22/08/2026
ሻምፒዮኖቹ በሁለተኛ አጋማሽ ፍፁም የጨዋታ ብልጫን በመውሰድ አዲሱን የውድድር ዓመት በድል ጀምረዋል።
ቻልሀኖሉ፣ ኢስፖሲቶ እና ቢሳክ እጅግ ማራኪ የሆኑ ጎሎችን አስቆጥረዋል! 💥
FT: ኢንተር 4-1 ሞንሳ (ቻልሀኖሉ፣ ዜልንስኪ፣ ኢስፖሲቶ፣ ቢሳክ/ ቫሬላ)
The best Serie A page around in Amharic & English ..... just don't waste ur time to check different
22/08/2026
ሻምፒዮኖቹ በሁለተኛ አጋማሽ ፍፁም የጨዋታ ብልጫን በመውሰድ አዲሱን የውድድር ዓመት በድል ጀምረዋል።
ቻልሀኖሉ፣ ኢስፖሲቶ እና ቢሳክ እጅግ ማራኪ የሆኑ ጎሎችን አስቆጥረዋል! 💥
FT: ኢንተር 4-1 ሞንሳ (ቻልሀኖሉ፣ ዜልንስኪ፣ ኢስፖሲቶ፣ ቢሳክ/ ቫሬላ)
22/08/2026
የጣልያን ሴሪ ኤ ዛሬ በሚደረጉ 4 ጨዋታዎች ይጀመራል
************
የ2026/27 የጣልያን ሴሪ ኤ ዛሬ ሲጀመር የአምናው የሴሪ ኤ ሻምፒዮን ኢንተር በሜዳው አዲስ አዳጊውን ሞንሳን ያስተናግዳል፡፡
ሌላኛው የሴሪ ኤ ጠንካራ ቡድና ናፖሊ በአዲሱ አሰልጣኙ ማክስ አሌግሪ እየታገዘ ወደ ስታዲዮ ሉዊጂ ፌራሪስ በመጓዝ ጄኖዋን የሚገጥም ይሆናል፡፡
ምሽት 1 ሰአት ከ30 ላይ የአምናው ክስተት ቡድን ኮሞ ከሜዳው ውጪ ኡዲኒዜን ይገጥማል።
ፓርማ ከካግሊያሪ ሌላኛው የምሽቱ የመክፈቻ ጨዋታ ይሆናል።
22/08/2026
Good Morning!
31/07/2026
Rest in peace KING BARESI! 💔
LEGEND OF THE GAME. The greatest defender of all time 🐐.
The one and only teacher of Maldini 🐐
🥹😭
SERIE A Ethiopia Italy in Ethiopia Lega Serie A AC Milan
25/05/2026
🚨🇮🇹 የተረጋገጠ | ኤሲ ሚላን እና ጁቬንቱስ የዩሮፓ ሊግ የተሳትፎ ቦታቸውን ሲያረጋግጡ፤ አታላንታ ደግሞ የአውሮፓ ኮንፍረንስ ሊግ ቦታውን አረጋግጧል! 🏆✨
🔴⚫ ኤሲ ሚላን በእጁ ገቡቶ የነበረውን የሻምፒዮንስ ሊግ ቦታ ባልተጠበቀ መልኩ በሜዳው በካግሊያሪ ተሸንፎ ከሻምፒዮንስ ሊግ ወቶ ወደ ዩሮፓ ሊግ ገብቷል።
⚪⚫ የመጨረሻ ሁለት ጨዋታዎቹ ላይ ነጥብ የጣለው ጁቬንቱስም በእጁ ገብቶ የነበረውን የሻምፒዮንስ ሊግ ቦታን ለኮሞ አሳልፎ በመስጠት ወደ ዩሮፓ ሊግ ገብቷል።
🔵⚫ የካቻምናው የዩሮፓ ሊግ አሸናፊ አታላንታ ደግሞ የአውሮፓ ኮንፍረንስ ሊግ የተሳትፎ ቦታውን በማግኘት አውሮፓዊ ጉዞውን ቀጥላል።
🇮🇹
25/05/2026
🚨🇮🇹 የተረጋገጠ | ሮማ እና ኮሞ የሻምፒዮንስ ሊግ የተሳትፎ ቦታን አረጋግጠዋል! 🏆✨
🐺 የጋስፔሪኒ ሮማ በሴሪ ኤ ጠንካራ እና ተፎካካሪ ቡድን በማሳየት በተለይ ከሁለተኛው ዙር በኋል አስደናቂ ጉዞን በማድረግ ከአውሮፓ ትልቁ የውድድር መድረክ ቦታዋን አረጋግጠዋል።
🌊 ሌላኛ የዘንድሮ የሴሪ ኤ ክስተት ቡድን ኮሞ በመጨረሻ ጨዋታ የኤሲ ሚላንን መሸነፍ ተከትሎ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሻምፒዮንስ ሊግ መድረክ ማለፍ ችሏል።
🔥 ኮሞ አዲስ ቡድን፣ አዲስ ታሪክ፣ ትልቅ ህልም!
🇮🇹
25/05/2026
🚨🇮🇹 የተረጋገጠ! U.S. Cremonese ወደ ሴሪ ቢ ወርዷል! ✅
ትላንት ፍፃሜውን ባገኘው ሴሪ ኤ በሜዳው በኮሞ የ4ለ1 ሽንፈትን አስተናግዶ ሶስተኛው ወደ ሴሪ ቢ የወረደ ቡድን ሆኗል። 🔙
24/05/2026
ዛሬ በሚደረጉ የ38ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታዎች ሴሪ ኤ ፍፃሜውን ያገኛል። የውጤት ግምታችሁን በኮሜንት አካፍሉን
🕧 10:00 ሰዓት
ፓርማ 🆚 ሳሱውሎ
🕒 1:00 ምሽት
ናፖሊ 🆚 ኡዲኒዜ
🕒 3:45 ምሽት
ኤሲ ሚላን 🆚 ካግሊያሪ
🕒 3:45 ምሽት
ክሬሞኔሴ 🆚 ኮሞ
🕒 3:45 ምሽት
ሄላስ ቬሮና 🆚 ሮማ
🕒 3:45 ምሽት
ቶሪኖ 🆚 ጁቬንቱስ
🕒 3:45 ምሽት
ሊቼ 🆚 ጄኖዋ