Ameya 01 Kebele Communication

Ameya 01 Kebele Communication

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ameya 01 Kebele Communication, Sport & recreation, Ameya, Addis Ababa.

Photos from Ameya 01 Kebele Communication's post 26/04/2026

ብልጽግና ፓርቲ ህዝቡ ሲያነሳቸው ለነበሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጠ የመጣ ፓርቲ ነው - ከንቲባ ተመስገን ደጄኔ

በኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳደር 7ተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ይፋዊ የቅስቀሳ መድረክ ተካሂዷል።

ምርጫው ሰላማዊ፣ ነጻ፣ ፍትሃዊ እና ተአማኒ እንዲሆን ሁላችንም የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ተብሏል።

በመድረኩ የተገኙት የአመያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተመስገን ደጄኔ ብልጽግና ፓርቲ ህዝቡ ሲያነሳቸው ለነበሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጠ የመጣ ፓርቲ ነው ብለዋል።

ብልጽግና ፓርቲ እንደ ሀገር ለነበሩ ችግሮች ምላሽ ከመስጠት ባሻገር ተሸክመን ለተሻገርናቸው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ምላሽ እየሰጠ የሚገኝ ፓርቲ መሆኑን ተናግረዋል።

በቁጥር ብዛት ሳይሆን በሀሳብ ብዘሃነትና በላይነት የምያምነው ብልጽግና ፓርቲ ሀገር መምራት ከጀመረ ወዲህ ባሉት ጥቅት የለውጥ ዓመታት በርካታ ስኬቶች ተመስግቧል ብለዋል።

ከንቲባው ጨምረውም ፓርቲዉ በባለፉት ጥቅት ዓመታት ለህዝባችን ተስፋ ሰጪ የሆኑና ተጨባጭ ለዉጥ ያመጣ ፓርቲ እንደሆነም ገልጸው፣ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ እና የኢትዮጵያን ዕድገት በላቀ ደረጀ ላይ ለማድረስ የብልጽግና ፓርቲ ሥራዎችን በጋራ ሊናበሥራዉ ይገባል ብለዋል።

የዞኑ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊና ድጋፍ አመራር አቶ ንጋቱ ኬሃሞ በበኩላቸው መንግስት እንደ ሀገር የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በማለፍ ትላልቅ ሀገራዊ ልማቶችን እያከናወነ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል ።

የብልጽግና ፓርቲ ሰዉ ተኮር ፓርቲ በመሆኑ በሀገር ደረጀ በርካታ የልማት አጀንዳዎችን ነድፈዉ የሚንቀሳቀስና ለወደፊቱም በህዝብ ልማት ዉግንና ላይ ትኩረት ያደረገ ፓርቲ ስለሆነ የፓርቲዉ አባላት በመንግስት ጎን በመቆም የተያዘዉ ሀገራዊ ተልዕኮ እንዲሣካ በቁርጠኝነት ሊንቀሳቃሱ ይገባል ብለዋል።

በመድረኩም ላለፉት ስድስት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት ያቀረቡት የከተማው የመንግስት ረ/ተጠሪና የፖለቲካ አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታደለ ተፈራ የብልፅግና ፓርቲ በኢትዮጵያ ውስጥ ለዘመናት ሲንከባለሉ የመጡና መልስ ሳያገኙ የቆዩ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ በማድረግ ታሪክ የሰራ ፓርቲ መሆኑን ያነሱ ሲሆን ባለፉት የለውጥ ዓመታት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በዲፕሎማሲ ድሎችን በማስመዝገብ ላይ ነዉ ብለዋል።

አክለዉም የብልፅግና ፓርቲ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በድል በማጠናቀቅ ሁለንተናዊና ዘላቂ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻ እንደሚያካሂድ ጠቁመው የከተማችን ህዝብ ብልፅግናን በመምረጥ የአካባቢያችንን ብልፅግና በቀጣይ አምስት አመታት ለማረጋገጥ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ይህ መድረክ የህዝብ ለህዝብ ትስስርን የሚያጠናክር እንደሆነና ዛሬ በሙሉ ህብረተሰባችን ዘንድ በሚታየው በጎ አስተሳሰብና ወትሮዉኑ በነበረን በሀሳብ አንድነት ሀገራዊ የሆኑ የልማት ተልዕኮዎችን ከዳር ለማድረስ አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ ግላዊ አመለካከቶችን በጋራ በማረም የብልጽግና ፓርቲ የልማት አጀንዳዎችን ማሣካት ያስፈልጋል ብለዋሉ የመድረኩ ተሳታፊዎች።

