Wolaita TV Media Supporter team

Wolaita TV Media Supporter team

Share

ወቅታዊ፣ ታማኝ እና ሚዛናዊ መረጃ የሚያገኙበት ገጽ ነው‼️ እናንተም #ፎሎው #Follow በማድረግ አበረታቱን❗️
ጥቆማ ስኖር በውስጥ መስመር ተከስት ያድርጉ
ምርትና አገልግሎት ለማስተዋወቅ ስትፈልጉ
በውስጥ መስመር ተከስት ያድርጉ!!!
👇👇👇👇👇

29/08/2026

‎🤝 ሊቨርፑል እና ኖቲንግሃም ፎረስት አቻ ተለያዩ

‎⏱️ ተጠናቀቀ
‎🔴 ሊቨርፑል 2 - 2 ኖቲንግሃም ፎረስት 🔵
‎⚽️60' አሌክሳንደር ኢሳክ ⚽️24' ዳን ንዶዬ
‎⚽️82' ቪክተር ሙኖዝ ⚽️70' ጊብስ-ዋይት (P)

29/08/2026

🇸🇪 አሌክሳንደር ኢሳክ በአዲሱ የዉድድር አመት የመጀመሪያ ጎሉን ኖቲንግሃም ፎረስት ላይ አስቆጥሯል።

29/08/2026

‎‎🌍 የ2026 የካፍ ሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ

‎⏱ እረፍት
‎⚪️ ካዌምፔ ሙስሊም ሌዲስ 1 - 0 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 🟣
‎⚽️17' ናካጎሎ

29/08/2026

‎🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿 𝗢𝗙𝗙𝗜𝗖𝗜𝗔𝗟: የ17 አመቱ ተከላካይ ማርሊ ሳልሞን በአርሰናል የመጀመሪያውን ፕሮፌሽናል ኮንትራት ተፈራርሟል።

29/08/2026

🔥 ዛሬ ቀን 8:30 በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሊቨርፑል ከኖቲንግሃም ፎረስት የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

ማን ያሸንፋል ❓❓

29/08/2026

🤣😁😂

28/08/2026

የስንቱን_ደም_የጠጣ_ባህር_ዛሬ_ደረቀ_አሉን‼️

28/08/2026

የማርሻል አርት አሰልጣኙ ማስተር ሀሰን ሞሚን ከጆኒ ጋር ለመፋለም ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ

በሀገር ውስጥ የኤምኤምኤ (MMA) ስፖርት ዘርፍ አዲስ ውጥረት የሚያነሳስ መረጃ ወጥቷል። የአፋር ክልል ተወላጅ እና የዳካይቶ ሪዩ (Dakayto Ryu) ማርሻል አርት አሰልጣኝ ማስተር ሀሰን ሞሚን፡ በቅርቡ ትልቅ ትኩረት ከሳበው ተፎካካሪ ጆኒ (Johnny) ጋር በሪንግ ውስጥ ለመጋጠም ጥሪ ማቅረባቸው ተሰምቷል።

ማስተር ሀሰን የሀገር በቀል የትግል ስፖርት እና የባህል ማርሻል አርት ጥንካሬን በኦክታጎን ውስጥ ለማሳየት ሙሉ ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን የገለፁ ሲሆን፡ አሁን ላይ የግጥሚያው መካሄድ በETFC አዘጋጆች እና በሚመለከታቸው አካላት ውሳኔ ላይ የተመሰረተ ሆኗል።

የሁለቱ ተወዳዳሪዎች የክህሎት ልዩነትና የተለያየ የስፖርት መነሻ የብዙዎችን ትኩረትስቧል።

የስፖርት ቤተሰቡ ግምት፦

• የዳካይቶ ሪዩ አሰልጣኙ ማስተር ሀሰን ሞሚን ያሸንፋሉ?
• ወይንስ የጆኒ የኤምኤምኤ ቴክኒክ የበላይነቱን ይይዛል?
እርስዎ የትኛውን ተወዳዳሪ ይደግፋሉ? አስተያየትዎን በኮመንት ያስቀምጡ።

