Ethiopian Table Tennis Federation

Ethiopian Table Tennis Federation

Share

This is Official Face book page of Ethiopian Table Tennis Federation!! Follow and Like for updated information.

Photos from Ethiopian Table Tennis Federation's post 17/07/2026

🇬🇭 🏓 Marta Meshesha Representing Ethiopia in Ghana! 🇪🇹
The Ethiopian Table Tennis Federation (ETTF)announce that coach Marta Meshesha is in Accra, Ghana, for the ITTF Africa Hopes Week & Challenge 2026!

As a beneficiary of the ITTF "My Gender, My Strength" program, Marta’s journey highlights the power of empowering female coaches. We wish her the best of luck as she represents Ethiopia on the continental stage!

🇬🇭 🏓 ማርታ መሸሻ ኢትዮጵያን በመወከል በጋና! 🇪🇹
የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን አሰልጣኝ ማርታ መሸሻ በጋና አክራ እየተካሄደ ባለው የ ITTF Africa Hopes Week & Challenge 2026 ላይ በመሳተፍ ላይ እንደምትገኝ በታላቅ ኩራት ይገልጻል!

የ(ITTF) "My Gender, My Strength" ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆነችው አሰልጣኝ ማርታ፣ በዚህ አህጉራዊ መድረክ ላይ ሀገራችንን ወክላ ለምታደርገው እንቅስቃሴ መልካም እድል እንመኛለን!


26/06/2026

📢 የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን 22ኛው ጠቅላላ ጉባኤ 🇪🇹🏓

የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን 22ኛውን የምርጫ ጠቅላላ አመታዊ ጉባኤ ቅዳሜ ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዋሽንግተን ሆቴል ለማካሄድ የቅድመ ዝግጅት ስራዎቹን አጠናቋል።
ጉባኤው የክልሎች እና የከተማ መስተዳደር ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን ሀላፊዎች ፣ የየክለቦች ሀላፊዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በሚገኙበት ይካሄዳል።

Ethiopian Table Tennis Federation 22nd ANNUAL GENERAL ASSEMBLY🇪🇹🏓

The Ethiopian Table Tennis Federation is making final preparations to host its 22nd Election Annual generel Meeting this Saturday, June 27, 2026, at the Washington Hotel in Addis Ababa. Bringing together regional sports leaders and club executives.

26/06/2026

🚨 ለኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ሌላ ትልቅ ታሪካዊ ስኬት! 🇪🇹🏓
ኢንተርናሽናል ዳኛችን ዳንኤል ታደሰ በታዋቂው የ ITTF ወጣት ዳኞች ፕሮጀክት (Phase 2) ላይ በመመረጡ የተሰማንን ታላቅ ደስታ እየገለጽን፤ እንኳን ደስ አለህ እንላለን! 🏆✨
ዳንኤል ከሐምሌ 13–20 በጋና 🇬🇭 አክራ ለሚካሄደው የ ITTF የአፍሪካ ወጣቶች ሻምፒዮና ላይ በዳኝነት እንዲያገለግል ይፋዊ ጥሪ ተደርጎለታል!
ይህ ስኬት ለዳኛ ዳንኤል ትልቅ ደረጃ ሲሆን፤ ለፌዴሬሽናችን (ETTF) እና ለሀገራችን ስፖርት ትልቅ ኩራት ነው! ዳኞቻችን በአህጉር ደረጃ እውቅና ማግኘታቸው የስፖርታችንን ፈጣን እድገት ያሳያል። 🌍✈️
ለኢንተርናሽናል ዳኛ ዳንኤል ታደሰ መልካም እድል እንመኛለን! 🎉👏

🚨 HUGE MILESTONE FOR ETHIOPIAN TABLE TENNIS! 🇪🇹🏓
Huge congratulations to International Umpire Daniel Tadesse for being selected for Phase 2 of the prestigious ITTF Young Umpires Project! 🏆✨
Daniel has been officially invited to umpire at the upcoming ITTF Africa Youth Championships in Accra, Ghana 🇬🇭 from July 20–27!
This is a massive achievement for Daniel and a proud moment for the Ethiopian Table Tennis Federation (ETTF), proving our officials are thriving on the continental stage! 🌍✈️ Let's wish him the best of luck! 🎉👏