በመጨረሻም በቀረበው ሰነድ መነሻ ከተሳታፊዎች ሀሳብ አስተያየት የተሰጠ ሲሆን ማላሽና የቀጣይ አቅጣጫ በማሰቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል ።‎

ዘገባው፦ የአመያ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

05/04/2026

በአመያ ከተማ አስተዳደር ከማለዳው ጀምሮ በሚካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ህዝቡ በነቂስ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበ

በኮንታ ዞን አመያ ከተማ በነገው ዕለት ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እንደሚካሄድ ተገልጿል

መጋቢት 24 ሀገራዊ ለውጡ የጀመረበትን ዕለት በመደገፍ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በነገው ዕለት በአመያ ከተማ በታላቅ ድምቀት ለማካሄድ የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን የአመያ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ ተመስገን ደጄኔ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት አስመልክቶ በአመያ ከተማ ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በነገው ዕለት ለማካሄድ የሚያስችል ሰፊ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል ።

ህብረተሰቡ በከተማዋ ከማለዳው ጀምሮ በሚካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ላይ በነቂስ በመውጣት እንዲሳተፍም ከንቲባው ጥሪ አቅርበዋል።

በሰልፉ ላይ የዞንና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮችን ጨምሮ ከየአካባቢው የተውጣጡ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊዎች እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

Photos from Ameya 01 Kebele Communication's post 23/03/2026

ከ7 ሚልየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባው የሁለተኛ ምዕራፍ ኮሪደር ልማት ሥራ የሳይት ርክክብ ተደረገ

በኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳደር አመያ 01 ቀበሌ "አራዳ" ሰፈር ከ7 ሚልየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባው የሁለተኛ ምዕራፍ ኮሪደር ልማት ሥራ የሳይት ርክክብ ተደርገዋል።

ይህንን ግንባታ ግሎሪ ኮንስትራክሽን ማህበር ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለመገንባት ከከንቲባው ጋር የሳይት ርክክብ ያደረጉት ስሆን ግንባታው በ2 ወር ውስጥ ተጠቅቆ አገልግሎት እንደሚሰጥ ታውቋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የአመያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ተመስገን ደጄኔ ፕሮጀክቱ ለከተማ ውቤትና ድምቀት ጉልህ ድርሽ ያለው ትልቅ ኘሮጀክት ስለመሆኑን ገልጸው ተቋሙ ሥራው እስከሚጠናቀቅ ድረስ በትኩረት እንደሚከታተል ተናግሯል።

ፕሮጀክቱ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ ቢሆንም፣ ወጪው ከህዝቡ በሚሰበሰብ ገቢና በከተማ አስተዳደሩ አቅም የሚሸፈን መሆኑን ጠቁመው ማህበሩ የሥራውን አስፈላጊነት ተረድተው በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ እንዲያጠናቅቁ ጥሪ አቅርበዋል።

የከተማው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ተገኝ ታደሰ በበኩላቸው የፓርቲ ኢንሼቲቭ የሆነው ኮርደር ልማት ከተማችን ለኑሮ ተስማሚ፣ ምቹ፣ ጽዱና ውብ ከተማ እንዲትሆን በትልቁ እንደሚረዳ ገልጸው ግንባታው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል አስፈላጊውን ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥቶ ተናግረዋል።

የዞኑ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ም/ኃላፊዋ ወ/ሪት ጠናዬ አወል እንዳሉት በዛሬው ዕለት የሚናስጀምረው ኮርደር ልማት ስራ ብርሃኑ ካልፋ እስከ አደባባይ የሚከናወነው የ200 ሜትር እንደሆነ የገለጹት ስሆን ከዚህ ቀደም ከተሰሩት በተለየ መልኩ ተጨማሪ የውበት እንደሚሰጥና ለከተማችን ትልቅ ውቤት እንደሚሆን ጠቁመዋል።

የግሎሪ ኮንስትራክሽን ማህበር አስተባባሪ ኢ/ር ታደለ ጌታቸው በበኩላቸው ድርጅታችን በዘርፉ ያለውን ልምድ በመጠቀም ፕሮጀክቱን በፍጥነትና በጥራት እንደሚያጠናቅቁ ገልጸዋል።

