Hussein Zinaab

Hussein Zinaab

Share

Yes we can!!!!! +~+ ~~~~~~~+++++++

Photos from Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ's post 12/08/2026
09/08/2026

የነገዋ
የትላንትን አስከፊ አሳዛኝና አስፈሪ እንዲሁም የነገን ተስፋ ቢስነት ህይወት የቀየረ የእህቶቻችንን አሰቃቂ ኑሮ በብርሀን ተስፋ የቀየረላቸው የስንቶቹን የፀሀይ፣ውርጭ እና ዝናብ ተፈራርቆ ያከሰማቸውን ህይወት ለውጦ አይዞሽ ትችያለሽ ብሎ አሰልጥኖ አስመርቆ ስራ አስይዞ ከጉዳና ህይወት አሰናብቶ ባለሙያ ያደረጋቸው የችግሩ ሰለባ የሆኑ ሴቶቻችንን ገበና ያፀዳ እጅግ ቤተሰባዊ ሀገራዊ ፕሮጀክት። በርካታ የአፍሪካ ሀገራት በጎበኙበት ወቅት የተደመሙበትና የቀኑበት ሀገራዊ አለኝታነቱን ያሳየ ተግባር። የክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ እሳቤና ተግባር በመሆኑ ትውልድ ያመሰግኖታል።

09/08/2026
Photos from Hussein Zinaab's post 08/08/2026

በዚህ ዘመን የትጥቅ ትግል ማድረግ ፋሽን ያለፈበት ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ በትጥቅ ትግል በኃይል ሥልጣን ለመያዝ ወይም ፍላጎትን ለመጫን የሚደረግ ሙከራ እንደማይሳካ ገልጸው፤ በዚህ ዘመን የትጥቅ ትግል ማድረግ ፋሽን ያለፈበት ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት ከኦነግ ሸኔ እና ከሌሎች የታጠቁ ቡድኖች በርካታ ታጣቂዎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ሰላማዊ መንገድ መመለሳቸውን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በጫካ የቀሩትም ቢሆኑ በሂደት ነገሩ እየገባቸው ይመጣሉ የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

መንግሥት በርካታ የፖለቲካ እስረኞችን ፈትቶ የዴሞክራሲ ምህዳሩን ያሰፋ ቢሆንም፣ የተወሰኑ አካላት ግን ትናንት ካሰሯቸው እና ከገረፏቸው አካላት ጋር ድብቅ ጥምረት ፈጥረው ወደ ጫካ መግባታቸው አሳዝኖናል ብለዋል።

በኦሮሚያ ክልል ሰፊ የዴሞክራሲና የፖለቲካ ተሳትፎ ዕድል በመኖሩ በሰላማዊ መንገድ መታገል ይቻላል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ በጫካ የሚገኘው የሸኔ ቡድን ግልጽ ዓላማ እና ግብ የሌለው "ተቀጣሪ ኃይል" ነው ሲሉ ገልጸውታል።

ቡድኑ ሽፍታ ሆኖ ሰዎችን ከመግደልና ከመዝረፍ ውጭ የፖለቲካ ፍላጎቱን ማሳካት እንደማይችልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የኦነግ መስራች ታጋዮች በአሁኑ ወቅት በሰላማዊ መንገድ በሀገር ውስጥ እና በፓርላማ ተቀምጠው እየታገሉ ባሉበት ሁኔታ፣ በጫካ ያለው ቡድን የማንን አጀንዳ ይዞ እንደሚታገል ሕዝቡ ሊጠይቅ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ማንኛውም አካል ፍላጎቱንና ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ እና በምክክር ማሳካት እንደሚችል ያመላከቱት ጠቅላይ ሚነስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ አሁንም ቢሆን የመንግሥት የሰላም በር ክፍት እንደሆነ አረጋግጠዋል።

08/08/2026

ትናንት አንዱን ከሌላው ጥቃት እንዲታደጋቸው መንግሥትን ሲወተውቱ የነበሩ ኃይሎች ዛሬ ጥምረት መፍጠራቸው እየተዳከሙ መምጣታቸውን ያሳያል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (ኦቢኤን) ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ በሀገራችን ብሎም በኦሮሚያ ክልል ለሚታየው የጸጥታ ችግር መሠረታዊ ምክንያቶችን በዝርዝር አብራርተዋል።

