09/09/2025
🇸🇸
ደቡብ ሱዳን ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኃይል ለማግኘት የሚያስችል ስምምነት መፈራረም እንደምትፈልግ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ገለፁ።
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃት ላይ የተገኙት የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት እንኳን ደስ አላችሁ ብሏል።
ፕሬዚዳንቱ ግድቡ ፕሮጀክት ብቻ ሳይሆን የመስዋዕትነት፣ የአንድነትና የቆራጥነት ምልክት ነው ብለዋል።
ሳልቫኪር ግድቡ ህዝብ በአንድ ራዕይ ላይ በአንድነት ከቆመ ሃገር ምን መስራት እንደምትችል ያሳየ ነው ብለዋል።
ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ዛሬ ከኢትዮጵያ ባለፈ ለቀጣናችን የኩራት ቀን ነው በማለት ከግድቡ ከሚመነጨው ኃይል ለመጠቀም የሚያስችል ስምምነት ለመፈራረም እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።