አርሰናል daily fans page በኢትዮጵያ

አርሰናል daily fans page በኢትዮጵያ

Share

ስለ አርሰናል፦
☞የዝውውር ዜናዎች
☞የጫወታ ቅድመ ትንታኔዎ?

14/07/2026

🚨 𝐇𝐄𝐑𝐄 𝐖𝐄 𝐆𝐎!

𝐁𝐄𝐒𝐈𝐊𝐓𝐀𝐒 የመድፉ ኮከብን ቤልጄማዊውን 𝐋𝐄𝐀𝐍𝐃𝐑𝐎 𝐓𝐑𝐎𝐒𝐒𝐀𝐑𝐃 ን ከአርሰናል ማስፈረማቸውን ይፋ አርገዋል ⚪️⚫️🦅

🇧🇪እናንተ ግን የአርሰናል አመራር ብትሆኑ ሊአንድሮ ትሮሳርድን ያውም በ20ሚ ትሽጡት ነበር ?

💣እኔ ትሮሳርድ ላይ ውሳኔ ሰጪ ብሆን በአርሰናል ቤት በትንሹ 2 አመት እንዲቆይ እድል እሠጠው ነበር እናንተስ ?

14/07/2026

✅ ያለፉት አመታት የመድፉ የወሳኝ ጌሞች አክተር ሳይጠበቅ የደመቀው ኮከብ አመለ ሸጋው ሊዬ ትሮሳርድ የኢምሬት ስንብት እውን ሆኗል

ሊያንድሮ ትሮሳርድ ያኔ የሙድሪክን ፊርማ ማሳካት ባለመቻላችን በሁለተኛ አማራጭ ተይዞ ብዙ ትኩረት ሳይሰጠው ኢምሬት የደረሰ ሙድሪክ በብሪጅ ባሳለፋቸው ምስቅልቅል የበዛበት አመታት ምክንያት የመድፉ ደጋፊ እንኳንም ትሮሳርድን አስፈርምን ብሎ በብዙ ያመሰጋገነበት ሳይጠበቅ የመድፉ የጀርባ አጥንት ሆኖ ያገለገለ መድፈኛ ነው

ቀላል በሚመስል ዝውውር ኢምሬት የደረሰው ኳስን አቅልሎ የሚጫወተው ሁለገብ አመለሸጋ ጥሩ የአጨራረስ ኳስን የመረዳት ኳሊቲ ያለው የተሟላም ባይሆን የሁለት እግር ተጫዋች የሁላችንም የቅርብ ጊዜ ትውስታ የሆነውን የዌስትሀም ጌም ጨምሮ ውድ ዋጋ ያላቸውን ጎሎች ለመድፉ በማስቆጠር የሚታወቀው የወሳኝ ሙመንቶች #ንጉስ ሊዬ ጊዜው ደርሶ የኢምሬት መውጫ በር ላይ ቋሟል

አርሰናልም ሆነ ትሮሳርድ ከቱርኩ ክለብ ጋር ሙሉ ለሙሉ ተስማምተዋል ዝውውሩም በዚህ ሳምንት ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል ሊዬ ኢምሬትን ሲለቅ ለመድፉ 20 ሚሊዬን ዩሮ ገቢ አድርጎ ነው

ዝውውሩም በመድፉ ታሪክ በወጣባቸው ዋጋም ሆነ በስኬታማነታቸው ከሚነሱ ቤስት ዝውውሮች መካከል አንዱ ሆኖ በወርቃማ ታሪክ ተመዝግቧል

ሊዬ ከመድፉ ጋ የሊግ ሻምፒዬን ሆኖ መለያየቱ በጥሩ ትዝታ ኢምሬትን እንዲሰናበት ያደርገዋል

GOOD LUCK LT 🙏

Habtsha Gunners .

13/07/2026

🚨 ሮይ ኪን🗣️

"ተጫዋቾች ከሌሎች ክለቦች ይልቅ አርሰናልን እየመረጡ መምጣታቸውን አስተውያለሁ። ሌሎች ክለቦችን ትተው አርሰናልን ይመርጣሉ። ይህም ሚኬል አርቴታ ምን ያህል ጠንካራ ስራ እንደሰራ በግልጽ የሚያሳይ ነው።"

"ዞሊስ አርሰናልን ብቻ እንደሚፈልግ፣ ብሩኖ ጊማሬዝ አርሰናልን እንደሚፈልግ በግልጽ እንደተናገረ፣ እና ሞርጋን ሮጀርስ በአርሰናል ፍላጎት ምክንያት ለመጠበቅ ፈቃደኛ እንደሆነ ሰምተናል። ሁሉም ዝውውሮች ይከናወኑ ወይም አይከናወኑ፣ ይህም ክለቡ በአሁኑ ሰዓት ያለውን ከፍተኛ ተወዳጅነት ያሳያል።"