ለችግሮቹ ዋና ዋና ምክንያቶች ያሏቸውም የፖለቲካ ሽግግሩ ተፈጥሯዊ ፀባይ፣ የሥልጣን ማዕከል ሽግግር እና የትጥቅ ኃይሎች መዳከምን ተከትሎ የተፈጠረ ያልተጠበቀ ጥምረት መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

የሥልጣን ማዕከል ሽግግሩን እና የፖለቲካውን ተፈጥሯዊ ፀባይ በተመለከተ ሲያብራሩ ቀድሞ ኢትዮጵያን በብቸኝነት ሲመራ የነበረው ቡድን ሥርዓቱ ሁሉንም አሳታፊ ወደሆነ መንገድ መግባቱን ባለመቀበል ሥልጣን በጉልበት ለመመለስ እያደረገ ያለው ጥረት ለግጭቶች መንስኤ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ የብዙ እምነቶች፣ ቋንቋዎች እና ባህሎች ባለቤት በመሆኗ በአንድ ብሔር ወይም ቡድን የበላይነት ብቻ ልትመራ እንደማትችልም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም የትጥቅ ኃይሎች መዳከምን ተከትሎ ስለተፈጠረው ያልተጠበቀ ጥምረት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች መንግሥትን ማሸነፍ እንደማይችሉ ሲገነዘቡ ያልተቀደሰ ጋብቻ መፍጠራቸውን ጠቁመዋል፡፡

ትናንት አንዱን ከሌላው ጥቃት እንዲታደጓቸው መንግሥትን ሲወተውቱ የነበሩ ኃይሎች፣ ዛሬ ተጣምረው መሰለፋቸው ምን ያህል እንደተዳከሙ እና ተስፋ እንደቆረጡ የሚያሳይ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ከዚህም አልፎ እነዚህ ኃይሎች እንደ ኤርትራ እና ሱዳን ያሉ የውጭ አካላትን ለእርዳታ እየጋበዙ መሆኑን ሕዝቡ ሊገነዘበው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ይህንን የተዛባ ትርክት በማረም እንዲሁም አፍራሽ ከሆነ አስተሳሰብ በመውጣት፣ ሁሉንም የሚያስታርቅ እና የተሻለ ሀሳብ የሚያመጣ ውህድ መንገድ መከተል አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል፡፡

07/08/2026

“የኦሮሞ ሕዝብ ኢትዮጵያን ያስተሣሠረ ጠንካራ ገመድ ነው” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦቢኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ የኦሮሞ ሕዝብ ከኢትዮጵያ ሀገር ግንባታ ጋር ያለውን ጥልቅ ቁርኝት በታሪካዊ ማሳያዎች እየጠቀሱ በስፋት አብራርተዋል።

“የኦሮሞ ሕዝብ ኢትዮጵያን ያስተሣሠረ ጠንካራ ገመድ ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ከጥንት ጀምሮ በኢትዮጵያ ሕዝብ ትሥሥር ውስጥ ያለውን አስተዋፅኦ በማሳያዎች ዘርዝረዋል።

በ1512 ዓ.ም የባሕረ ነጋሽ ንጉሥ የነበረው 'ዶሪ' ኦሮሞ እንደነበር፣ በተጨማሪም 'ባሬንቱ' የተሰኘው ትልቅ ከተማ እና እንደ አምባ ሶይራና አምባ ደብራ ያሉ ተራራዎች ስያሜያቸው የኦሮሞ ሥረ-መሠረት እንዳለው አስረድተዋል።

