Athlete Gudaf Tsegaye

Athlete Gudaf Tsegaye

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Athlete Gudaf Tsegaye, Sport & recreation, Addis Abeba, Addis Ababa.

Photos from Athlete Gudaf Tsegaye's post 06/06/2026

አዲስ የጤና ቴክኖሎጂ ለአዲስ

ለአዲስ አበባ አዲስ የሆነ እና በአይነቱ የመጀመሪያው ነው የተባለለት የጤና አገልግሎት ተጀምሯል፡፡አግልገሎቱ የከተማችንን ህዝብ የጤና አገልግሎት በአዲስ ከፍታ ላይ የሚያስቀምጥ ነው፡፡ ይህ ብዙ የተባለለት የጤና አገልግሎት የዲ.ኤን፣ኤ (DNA) የፎረንሲንክ እና የስነ-ምረዛ ምርመራ ልህቀት ማዕከል ሲሆን ማዕከሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተመርቋል፡፡

የማዕከሉ አገልግሎት ስራ ሲጀመር አገራችን ከፍተኛ ወጪ የምታወጣባቸው የጤና ምርመራ አግልገሎቶች በአገር ውስጥ እንዲሰጡ ያስችላል፡፡ በዚህም ውጪ አገር በመላክ ረጅም ጊዜ ይወስድ የነበረው ምርመራ በአገር ውስጥ ፈጣን በሆነ መንገድ ማግኘትን ያስችላል፡፡ በዚህም በከፍተኛ ደረጃ ጊዜንም ወጪንም ይቆጥባል ተብሎለታል፡፡

ማዕከሉ ለአዲስ አዲስ የሚያሰኘው ሌላው ጉዳይ ዘመናዊ ምርመራ መስጠቱ ብቻ ሳይሆን የጤና መረጃ ማዕክል የመሆኑ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህም ማዕከሉ የDNA መረጃ ማካመቻና ማነፃፀሪያ ሲስተም (CODIS)፣ በወንጀል የተጠረጠሩ ፣ ወላጅነትን ለማረጋገጥ የሚቀርቡ የማስረጃ ጥያቄዎችን እና ተመሳሳይ የዘር መለያ ፣ የቤተሰብ ግንኙነት የዘር ሀረግ መለይትንና ማረጋገጥን የመሳሰሉ ዘመናዊ አግልግሎቶችን የሚሰጥ ዘመናዊ ማእክል ነው፡፡

ማዕከሉ ከጤና ባሻገር የአገራችንን የፍትህ ስርዓት በማገዝም እጥፍ ድርብ ጠቀሜታ እንዳለው ነው ከንቲባዋ የተናገሩት፡፡ ምክንያቱም ደግሞ የፍትህ ስርዓቱ ማስረጃዎች መካከል አንዱ በዚህ ማዕክል የሚሰጡ የDNAን አይነትና ተዛማጅ የጤና ምርመራ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ በዚህም እነዚህ አግልግሎቶች ቀልጣፋ በሆነ መንገድ ማግኘት ከተቻለ ቀልጣፋ ፍትህም ማግኘት ይቻላል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የህብረተሰቡ የመብት ጥያቄዎችን በብቃት ለመመለስ ማዕከሉ ከፍተኛ ድርሻ አለው፡፡ በእነዚህና በመሳሰሉት የማእከሉ አዳዲስ አግልግሎቶች የተነሳ አዲስ የጤና ቴክኖሎጂ በአዲስ ተጀመረ ተብሎሎታል፡፡

Photos from AMN-English's post 29/05/2026
Photos from Ethiopian Broadcasting Corporation's post 26/05/2026
Photos from የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ Addis Ababa City Communication's post 15/05/2026
Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Addis Abeba
Addis Ababa