Daniel Tadesse

26/06/2026

🚨 ለኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ትልቅ ኩራት! 🇪🇹🏓
ለአሰልጣኝ ማርታ መሻሻ እንኳን ደስ አለሽ!
ማርታ የ2026 የITTF "My Gender. My Strength." ፕሮግራም ተጠቃሚ በመሆን፤ በመጪው ሐምሌ በጋና 🇬🇭 ለሚካሄደው የITTF-አፍሪካ ሆፕስ ሳምንት እና ቻሌንጅ የአሰልጣኞች ቡድንን እንድትቀላቀል ተመርጣለች!
በቆይታዋም ከታዋቂዋ የITTF ዋና አሰልጣኝ ኤቫ ጄለር ጋር በቅርብ በመስራት ጠቃሚ ልምዶችን የምታገኝ ሲሆን ከአፍሪካ ምርጥ ወጣት ተሰጥኦዎች ጋርም ትሰራለች። ይህ ስኬት ለማርታ ትልቅ እቅጫ ሲሆን ለፌዴሬሽናችን እና ለሀገራችን ስፖርት እድገት ደግሞ ትልቅ ድል ነው! 🌍✨
ለአሰልጣኝ ማርታ መልካም እድል እንመኛለን! 🎉👏

🚨 PROUD MOMENT FOR ETHIOPIAN TABLE TENNIS! 🇪🇹🏓
Huge congratulations to our very own Coach Martha Meshesha She has been selected for the 2026 ITTF "My Gender. My Strength." programme and invited to join the continental coaching team at the ITTF-Africa Hopes Week & Challenge in Ghana 🇬🇭 this July!
Martha will be learning directly from ITTF Head Coach Eva Jeler and working with Africa's brightest young talents. This is a massive milestone for Martha, a huge success for ETTF, and a proud moment for the growth of our sport! 🌍✨

23/04/2026

"Happy World Table Tennis Day! 🏓🌍

Celebrating the sport we love today and every day. Let’s play!

የአለም ጠረጴዛ ቴኒስ ቀን ለሁላችሁም እንኳን አደረሳችሁ! 🇪🇹

"

Photos from Ethiopian Table Tennis Federation's post 31/03/2026

19 ኛው ሃገር አቀፍ የፌደራል መንግስት ሰራተኞች የጠረጴዛ ቴኒስ ስፖርት ውድድር በአዲስ ከተማ ወወክማ እየተካሄደ ይገኛል።
10 የፌደራል የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሁለቱም ፆታ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ስፖርቱ ሰራተኞችን ከስራቸው ጐን ለጐን ጤናቸውን የሚጠብቁበት ፣ ትውውቅን እና ወዳጅነትን የሚፈጥሩበት ነው።
ፌዴሬሽኑ ለነዚህ መስሪያ ቤቶች ክለብ እንዲያቋቁሙ እና ስፖርቱን ወደተሻለ ደረጃ እንዲደርሶ የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ ያስተላልፋል ።

ውድድሩ አርብ 25 07 2018 ዓ.ም ፍፃሜውን ያገኛል ።

Photos from Ethiopian Table Tennis Federation's post 12/02/2026

የወደፊቶቹ የጠረጴዛ ቴኒስ ኮከቦች በአዳማ! 🏓

በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ባለው የመጀመሪያው ሀገር አቀፍ ከ15 ዓመት በታች የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ምዘና ውድድር ላይ የጠረጴዛ ቴኒስ ውድድሮች በቡድን እና በነጠላ በሁለቱም ፆታዎች መከናወን ጀምረዋል። በውድድሩ ላይ 6 የወንድ እና 5 የሴት ቡድኖች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን ይህ ተሳትፎ በየክልሉ በሚገኙ ታዳጊ ስፖርተኞች ላይ በትኩረት መስራት አስፈላጊ መሆኑን በግልጽ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን ከዚህ ቀደም ከነበረው ሁኔታ አንፃር በዚህ ውድድር ላይ የተሻለ የእድሜ ተገቢነት ተከብሮ በመገኘቱ የተሰማውን ደስታ ገልጾ ለክልል አሰልጣኞች እና ለባለድርሻ አካላት ምስጋናውን አቅርቧል። ፌዴሬሽኑ ለሁሉም ተሳታፊ ስፖርተኞች መልካም የውድድር ጊዜን እየተመኘ ስፖርታዊ ጨዋነት የሰፈነበት ቆይታ እንዲሆንላቸው ይመኛል።

📅 የካቲት 2018 📍 አዳማ፣ ኢትዮጵያ



Future Table Tennis Stars Shine in Adama! 🏓

The first-ever National Under-15 Youth Sports Training Assessment Competition is currently taking place in Adama, where table tennis matches have officially commenced in both team and individual event for both genders. With 6 boys' teams and 5 girls' teams participating, this event highlights the vital importance of consistently investing in youth talent across all region.

The Ethiopian Table Tennis Federation has expressed its appreciation to regional coaches and stakeholders, noting that age eligibility standards have significantly improved in this competition compared to previous years. As the games continue, the Federation extends its best wishes to all young athletes for a successful and fair competitive season .