የዛግዌ ሥርወ-መንግሥት እና የገዳ ሥርዓት ትሥሥር፡ የዛግዌ ሥርዓት የመጀመሪያው ንጉሥ 'መረሪ' የተባለ የኦሮሞ ስም ያለው መሆኑን፣ እንዲሁም ነገሥታቱ (እንደ ይምርሃና እና ላሊበላ ያሉት) ለ40 ዓመታት መግዛታቸው በገዳ ሥርዓት (8x5=40) ሥልጣን ከሚረከብበት ዕድሜ ጋር ያለውን አስገራሚ መመሳሰል ጠቁመዋል። አሁንም ድረስ በላሊበላ ዙሪያ አፋን ኦሮሞ የሚናገሩ ማኅበረሰቦች መኖራቸውንም አክለዋል።

የሥነ-ሕንፃ እና የቅርሶች መመሳሰል፦ በአክሱም እና በምሥራቁ የሀገራችን ክፍል ያለው የባህል መገለጫ (የአለባበስ) መመሳሰል፣ እንዲሁም በባሌ የሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ካሉ ዋሻዎች ጋር ያለው መመሳሰል፣ እንዲሁም በላሊበላ የሚገኘው ውቅር ቤተ-ክርስቲያን (ቤተ ጊዮርጊስ) በሸዋ ከሚገኘው አዳዲ ማርያም ጋር ከአንድ ድንጋይ ተፈልፍለው በመውጣት በአሠራርም ሆነ በዘመን ያላቸውን ጥልቅ ተመሳሳይነት አንሥተዋል።

የዘመኑ ማኅበረሰቦች ዘመናዊ መጓጓዣ ባልነበረበት ወቅት የነበራቸውን ጥልቅ የታሪክ እና የምሕንድስና ትሥሥርን እንደሚያሳይ አብራርተዋል።

ማኅበራዊ መስተጋብር በጎጃም፦ በጎጃም አካባቢ "ቄሮ ገብርኤል" የሚባል የኦሮሞ ስያሜ ያለው መንደር መኖሩ በ16ኛው ክፍለ ዘመን እና ከዚያም በፊት በሕዝቦች መካከል የነበረውን ሰፊ መስተጋብር ያሳያል።

የዘመናዊው ትግል አቃፊነት፦ የመጫ እና ቱለማ ማኅበር ሲመሠረት ትግሉ የኦሮሞን ሕዝብ መብት ከማስከበር ባለፈ የሌሎችንም ብሔር ብሔረሰቦች (እንደ ሲዳማ፣ ወላይታ፣ አፋር፣ ሶማሌ ወዘተ) ጥያቄ ያቀፈ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

በተለይም የሶሻሊዝም ርዕዮተ ዓለም መምጣቱን ተከትሎ ትግሉ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ መልክ በመያዝ አቃፊነቱን አስመስክሯል ነው ያሉት።

Photos from Hussein Zinaab's post 07/08/2026

የኦሮሞ ሕዝብ በታሪኩ የተቃወመው የተበላሸ የአስተዳደር ሥርዓትን እንጂ ኢትዮጵያን አይደለም - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የኦሮሞ ሕዝብ ነፃነት እና እኩልነት ታሪክ ከኢትዮጵያ ሀገር ግንባታ ጋር ያለውን ጥልቅ ቁርኝት በታሪካዊ ማሳያዎች እየጠቀሱ በስፋት አብራርተዋል።

የኦሮሞ ሕዝብ በታሪኩ የተቃወመው የተበላሸ የአስተዳደር ሥርዓትን እንጂ ሀገርን (ኢትዮጵያን) አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሀገርን በመገንባት ሂደትም ደሙን፣ አጥንቱን እና ላቡን ማፍሰሱን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ኦሮሞ ሕዝብ የረጅም ዘመን ትግል መነሻ ምክንያቶች እንዲሁም ትግሉ ግቡን ለመምታት ስለዘገየበት እና ስላጋጠሙት ተግዳሮቶች ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም የኦሮሞ ሕዝብ የትግል ጥያቄዎች በዋናነት በሦስት መሠረታዊ ክፍሎች የሚከፈሉ መሆኑን እና እነዚህም የኢኮኖሚ፣ የማንነት እና የዴሞክራሲ ጥያቄ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የኢኮኖሚ ጥያቄን በተመለከተ፦ ሕዝቡ የመሬት እና የሀብት ባለቤት የመሆን፣ በላቡ ሠርቶ የማደግ እና አካባቢውን የመቀየር ፍላጎት እንደነበረው ጠቁመዋል። መሬት ለኦሮሞ ሕይወቱ ቢሆንም፣ ይህ ሀብቱ ሲነጠቅ እና ሲበዘበዝ መቆየቱ እንዲሁም አራሹ አርሶ አምርቶ የመጠቀም መብት ማጣቱ ዋነኛ የትግል መነሻ ሆኗል ነው ያሉት።