"ይህ ለአንድ አሰልጣኝ ሊሰጥ ከሚችለው ትልቁ ምስጋና አንዱ ነው። ተጫዋቾች ትልቅ ክፍያ ከመከታተል ይልቅ የአንተን ፕሮጀክት ሲመለከቱ፣ ልዩ የሆነ ነገር መገንባትህን ያሳያል። አርቴታ አርሰናልን ምርጥ ተጫዋቾች በራሳቸው ፈቃድ መቀላቀል የሚፈልጉበት ክለብ አድርጎታል።" 🔴⚪️

13/07/2026

This Goal💔 መቼም ልረሳት የማልችል ጎል⚽

Thank you Leo♥️♥️

13/07/2026

በዓለም ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ላይ የሚጫወቱ እና ከፍተኛ የገበያ ዋጋ ያላቸው Top 10 ተጨዋቾች መካከል ክለባችን አርሰናል 3 ተጫዋቾቹ ውድ ዋጋ ያላቸው ሊስት ውሥጥ ይገኛሉ አልቫሬዝን ከጨመርን ደሞ 4

SHARE 📲

13/07/2026

🚨| 𝐌𝐀𝐉𝐎𝐑 𝐁𝐑𝐄𝐀𝐊𝐈𝐍𝐆 :

🇬🇷ክርስቶስ ዞሊስ Only Arsenal ብሏል...

✍ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ግሪካዊውን የመስመር አጥቂ ክርስቶስ ዞሊስን ለማስፈረም ለክለብ ብሩዥ ይፋዊ የዝውውር ጥያቄ አቅርቧል፣ ነገር ግን ክርስቶስ ዞሊስ የዶርትመንት የዝውውር ጥያቄን ለመስማት ፍቃደኛ አልሆነም🇩🇪❌

🔰እንዲሁም ይህን ግሪካዊ ኮከብ ክርስቶስ ዞሊስን ከርሰናል ለመጥለፍ በርካታ ታላላቅ ክለቦች የዝውውር ጥያቄ ያቀረቡለት ቢሆንም ለዞሊስ ከሚከተሉት ቡድኖች የቀረቡ የዝውውር ጥያቄዎችን በሙሉ ውድቅ አድርጓል

🇩🇪 ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ❌

🇬🇬ቼልሲ ❌

🇪🇸 ሪል ቤቲስ ❌

🇮🇹 ኤሲ ሚላን ❌

🇬🇷 ተጫዋቹ ከየትኛውም ክለብ የዝውውር ጥያቄ ቅድሚያ የሚሰጠው ለአርሰናል እና አርሰናል ብቻ ነው ቀድሞውኑ ዞሊስ Only Arsenal ብሏል❤️🤍

⏳አርሰናል የክርስቶስ ዞሊስ ዝውውር ለማጠናቀቅ በሚቀጥሉት 48 ሰዓታት ውስጥ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ ይሸጋገራል ተብሎ ይጠበቃል የበርካታ ታላላቅ ክለቦችን ትኩረት የሳበውን ግሪካዊ ኮከብ ፊርማውን ለማግኘት አርሰናል ከመጋረጃ ጀርባ ስምምነቱን ለመጨረስ በከፍተ ኛ ሁኔታ እየሰራ ነው።

❌ ተጫዋቹ ፍላጎቱ አርሰናል እና አርሰናል ብቻ በለሆኑ ቸልሲዎችም በዝውውሩ ተስፋ ቆርጠዋል በአሁኑ ሰዓት ከአርሰናል ሌላ የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ ክለብ ዞሊስን ለማዘዋወር በዚህ ጉዳይ ላይ አልተሳተፈም።

🔴 ዞሊስ ምርጫው አርሰናል እና አርሰናል ብቻ ነው።

Via ✍[📰aztecapuebla]

🔴⚪️⌛️

13/07/2026

📲ማርቲን ኦዴጋርድ በኢንስታግራም ፖስቱ ያስተላለፈው መልዕክት 🇳🇴 𝐎𝐔𝐑 𝐂𝐀𝐏𝐓𝐀𝐈𝐍! 🫡❤️

🎙“ከባድ ነበር ግን እንዴት ያለ የክረምት ጀብድ ነው 🇳🇴❤️ ዋው፣ እንዴት አስደናቂ ነበር!ባሳካነው ነገር፣ በቡድናችን እና በምንጫወተው እግር ኳስ እንኮራለን። ለኖርዌዮች ሁሉ ምስጋናችን በጣም ትልቅ ነው።