Via

28/08/2026

ይሄ ልጅ ከዳዊት ድሪምስ የተሻለ እያነቃቃኝ ነው ቢዝነሱ ገብቶታል😁😂🤣

Photos from Wolaita TV Media Supporter team's post 28/08/2026

በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 590.08 ውጤት ያስመዘገበው ሌላኛው የኢትዮጵያ ተስፋ - ተማሪ ሮቤል ጌታቸው
*********************

በአንድ ሀገር የዕድገት ጉዞ ውስጥ ትልቁ ካፒታል የነገን ራዕይ ሰንቀው የሚነሡ ምጡቅ አዕምሮ ያላቸው ወጣቶች ናቸው።

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ሲገለጽም፣ ኢትዮጵያ መፃኢ ጊዜዋን በልበ ሙሉነት ልታስረክባቸው የምትችላቸውን ብሩህ ተስፋዎች ተመልክታለች።

ከእነዚህ ሀገር አኩሪ ኮከቦች መካከል ደግሞ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ሀድያ ዞን፣ ሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የሊች ጎጎ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነው ሮቤል ጌታቸው አንዱ ሆኖ ይጠቀሳል።

በሀገር አቀፍ ፈተናው ከፍተኛው ውጤት 591.6 ሆኖ በተመዘገበበት በዚህ ዓመት፣ ተማሪ ሮቤል ከ600 ውስጥ 590.08 ውጤት በማስመዝገብ በሀገር ደረጃ ሁለተኛውን ከፍተኛ ደረጃ ተቆናጥጧል።

ይህ አኩሪ ስኬት በአጋጣሚ የተገኘ ሳይሆን በዓላማ፣ በጠንካራ የጥናት ስልት እና በማያወላውል ትኩረት የተገነባ፣ የለፋበትን እና የደከመበትን እልህ አስጨራሽ ጉዞ የሚያሳይ የድካም ፍሬ ነው።

የሮቤል ስኬት ከኋላው ብዙ የሚነገሩ ትምህርት ሰጪ ታሪኮች አሉት። ይህም የንባብ ጊዜውን በከፍተኛ ትኩረት ማሳለፍ፣ ማስታወሻ የመያዝ እና በርካታ ጥያቄዎችን የመሥራት የዳበረ ልምድ ያለው መሆኑ ነው።

ሮቤል ለ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የተዘጋጀበት መንገድ ውጤታማ እንዳደረገው ይናገራል። ከምንም በላይ ደግሞ ለደረሰበት ከፍታ የወላጆቹ ዐሻራ ጎልቶ ይታያል። እናት እና አባቱ መምህራን መሆናቸውን እና እነሱ በትምህርት ዘርፍ ውስጥ መሆናቸው እርሱም ሙሉ ትኩረቱን ትምህርቱ ላይ እንዲያደርግ አስችሎታል።

የምናልመው ነገር ትልቅ ከሆነ የሚመጣው ውጤትም በተመሳሳይ ከፍተኛ እንደሚሆን ጽኑ እምነት አለው፤ ይህንንም በተግባር አሳይቷል።

በዚህ አስደናቂ ውጤቱ ምክንያት የክልሉ መንግሥት እና የትምህርት ቢሮ ከፍተኛ ኩራት እንደተሰማቸው በመግለጽ፣ ልዩ የማበረታቻ ሽልማት አበርክተውለታል።

ሮቤል ጌታቸው፣ ቀጣይ ጉዞው ሰማየ ሰማያትን ሰንጥቆ መብረር ነው። ከልጅነቱ ጀምሮ በልቡ ያሳደገውን የአውሮፕላን አብራሪነት (ፓይለት) ሕልሙን እውን በማድረግ፣ በአቪዬሽኑ ዘርፍ ጥሩ ቦታ የመድረስ ጽኑ ራዕይ እንዳለው አጽንኦት ሰጥቶ ይናገራል።

በእርግጥም የሮቤል ታሪክ የውጤት ብቻ ሳይሆን፣ የትልቅ ሕልም፣ የዓላማ ጽናት፣ እና የትኩረት ማሳያ ነው። እሱ ለትውልዱ አብነት፣ ለሀገሩም ሌላኛው ብሩህ ተስፋ ነው!

በዮናስ በድሉ

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address

Wolaita S**o
Addis Ababa