18/08/2026
አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ እባክዎ ‼
ውድና የተከበራችሁ እህት ወንድሞቼ በሙሉ ከታች በፎቶ የምትመለከቷት እህታችን ፈቲሃ ሚፍታ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ በቀቤና ልዩ ወረዳ የፈረጀቴ ቀበሌ ነዋሪ ናት‼
✍️ከዓመት በፊት በደረሰባት የጤና ችግር ምክንያት ከፈረጀቴ ተወላጆችና ከኸይር ፈላጊ ወንድሞች በተደረገላት ድጋፍ ከ200,000 ብር በላይ ወጪ ተደርጎላት ሕክምና ስታገኝ ቆይታለች። ሆኖም በአላህ ፈቃድ ህመሟ እንደገና አገርሽቶባታል። በአሁኑ ወቅትም ወራቤ ሆስፒታል ትገኛለች‼
✍️የህመሟ ተደጋጋሚ መሆኑ በሐኪሞች ከተገለጸላት በኋላ፣ የተጎዳው እግሯ እንዲቆረጥ ውሳኔ መሰጠቱ ተገልጿል። እህታችንም እንደገና “አሳክሙኝ” በማለት የእርዳታ ጥሪ አቅርባለች። አንድ ብር ብቻ ቢሆንም እንኳ ለእህታችን ትልቅ እገዛ ነው። በቻልነው አቅም እንርዳት፤ ይህንንም መልዕክት ሼር በማድረግ ለሌሎች እንዲደርስ እናድርግ‼
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)
1000604808107
📞 የእህታችን ስልክ:
+251 95 312 7278
📞 የአስተባባሪዎች ስልክ:
+251 93 777 3247 — አ/ወሃብ
+251 92 096 0867 — ፈጅሩ ሰይድ
+251 91 018 8604 — አ/ሀይ ደዋ
አላህ ሙሉ ጤናና ፈውስ ይስጣት።
የምትችሉትን በማድረግ እንርዳት፤ የማንችለውን ደግሞ በሼር እናድርስ‼ ❤️🤲
08/06/2026
ከሰሞኑ በምዕራብ አርሲ የተፈፀመውን ጥቃት አስመልክቶ ኢሰመኮ ‹አጣርቼ ደርሼበታለሁ› ያለውን መረጃ ለሕዝብ ይፋ አድርጓል። የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።
ጋዜጣዊ መግለጫ፡ ኦሮሚያ፦ በአርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ የደረሰውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች በተመለከተ
መንግሥት ተገቢውን ምርመራ በማካሄድ ተጠያቂነትን የማረጋገጥ እና ተጎጂዎችን ለመካስና ለማቋቋም የሚያስችሉ እርምጃዎችን ሊወስድ ይገባል
. . . .
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ ግንቦት 23 እና 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የተፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ ክትትል እና ምርመራ እያከናወነ ይገኛል፡፡ ኢሰመኮ ይህ መግለጫ ይፋ እስከተደረገበት ጊዜ ድረስ በአካባቢው በአካል በመገኘት ከዐይን እማኞች፣ ከተጎጂዎች፣ ከተጎጂ ቤተሰቦች፣ እና ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ባሰባሰባቸው መረጃዎችና ማስረጃዎች ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው “በተለምዶ ኦነግ ሸኔ” ታጣቂ ቡድን በፈጸመው ጥቃት የመንግሥት የጸጥታ ኃይል አባላትና ሲቪል ሰዎች መገደላቸውን፣ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን፣ የንብረት ውድመት እና ቃጠሎ መድረሱን ለማረጋገጥ ችሏል።
