መመለስ ያልቻሉ የሶዶ ከተማ አመራሮች ግን በመሬት ዝርፊያ ላይ ተሰማርተዋል። ከንቲባዋ ደግሞ እድሜዋን ለማራዘም የህዝብ የልማት ጥያቄ በአግባቡ ለመመለስ እየታገለች አይደለችም። በየአስራ አምስት ቀኑ ለሰውየው ፍየል እየገበረች፣ የስልጣን ዘመኗን እያራዘመች ነው።
🤝ትላንትና የደገፍናት፣ በደስታ የተቀበልናት አሁን ለህዝብ ጥያቄ መልስ መስጠቱን ያቆመች ይመስላል። ጥሩ መስራት በጀመረች ጊዜ ያደነቅናት እንዲትበረታ እንጂ እንዲትደክም አይደለም። እርሷ ግን የስህተት መንገድ የመረጠች ይመስላል። ጫናዎች ካሉ፣ ለህዝብ ውግንና በማሳየት ከስልጣን መነሳትንም ጭምር ዋጋ መክፈል አለባት።
💪ህዝብ ሆይ ተነስ፣ ወጣት ሆይ ታጠቅ። የሀሳብ ሰይፊህን ያዝ፣ የህዝብ ጠላቶችን ቆራርጥ❕❕
👉ንዋይ ሳሙኤል ያያ ከገሱባ💪💪
10/06/2026
🚨 ማይክል አርቴታ የአርሰናልን ባለስልጣናት ቪኒሲየስ ጁኒየርን ለማስፈረም እንዲሞክሩ ጠይቋል ።
[TheTouchline]
10/06/2026
🚨ሰበር:Breaking !!!
አርጀንቲናዊው የአትሌቲኮ ማድሪድ አጥቂ ጁሊያን አልቫሬዝ ከክለቡ የሚለቅበት ብቸኛው አማራጭ በአርሰናል በኩል ብቻ እንደሆነ ተሰምቷል።
መድፈኞቹ ተጫዋቹን የመግዛት ከፍተኛ ፍላጎት እና የገንዘብ አቅም ያላቸው ቢሆንም ዝውውሩ ግን ቀላል አይሆንም። ባርሴሎና ያቀረበውን የ 100 ሚሊዮን ዩሮ ሂሳብ ለማሻሻል ፍላጎት የሌለው ሲሆን፥ ሪያል ማድሪድ ደግሞ ፊቱን ወደ ሌላ አማራጭ አዙሯል። 🇦🇷🇪🇸👀
[Via - JFelixDiaz] 📑🔴⚪
10/06/2026
በዎላይታ ሶዶ ከተማ ውስጥ ከኮቴ - ግብርና ኮሌጅ፣ ከጦና አደባባይ - አረካ አቅጣጫ እየተገነባ የነበረው የአስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ከባለፈው ረቡዕ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ መቆሙን ለማወቅ ተችሏል።
የግንባታው መቆም ምክንያት ደግሞ ሌላ ሳይሆን የገንዘብ ክፍያ (Payment) እጥረት ነው። መንግሥት ግንባታውን ለሚያከናውነው የቻይና ድርጅት ወደ 1.6 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ውዝፍ ክፍያ ባለመፈጸሙ ምክንያት ድርጅቱ ሥራውን ለማቆም ተገድዷል።
ነገሩን ይበልጥ አሳሳቢና አሳዛኝ የሚያደርገው ግን ከግንባታው መቆም በኃላ በኃላፊዎቹ በኩል እየተሄደበት ያለው የሕዝብ ማዘናጊያ መንገድ ነው።
ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ መቆሙ ይፋ እንዳይሆንና የሕዝብ ተቃውሞ እንዳይነሳ ለመሸፈን በአንድ መለስተኛ ማሽን እና በአነስተኛ ገልባጭ መኪና (Dump-truck) ብቻ "ሥራው እንደቀጠለ" አስመስሎ በማሳየት ሕዝቡን የማዘናጋትና የውሸት ተስፋ የመስጠት እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል።
ለምርጫ ተብሎ የሚቀመጥ መሠረተ ድንጋይ ሆነ የፎቶ ጋጋታም ጠፋ አይደል?
08/06/2026
🚨በአርሰናል እና በሮጀርስ ወኪሎች መካከል የመጀመሪያ ደረጃ ውይይቶች ተደርገዋል።
ከ80 እስከ 100 ሚሊዮን ፓውንድ የሚደርስ ከፍተኛ የዝውውር ጥያቄ ከቀረበ፣ አስቶን ቪላዎች ካለባቸው የፋይናንስ ገደብ አንጻር ተጫዋቹን ለመሸጥ ሊገደዱ ይችላሉ።
06/06/2026
▪️ጁሊያን አልቫሬዝ ወደ ባርሳ የሚያደርገው ዝውውር ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል!
[Pedro Fullan]🥈
06/06/2026
👐 🤩 ራፋኤል ሌኦ በፕሪሚየር ሊግ ቡድኖች ላይ፡ “ማን ዩናይትድ እወዳለሁ፣ ምክንያቱም idol ክርስቲያኖ ሮናልዶ ነው… ..አርሴናልንም እወዳለሁ። 💣 አስታውሱ ራፋኤል ሌኦ በዚህ ክረምት ኤሲ ሚላንን 𝐋𝐄𝐀𝐕𝐄 ለማድረግ መወሰኑን በዚህ ሳምንት አስታውቋል…
05/06/2026
በአመቱ ድንቅ ብቃት ያሳየውን ማንን ትመርጣላችሁ?
ሶስት የአርሰናል ተጫዋቾች የተካተቱበት የፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጨዋቾች ማህበር የመጨረሻ እጩዎች ይፋ ሆኑ
የፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጨዋቾች ማህበር ( PFA ) የውድድር ዓመቱን ምርጥ ተጨዋች ለመምረጥ የመጨረሻ ስድስት ተጫዋቾች ይፋ ተደርገዋል።
ሶስት የአርሰናል ተጫዋቾች በተካተቱበት ምርጫ ጋብሬል ማጋሌሽ፣ ዴቪድ ራያ እና ዴክላን ራይስ ከአርሰናል እጩዎች ሆነው ቀርበዋል፡፡
የማንቸስተር ሲቲዎቹ ኤርሊንግ ሀላንድ እና ራያን ቼርኪ ሌሎች እጩዎች ሲሆኑ የፕሪሚየር ሊጉ ምርጥተጫዋችነት ሽልማትን ያሸነፈው ብሩኖ ፈርናንዴዝ ሌላኛው እጩ ሆኗል፡፡
05/06/2026
🚨🔴 ሊቨርፑል ማንቸስተር ዩናይትድን በማቲየስ ፈርናንዴዝ እንደሚፎካከር ከፖርቹጋል የሚወጡ ዘገባዎች አመልክተዋል። 💸 ዌስትሃም £80 million ይፈልጋሉ