4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ

4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ hope sport tips to funs I wos born in basketo zone in 1987

14/09/2026

የሳምንቱ ታላቅ ፍልሚያ፡ ቢንያም ሽብሬ ከ አገረ ሰላም ጋር ፊት ለፊት ተገናኙ!

በመላው የቦክስ እና የማርሻል አርት አፍቃሪያን ዘንድ በከፍተኛ ጉጉት ሲጠበቅ የቆየው የ Ethio Fight Night ኦፊሴላዊ የFace-Off መርሃ ግብር ዛሬ በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል!

በመድረኩ ላይ ፍፁም ስፖርታዊ ጨዋነት እና መከባበር የታየበት ሲሆን፡ ሁለቱ ተወዳዳሪዎች አይን ለአይን ተጋጥመዋል። ከዝግጅቱ አስደናቂ ክስተቶች አንዱ ተወዳዳሪ አገረሰላም የሀገር ባህል ስካርፍ (Scarf) ለተቃራኒ ተወዳዳሪው ቢንያም ሽብሬ በስጦታ በማልበስ ያሳየው የወንድማማችነት እና የፍቅር ምልክት ነበር።

የፍልሚያው ሙቀት አዲስ አበባንም ለሁለት ከፍሏታል፤

* የፈረንሳይ ለጋሲዮን ልጆች የሰፈራቸውን ኮከብ ቢንያም ሽብሬን በሙሉ ድምፅ እየደገፉ ይገኛሉ።

* የሽሮሜዳ ልጆች በበኩላቸው አገረ ሰላምን ከጎኑ በመቆም ድጋፋቸውን እያጎረፉለት ነው!

ይህ ታላቅ ግጥሚያ የማንን የበላይነት ያረጋግጣል? ቀለበቱ ውስጥ ማን ድል አድርጎ ይወጣል? ሁላችንም በጉጉት የምንጠብቀው ይሆናል!

ለእርስዎ ማን የሚያሸንፍ ይመስልዎታል? ሃሳቦቻችሁን ኮመንት ላይ አስፍሩልን!

* ቢንያም ሽብሬ ወይንስ አገረ ሰላም ?

!

14/09/2026

📚❤️ ውድ ወላጆች፣ የልጆቻችንን ነገ ዛሬ እንገንባ!
ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሰ ህፃናት እንዳይቀር፤ ወደ ትምህርት ቤት እንላክ! 🎓🌱
ትምህርት የልጆቻችን መብት፣ የእኛ ኃላፊነት፣ የሀገራችን ተስፋ ነው! 🙏📖
📢 ጥሪ፦ ውድ ወላጆች፣ ልጆቻችሁን ዛሬ ወደ ትምህርት ላኩ፤ የነገ ሕልማቸውን እንዲያሳኩ ዕድል ስጧቸው!

ከባስኬቶ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን

14/09/2026

‎የላስካ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ዩኒት የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በነጌው ዕለት እንደሚጀምር አስታወቀ።
‎
‎ላስካ: መስከረም 04/2019 ዓ/ም
‎
‎የ2019 ዓ.ም የመማር ማስተማር ሥራ መስከረም 05/2019 ዓ.ም በይፋ እንደሚጀመር የላስካ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ዩኒት አስተባባሪ አቶ አንተነህ አጥናፉ አስታውቀዋል።
‎
‎ለአዲሱ የትምህርት ዘመን በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸውን ያወሱት አቶ አንተነህ ተማሪዎችና መምህራን በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱም ጥሪ አቅርበዋል።
‎
‎አስተባባሪው አክለውም የተማሪ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት በመላክ የበተሰብ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀው ተማሪዎችም የነጌው ዕለት የ2019 ዓ.ም የትምህርት ሥራ ማስጀመሪያ መሆኑን አውቀው የመማርያ ቁሳቁስ በመያዝ በየትምህርት ቤቶቻቸው እንድገኙ መልዕክት አስተላልፈዋል።
‎
‎ መስከረም 4/2019 ዓ.ም
‎ ላስካ
!

12/09/2026
12/09/2026

🏆 እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ
🔴 Sunderland 🆚 Arsenal 🔴
📅 ዛሬ | ቅዳሜ 12 ሴፕቴምበር 2026
⏰ 22:00 PM BST — በኢትዮጵያ ሰዓት 4:00 ማታ
🏟️ Stadium of Light
🔥 አርሰናል የድል ጉዞውን ይቀጥላል?
🖤❤️ ወይስ Sunderland በሜዳው ተጠቅሞ ያሸንፋል?
👇 እናንተ ግምታችሁን በኮሜንት ላይ አስቀምጡ!
Sunderland ወይስ Arsenal? ውጤቱስ ስንት ይሆናል?
📢 የፌስቡክ ገፅን ይከተሉ!
⚡ ፈጣንና እውነተኛ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ!

09/09/2026

?? 😭😭😭😭
ድንገተኛ ህልፈትህ እጅግ አሳዝኖናል። እንደ ወንድምና ወዳጅ የምናውቀው፣ በፈገግታ፣ በትህትናና በመልካም ባህሪ የተሞላው ውድ ሰው በድንገት ከመካከላችን መለየቱን ማመን ከባድ ነው።
በሥራውም በትጋትና በታማኝነት ሕዝብን ያገለገለ ልዩ ባለሙያ ነበር። በጎ ሥራውና መልካም ትዝታው ሁሌም በልባችን ይኖራል።
ውድ ካልፎ፣ ህልፈትህ ልባችንን ሰብሮታል። ከልባችን አዝነናል! 🖤😭
ለመላው ቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድና የሥራ ባልደረቦች ፈጣሪ መጽናናትና ብርታት ይስጥ።
ነፍስህን በአብርሃም እቅፍ ያኑርልን። መልካም እረፍት! 🙏🖤

09/09/2026

🏆⚽ የ2018 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሽልማት 🏆
🥇 የኢትዮጵያ ሊግ አንድ – ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ
⚽ አብዲ አየለ – ባስኬት ቡና
🔥 22 ጎሎች!
👏 እንኳን ደስ አለህ አብዲ! 🎉🏆
ይህ ሽልማት የትጋትህ፣ የችሎታህና የልፋትህ ውጤት ነው።
🌟 አንተ ገና ትልቅ ደረጃ የምትደርስ ድንቅ ተጫዋች ነህ። በቅርብ ጊዜ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ስትደርስ ለማየት እንጠብቅሃለን! 💪⚽🔥
❤️💛 የባስኬቶ ህዝብ ይወድሃል፣ ያከብርሃል፣ ከአንተም ብዙ ይጠብቃል!
👉 እናንተስ ለአብዲ አየለ ምን መልዕክት አላችሁ?
👇 የምትመኙለትን በComment አስቀምጡ! ❤️⚽
በርታ አብዲ! የባስኬቶ ኩራት! 🏆🔥





Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when 4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to 4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ:

Shortcuts

Share

Category