የማንነት ጥያቄን በተመለከተ ደግሞ ይህ ጥያቄ አፋን ኦሮሞን ከመናገር ባለፈ ባህልን፣ ማንነትን፣ ሥነ-ምግባርን (ሰፉ)፣ ታላላቆችን፣ ፍጥረታትን እና ፈጣሪን ማክበርን በውስጡ ያካተተ ጥልቅ ጥያቄ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

በኦሮሞነት ማንነት አድጎ ቋንቋን መናገር ብቻውን የማንነት ጥያቄን ሙሉ በሙሉ ይመልሳል ማለት አይቻልም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ስለዚህ የቋንቋ፣ የባህል እና የማንነት ጥያቄዎች አሁንም እንዳሉ ጠቁመዋል።

ከዴሞክራሲ ጥያቄ አንጻር ደግሞ የኦሮሞ ሕዝብ የራሱ የሆነ አሳታፊ የገዳ ሥርዓት የነበረው ሕዝብ በመሆኑ፣ ራሱን በራሱ የማስተዳደር፣ የራሱን ሕግ የማውጣት እና በሕጉ የመተዳደር የረጅም ጊዜ ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ እንደነበረው ጠቁመዋል።

የመንግሥት አስተዳደር ደግሞ ሕዝቡ ከለመደው ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር አንፃር ተቃራኒ ሲሆንም ጥያቄዎችን ሲያነሣ እንደነበር ነው የገለጹት።

ይህ የኦሮሞ ሕዝብ ትግል ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ ቢቆይም፣ በሚፈለገው ፍጥነት ድል ሳያመጣ የዘገየባቸውን ምክንያቶች ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአራት ዋና ዋና ነጥቦች አስቀምጠዋል።

አንደኛው የስትራቴጂያዊ ሐሳብ እጥረት ነው፦ ምርት ለማግኘት ትራክተር ቢኖርም 'ምርጥ ዘር' ከሌለ ዋጋ እንደሌለው ሁሉ፣ የትግል ግብን ለማሳካት የሚያስችል ጥራት ያለው ስትራቴጂያዊ ሐሳብ አለመኖር ትልቁ ክፍተት ነበር ሲሉ በምሳሌ አስረድተዋል።

ሁለተኛው የአንድነት እጥረት ነው፡- ኦሮሞ በሰፊ መሬት ላይ የሚኖር እና የጋራ ማንነት ያለው ቢሆንም፣ በፖለቲካ ሴራዎች፣ በእምነት፣ በወንዝ እና በዞን በመከፋፈል ጠንካራ ውስጣዊ አንድነትን ማስቀጠል አለመቻሉን ጠቅሰዋል።

ሦስተኛ የግንኙነት አያያዝ ችግር፦ ከሌሎች ኃይሎች ጋር የሚደረጉ ግንኙነቶች በጊዜያዊ ፍላጎት ላይ ብቻ የተመሠረቱ መሆናቸው እና የኦሮሞን ሕዝብ ፍላጎት ከማስከበር ይልቅ ለሌሎች ተገዢ ወይም አገልጋይ የሚያደርጉ በመሆናቸው በሂደቱ ላይ ትልቅ ጉዳት አምጥቷል ብለዋል።

አራተኛው የአመራር እጦት እና የአሸናፊነት ሥነ-ልቦና ማጣት ነው፦ ሕዝቡን አደራጅቶ እና አቅጣጫ አስይዞ ሊመራ የሚችል ትልቅ ዕይታ ያለው አመራር ማጣት እንቅፋት እንደነበር ነ

07/08/2026
Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Addis Ababa