03/05/2026
በዩናይትድ ቤት ስኬታማ መሆን ከየትኛውም ክለብ ስኬት በላይ ነው - ብሩኖ
ካፒቴን ብሩኖ ፈርናንዴሽ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ስኬታማ መሆን በየትኛውም ሌላ ክለብ የማይገኝ ደስታ ይፈጥርልኛል ብሏል።
ብሩኖ 19 ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል በሊጉ አዲስ ክብረወሰን (21) ለማስመዝገብ በቀሪ አራት ጨዋታዎች ሁለት ተጨማሪ አሲስት ይጠበቅበታል።
ደጋፊዎቻችን ዩናይትድን ወደቀደመ ከፍታው እንዲመለስ ምን ያህል ጉጉት እንዳላቸው አውቃለሁ፥ እኔም ከደጋፊዎቻችን ጋር ለክለቡ ስኬት አብሬ መጓዝና የሚቻለንን ማድረግ ነው የምፈልገው ብሏል።
ከክለቡ ጋር የካራባኦ እና ኤፍ ኤ ዋንጫዎችን ቢያሸንፍም ይህ በቂ አለመሆኑን ለስካይ ስፖርት ተናግሯል።
እነዚህን ዋንጫዎች ብናሸነፍም ክለቡም እኔም የምመኘው ስኬት ገና ስለሆን በዩናይትድ ያለኝ ውል እስከሚያበቃ ጥረታችን ይቀጥላል ሲል ተደምጧል።
02/05/2026