📽አስማታዊ ትዕይንቶች እና የህይወት ትዝታዎች 🇳🇴🥁🛶❤️ ከዚህ ቡድን ገና ብዙ ይመጣል። በድጋሚ እንገናኝ 🫶”

🇳🇴 𝐎𝐔𝐑 𝐂𝐀𝐏𝐓𝐀𝐈𝐍! Martin Ødegaard 🫡❤️

13/07/2026

🚨Bruno Guimarães ከአርሰናል የመሀል ሜዳ አማካይ ተጫዋቾች ጋር ያለው ንጽጽር ...ጉማሬሽ ባሳልፍነው የውድድር አመት በእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ በአማካኝ በ90 ደቂቃ ያለው ቁጥራዊ መረጃ እና ከአርሰናል አማካይ ተጫዋቾች ጋር ያለው ንጽጽር ፦

🏆 የአንድ ለአንድ ግንኙነት በማሸነፍ [Duel's] : 6.1 (ከፍተኛ)

🏆ኳስ ሪከቨር በማረግ [ Recoveries]: 5.0 (በዴክላን ራይስ ብቻ ነው የሚበለጠው )

🏆ሸርተቴዎችን በማሸነፍ : 1.6 (ከፍተኛ)

💪ጉማሬሽ ወደ አርሰናል ቢዘዋወር ይህን ቡድን እንዴት ሊያጠናክረው እንደሚችል አስቡት ጉማሬሽ ከመጣልን ክለባችን አርሰናል ኳስን ከተጋጣሚ ቡድን ለማሸነፍ ለመንጠቅ የአንድ ለአንድ ግንኙነት ለማሸነፍ ቡድናችንን አንድ ደረጃ ወደፊት ያራምደዋል!

13/07/2026

🚨 የአርሰናል እና የሁሊያን አልቫሬዝ የዝውውር ወቅታዊ ሁኔታ

👉የአርሰናል ጥረት፦ መድፈኞቹ የቅድመ-ውድድር ዝግጅታቸው ከመጀመሩ በፊት የዚህን የ26 ዓመት አጥቂ ዝውውር በፍጥነት ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ግፊት እያደረጉ ነው።

👉የአርቴታ ምርጫ፦ ዋና አሰልጣኙ ሚኬል አርቴታ ተጫዋቹን የዘንድሮ ክረምት ዋነኛ የክለቡ የማጥቃት መስመር ማጠናከሪያ አድርጎ መርጦታል።

👉የተጫዋቹ ፍላጎት፦ አልቫሬዝ ወደ አርሰናል ለመዘዋወር ፈቃደኛ ቢሆንም፣ የመጀመሪያ ምርጫው ግን በስፔን ላሊጋ መቆየት ነበር።

👉የአትሌቲኮ አቋም፦ አትሌቲኮ ማድሪዶች ተጫዋቹን በስፔን ለሚገኙ ቀጥተኛ ተቀናቃኞቻቸው (ባርሴሎና ወይም ሪያል ማድሪድ) ለመሸጥ ፍጹም ፈቃደኛ አይደሉም። ይህ ሁኔታ አርሰናልን የተሻለ ዕድል እንዲኖረው አድርጎታል።

👉የዝውውር ዋጋ፦ አትሌቲኮ ማድሪድ ለተጫዋቹ ከ100 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ የሚፈልግ ሲሆን፣ አርሰናል ግን በ90 ሚሊዮን ፓውንድ አካባቢ ስምምነቱን ለመቋጨት ተስፋ አድርጓል።

👉የድርድሩ መሪ፦ የአርሰናል ስፖርቲንግ ዳይሬክተር አንድሪያ ቤርታ (ቀድሞ በአትሌቲኮ ማድሪድ የነበራቸውን ጠንካራ ግንኙነት በመጠቀም) ድርድሩን እየመሩት ይገኛሉ።

via [ Soccer bet]

13/07/2026

🔥𝐍𝐄𝐖 ...🇳🇴 𝐎𝐔𝐑 𝐂𝐀𝐏𝐓𝐀𝐈𝐍! 🫡❤️

🔰አርሰናል የማርቲን ኦዴጋርድን ውል ለማራዘም ንግግሮች በቅርቡ ሊጀምሩ እንደሚችሉ የሚያሳይ ተስፋ አለ።🔜✍️

⌛ለተጫዋቹ ቅርብ የሆኑ ምንጮች በአርሰናል ደስተኛ መሆኑን እና በአርሰናል ቤት የመቆየት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው ይናገራሉ።

✍[Tom Canton -football london]

🇳🇴 𝐎𝐔𝐑 𝐂𝐀𝐏𝐓𝐀𝐈𝐍! 🫡 በአርሰናል ቤት መቆየት አለበት ወይሥ መሸጥ አለበት ?🔜✍️

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Address

Addis Ababa