ኢሰመኮ በምርመራ ሂደቱ እንዳረጋገጠው በአሰኮ ወረዳ ደለተ ጫፋ ቀበሌ አካባቢ ከግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ የታጣቂዎች እንቅስቃሴ በመስተዋሉ የአካባቢው ሚሊሻዎችና የኦሮሚያ ጸረ ሽምቅ ውጊያ ፖሊስ አባላት በስፍራው በመሰማራታቸው “በተለምዶ ኦነግ ሸኔ” ተብሎ በሚጠራው ታጣቂ ቡድን እና በተሰማሩ የጸጥታ አካላት መካከል ግጭት ተፈጥሯል። ግጭቱን ተከትሎ የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ሰዎች ላይ ታጣቂ ቡድኑ ባደረሰው ጥቃት ከአካባቢው መሸሽ ባልቻሉ ኃይሉ ንጉሴ እና ሰሙ አባይነህ በተባሉ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንዲሁም በአካባቢው ከብቶች በመጠበቅ ላይ የነበረ ባቶ ሰፈኖ የተባለ የእስልምና እምነት ተከታይ በአጠቃላይ የሦስት ሲቪል ሰዎች ሕይወት ሊያልፍ ችሏል።
በተጨማሪም ቁጥራቸው ለጊዜው በውል ባልታወቁ ቤቶች ላይ ቃጠሎ መድረሱን፣ የጠለታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን መቃጠሉን፤ ቢዮ ቡጡሌ የሼክ ሙስተፋ መስጅድ አጥር ላይ ጉዳት መድረሱን፣ በድለተ ጫፋ ጤና ጣቢያ፣ በነዋሪዎች መኖሪያ ቤቶችና የንግድ መደብሮች ላይ በመደዳ ዘረፋ መፈጸሙን እንዲሁም ከ2,650 በላይ የሚገመቱ የአካባቢው ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ኢሰመኮ አረጋግጧል።
ኢሰመኮ በአርሲ ዞን በሽርካ፣ በአሰኮ፣ በአንቆሎ ዋቤ፣ ጉና እና መርቲ ወረዳዎች ላይ በታጣቂዎቹ ሲፈጸሙ የነበሩ ጥቃቶች ዳግም እንዳይከሰቱ ተገቢው ጥንቃቄ እንዲደረግ እና ጥቃት ፈጻሚዎች ላይ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ በተለያዩ ጊዜያት ማሳሰቡ ይታወሳል። መንግሥት በአካባቢው ላይ በተደጋጋሚ መሰል ጥቃቶች እና የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መከሰት መቀጠላቸው አሳሳቢ መሆኑን ከግምት በማስገባት ጥቃት በተፈጸመባቸው አካባቢዎች የጀመራቸውን ጥረቶች በማጠናከር በአስቸኳይ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እንዲሰማሩ እና ሰላምና ደኅንነትን በማረጋገጥ ነዋሪዎችን ወደ ተረጋጋ ሕይወት የመመለስ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም በመንግሥትና በሌሎች አጋር አካላት በጥቃቶቹ ምክንያት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ነዋሪዎች በቂ የሆነ የአስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ እንዲቀርብና ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ተመልሰው በዘላቂነት የሚቋቋሙበት ሁኔታ እንዲመቻች ኢሰመኮ ያሳስባል። በሌላ በኩል ኢሰመኮ ጉዳዩን አስመልክቶ ዝርዝር የምርመራ ሪፖርት ይፋ የሚያደርግ መሆኑን እየገለጸ፤ የተፈጸሙ ጥቃቶችን በአግባቡ ሳያረጋግጡ የሚሰነዘሩ ፍረጃዎችና ቅስቀሳዎች ተጨማሪ ግጭ
25/03/2026