በርክክቡ ላይም የአመያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተመስገን ደጄኔ፣ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ተገኝ ታደሰ፣ የዞኑ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ም/ሀላፊዋ ወ/ሪት ጤናዬ አወልን ጨምሮ ሌሎች የከተማ አስተዳደር አመራሮችና የቀበሌ አመራሮች ሌሎች ተገኝተዋል።

Ameya Town Communication

Photos from Ameya 01 Kebele Communication's post 22/03/2026

በኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳደር አመያ 01 ቀበሌ ላለፉት ለተከታታይ 30 ቀናት ህዝብ ተሳትፎ ስከናወን የቆየው የ2018 ዓ.ም የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ሥራ የማጠቃለያ መርሀ-ግብር ተከናውኗል።

Photos from Ameya 01 Kebele Communication's post 06/03/2026

በአመያ ከተማ አስተዳደር አመያ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት G+1 ህንፃ ግንባታ ዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ እና የአመያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተመስገን ደጄኔ መሰረተ ድንጋይ አስቀመጡ።

በኮንታ ዞን በአመያ ከተማ አስተዳደር አመያ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት G+1 ህንፃ ግንባታ ዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ እና የአመያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተመስገን ደጄኔ መሰረተ ድንጋይ አስቀምጧል።

ግንባታው በአጭር ጊዜ ተጠናቆ አገ/ሎት እንደሚሰጥ ታውቋል።

መሠረተ ድንጋዩን ያስቀመጡት የኮንታ ዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ታከለ ተስፉ የትምህርት ስራ ውጤታማነት ለማረጋገጥ መንግስት ከመቼም ጊዜ በበለጠ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ትምህርት ላይ መስራት ትውልድ ላይ መስራት በመሆኑ በእውቀት፣ በክህሎትና በተግባር የተካኑ የነገ ሀገር ተረካ ትውልድን ለመፍጠር የት/ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል ማስፋፋት አስፈላጊ በመሆኑ አመያ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ለብዙ ትውልድ መሰረት የሆነች ዛሬ የሚናስጀምረው ህንጻ ግንባታ የሁላችንም ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

የአመያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተመስገን ደጄኔ ትምህርት ለልማት ሁሉ መሰረት በመሆኑ ከታች ከመሰረት ጀምሮ መስራት አስፈላጊ ነው ስሉ አንስተው ይህ የሚገነባው አመያ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ግንባታ እያጋጠመን ያለው የት/ት ስብራትን መጠገን ትልቅ አስተዋጽኦ መኖሩን ገልጸዋል።

የአመያ ከተማ አስተዳደር የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ አበራ በበኩላቸው ትምህርት ቤቱ ብዙ ዓመታት ከመቆየቱ የተነሳ እያረጀ እየሄደ ስለሆነ አሁን ላይ መንግስት ለትምህርት ስራ በሰጠው ትኩረት ትምህርትቤቶችን ደረጃቸውን ማሻሻል አለበት በሚል ዛሬ ላይ በመንግሥትና በህብረተሰብ ተሳትፎ መሰረተ ድንጋይ ማስቀመጡን ገልጸዋል።

መሠረተ ድንጋዩን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ፣ የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ገዛኸኝ ገዝሙ፣ የዞኑ የምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ ብርሃኑ አቱ፣ የከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተመስገን ደጄኔ ፣የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አጥናፉ አበራ ያስቀመጡ ሲሆን በመርሃ ግብሩ የዞንና የከተማ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

Photos from Ameya 01 Kebele Communication's post 25/01/2026

በኮንታ ዞን የአመያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ግማሽ ዓመት ከ14 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች የጤና መድህን ህክምና አገ/ሎት መስጠቱን አስታወቀ።

ሆስፒታሉ የበጀት ዓመቱን የ1ኛ ግማሽ ዓመት የቦርድ ውይይት መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ የተገኙት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪና የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ታከለ ተስፉ በዞኑ የጤና አገ/ሎት ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲደርስ የአመያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሚና ቀዳሚ መሆኑን ገልፀዋል።