📅 February 2026 📍 Adama, Ethiopia

Photos from Ethiopian Table Tennis Federation's post 06/02/2026

በኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ላለፉት አምስት ቀናት ሲካሄዱ የቆዩ ውድድሮች ዛሬ ፍፃሜቸውን አገኙ።

ጥር 20፣ 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን የ2018ዓ.ም 1ኛ ዙር የክለቦች ሻምፒዮና ውድድርን በአራት የእድሜ ካታጎሪ በሁለቱም ፆታ እና ለመጀመሪያ ጊዜ 1ኛ ዙር የምርጥ 16 ውድድርን በሁለቱም ፆታ ከጥር 15-19/2018ዓ.ም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ሲያካሂድ ቆይቶ ዛሬ በተካሄዱ የፍፃሜ ውድድሮች አጠቃላይ መርሀ-ግብሩን አጠናቋል።

11 ክለቦች የተሳተፉበት ውድድር በነጠላ ከ15 ዓመት በታች በወንድ ትንሳኤ ሞገስ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሴት እየሩሳሌም አያሌው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ ከ15 ዓመት በታች በቡድን በወንድ የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ፣ ከ19 ዓመት በታች በነጠላ በወንድ ለይኩን ኤፍሬም ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ እና በሴት ጅንካለም ጎሹ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እንዲሁም ከ19 ዓመት በታች በቡድን በወንድ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና በሴት ኦሜድላ ስፖርት ክለብ አሸናፊዎች ሆነዋል፡፡

ከ40 ዓመት በታች በተደረጉ ውድድሮች በወንድ ነጠላ ደራራ መኮንን እና በሴት ፌቨን ታምሩ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሸናፊዎች ሆነዋል። በተመሳሳይ ከ40 ዓመት በታች በወንድ ቡድን በተደረገ ውድድር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በሴት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አሸናፊ ሆነዋል።

ከ40 ዓመት በታች በድብልቅ ወንድ እና ከ40 ዓመት በታች በጥንድ በወንድ እና በሴት በተደረጉ ውድድሮችም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሸናፊ ሆኗል፡፡ ።

በ2018ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው የምርጥ 16 ውድድርም በኢትዮጵያ የጠረጴዛ ቴኒስ ስፖርት በተጫዋችነት፣ በአሰልጣኝነትና በመሪነት ጉልህ አሻራ አሳርፈው ላለፉት ኢንስትራክተር ሀይለየሱስ አስፋው መታሰቢያነት እንደተካሄደ ፌዴሬሸኑ አስታውቋል።

በተያያዘም በዚህ የምርጥ 16 ውድድር የሚሳተፉት ተወዳዳሪዎች በ1ኛው ዙር የክለቦች ሻምፒዮና ተሳትፈው ባስመዘገቡት ውጤትና ከዚህ በፊት በተደረጉ ውድድሮች በነበራቸው ደረጃ የተመረጡ ስፖርተኞች በሁለቱም ፆታ ያለ እድሜ ልዩነት በውጤት እንዲወዳደሩ የተደረገበት መሆኑን ፌዴሬሸኑ በማሳወቅ ስፖርተኞች እርስ በርስ ልምድ የሚቀስሙበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እና በዓለም አቀፍ የጠረጴዛ ቴኒስ የውድድር ስታንዳርድ መሰረት ተተኪ የብሔራዊ ቡድን ስፖርተኞችን ለማፍራት ዓላማ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በመጨረሻም በተለያየ የእድሜ እርከን በግልና በቡድን በተካሄዱ ውድድሮች አሸናፊ ለሆኑ ስፖርተኞቸ በየደረጃው የዋንጫ የሜዳሊያና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶ በ2018ዓ.ም የክለቦች ሻምፒዮና ለተሳተፉ ክለቦችና ጨዋታውን ለመሩ ዳኞች የመስክር ወረቀት ተሰጥቶ አጠቃላይ አሸናፊ የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ አንስቷል።

Photos from Ethiopian Table Tennis Federation's post 03/02/2026

የቶፕ 16 አሸናፊዎች (Top 16 Winners)
ታሪክ ተጻፈ! የመጀመሪያው የቶፕ 16 ውድድር ንጉሥና ንግሥት ታወቁ! 👑

በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደውና እጅግ አስደሳች የነበረው የ"ቶፕ 16" ውድድር በታላቅ ድምቀት ተጠናቋል። በኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ዓለም አዲስ ምዕራፍ የከፈቱት አሸናፊዎቻችን፦🏓

🏅 በወንዶች፡ እዮብ ሲሳይ – የጥንካሬ እና የክህሎት ተምሳሌት በመሆን አሸናፊነቱን አረጋግጧል!
🏅 በሴቶች፡ ፌቨን ታምሩ – ድንቅ ብቃቷን በማሳየት የንግሥትነቱን ዘውድ ደፍታለች!🇪🇹

ለአሸናፊዎቻችን ያለዎትን አድናቆት በኮሜንት ይግለጹላቸው! 👏🎊🏓🇪🇹

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address

Stifanos
Addis Ababa