ዛሬ ኢሻን እየሰገድን ማብራቱ ጠፍ ወዲያው ተሰግዶ እንዳለቀ አንድ ወንበር ላይ ተቀምጦ ሲሰግድ የነበረ ሰላሳ ወቹ ቤት ያለ ወጣት ንግግር ማድረግ ጀመረ ።
ወንድማችን ምክሩን ሲጀምር ዱዓ እንድታደርጉልኝ ነው ።የህይወት ተሞክሮየን ላካፍላቹህ ሲል ሀሳብ ጀመረ ። እኔ የሁለት ልጅ አባት ነኝ በፊት ላይ ልክ እንደ ኢማማችን ሀፊዝ ነበርኩ 15 ጁዝ ሀፍዤ ከላይ ጀምሬ ደሞ እየቀራሁ ነበር ። የደረሳ ሀያት ከበደኝና ታክሲ ከዛም አልፎ የከባድ መኪና ሹፌር ለመሆን በቃሁ በዚህ ሁኔታ ታዲያ ከአላህ በጣም ራኩኝ ሶላተል ጀምእ እያደረኩ መስገድ ጀመርኩ እሱም ሲከብደኝ ሶላትን ከነ ጭራሹ ተውኩት አላህ ወደሱ ሊመልሰኝ ፈለገና የሆነ ቀን ህፃናትን አድናለሁ ብየ የመኪናየን መሪ ጨርሼ ተገለበጥኩ ራዳቴ ሞተ እኔ ለተውበት ሌላ እድል ተሰጠኝ ዛሬ ሁለቱም እግሬ ውስጥ ብረት ገብቷል ወገቤ በየጊዜው ይተላል አንዳንዴ መስጅድ ተቀምጫ ትሉ ሲያስቸግረኝ ምነው ያ አላህ ወዳንተ መውሰድ ከበደህ አልቻልኩም እያልኩ አለቅሳለሁ ምናልባት ዛሬ ስምንት ጁዝ ሙራጀዓ አድርጌለሁ ሶላትም በትክክል እየሰገድኩ ነው ። አላህ ተውበትን ወፍቆኝ ራሴን በማስተካከል ላይ ነኝ ምናልባት ወላጆች ልጆቻችሁን ምከሩ አስፓልት ላይ መንገዳቸውን ይዘው ይንቀሳቀሱ ። ዛሬ እኔ መስገድ እየቻልኩ አይደለም ወገቤን ለመታከም 500 ሺ ምናምን ተጠይቄ ጓደኞቼ አስተባብረውልኝ 300ሺ አከባቢ ደርሻለሁ ከቻላቹህ እገዙኝ ካልቻላቹህ አላህ አፊያ እንዲያደርገኝ ዱዓ አድርጉልኝ ። ይህንን ፈተና አላህ ወደሱ ሊመልስኝ እየተፈተነኝ ነው እገዙኝ ሲል አለቀሰ ጀመዓው በአንድ ስሜት ቀልባችን ተሰበረ።
የመኪና አደጋ ስለገጠመኝ መጥፎ ቢሆንም የተውኩትን ማንነቴን እንዳገኝ አላህን ዳግም እንድጠጋ አግዞኛል ይበልጥ ወደ ዲኔ እንድጠጋ ደሞ አፊያየ እንዲመለስልኝ የቀረኝን ገንዘብ ሞልቼ ልታከም ወደ ልጆቼ በደስታ ልቀላቀል ይለናል ወንድማችን ።
ወንድማችንን ማገዝ የምትፈልጉ
1000713685627
አህመድ ሰኢድ ያሲን
0986226108
08/02/2026
TikTok · Blossomofem_
1965 likes, 12 comments. “Wait for it ”
05/02/2026
TikTok · canruaqakkb
172.3K likes, 1525 comments. “ ”
05/02/2026
TikTok · Heaven family 👸👸👸
8435 likes, 1703 comments. Check out Heaven family 👸👸👸’s video.
05/02/2026
TikTok · MORENINHA( RONARIA ) ❤️🩹
34.3K likes, 610 comments. “ ”
14/12/2025
3 ዓመት ሊሞላው 1 ወር ከ18 ቀን ቀርቶታል
አልተገኘም
አባት :- ልጄን አፋልጉኝ እባካችሁ ሼር አድርጉልኝ
ህፃን ማሂር ሰይድ ይባላል እድሜው ሁለት አመት ከስድስት ወር ሲሆን በጋምቤላ ክልል ማጃንግ ብሄረሰብ ዞን ሜጢ ከተማ
በ2015 ዓመት ምህረት ጥር 16, ከቀኑ 8:00 ሰዓት አካባቢ ባልታወቁ ሰዎች ሲወሰድ :-
* ባባ 😭
* ባባ 😭
* ባባ 😭
እያለ ቢጮህም ልንደርስለት ግን አልቻልንም 😭??
ይሀው 2 ዓመት
ከ10ወር ከ15 ቀን ሙሉ በመከራና በስቃይ ቆየን
እባካችሁ የኢትዮጵያ ህዝብ ልጄ አፋልጉኝ
* በጣም ናፈቀኝ
* ልጄን አፋልጉኝ
እባካችሁ
* 0911334363
* 0913915460
አባት : ሰይድ መሀመድ
🌴🌴🌴