ሆስፒታሉ የሚሰጧቸው አገልግሎቶች የበለጠ እንዲጠናከሩ የቦርድ ውሳኔዎች ተፈፃሚ እንዲሆኑ በማመላከት ውጤቶች የበለጠ ተጠናክረው እንዲመሩና በእናቶችና ህፃናት አገ/ሎት ላይ የበለጠ ማተኮር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ኡቴ አየለ የአመያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በዞኑ ብቸኛ ሆስፒታል በመሆኑ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ በመግለፅ የበለጠ ትኩረት በሚፈልጉ ጉዳዮችና በሽታዎች ላይ እንደጤና መምሪያ ድጋፍና ክትትል እንደሚያጠናክሩ ገልፀዋል።

የሆስፒታሉን ስታንዳርድ ለማሳደግ የሪፎርም ስራዎችን ማሻሻልና የአ/ሎት አሰጣጡን የተሻለ ማድረግ እንደሚገባም አስረድተዋል።

የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ አለማየሁ አሻ ሆስፒታሉ የሚሰጠውን አገ/ሎት ከፍ ለማድረግ በፌደራል ጤና ሚ/ር ድጋፍ የውስጥ ግንባታ የማስፋፋትና ምቹ የማድረግ ስራ ተከናውኖ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን አንስተው ከዚህም ባሻገር
በዞኑ መንግስት ድጋፍና በውስጥ ገቢ ግብዓትና መድሃኒት የማሟላት እንዲሁም የሰው ሀይል የማደራጀት ስራዎች በትኩረት እየተከናወኑ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የሆስፒታሉ ስራ አፈፃፀም የተሻለ እንዲሆን በየደረጃው እየገመገሙና የሚስተዋሉ ችግሮችን እያረሙ እንደሚገኙ ገልፀው ከተቋሙ አቅም ከፍ ያሉ ጉዳዮችን ቦርዱ ውሳኔ እየሰጠ እንዲሄድ አንስተዋል።

በግማሽ ዓመቱ ከ1.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ነፃ የህክምና አገ/ሎት መስጠታቸውን ያመላከቱት አቶ አለማየሁ በተሰጡ አገ/ሎቶች የሆስፒታሉን የሪፎርም ስራ 59% ላይ እንደሚገኝም አመላክተዋል።

የሆስፒታሉ የ6 ወራት አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን በግማሽ ዓመቱ 27,316 ህሙማን ተመላላሽ ህክምና ማግኘታቸውና ለ207 ሰዎች የአምቡላስ አገልግሎት መሰጠቱ ተገልጿል።

በሆስፒታሉ ከ2,160 በላይ እናቶች የቤተሰብ ምጣኔ አገ/ሎት ያገኙ ሲሆን ለ378 እናቶች የወሊድ አገ/ሎት ለመስጠት ታቅዶ 470 እናቶች በሆስፒታሉ የወሊድ አገ/ሎት ማግኘታቸው በሪፖርቱ ቀርቧል።

በግማሽ ዓመቱ 74 ወላድ እናቶችን ጨምሮ 223 ሰዎች የቀዶ ጥገና ህክምና ያገኙ ሲሆን 80 የሳምባ ምቹ ታማሚዎችን በመለየት የህክምና አገ/ሎት እንዲያገኙ ተደርጓል።

የሆስፒታሉ የ6 ወራት የክትባት አፈፃፀም በአጠቃላይ 85% አከባቢ እንደሚገኝ በሪፖርቱ የተገለፀ ሲሆን ከ13 ሺህ በላይ ታካሚዎች መድሃኒት ከሆስፒታሉ እንዲገኙ በማድረግ የዕቅዳቸውን 80% መፈፀም መቻሉ ታውቋል።

በ6 ወሩ ከ9.2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የጤና መድህን አገ/ሎት ከ14 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች የህክምና አገ/ሎት መስጠቱም ተመላክቷል።

የቦርዱ አባላት ባነሱት አስተያየት ሆስፒታሉ የሚሰጠው አገ/ሎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ጠቁመው ይህንንም በበለጠ ለማሻሻል የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከርና በቦርድ የሚወሰኑ ስራዎች ተፈፃሚ እያደረጉ መምራት እንደሚገባ አንስተዋል።

አክለውም በ6 ወራት በጉድለት የተስተዋሉ የህፃናት ሞት መቀነስ፣ የሰራተኛ ድስፕሊን ማረም፣ የበሽታ መከላከል ስራን መደገፍና የአገ/ሎት አሰጣጡን የበለጠ በማሳ

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Ameya
Addis Ababa